መነሻ ገጽ ሀዋሳ ከተማ የጨዋታ ዳሰሳ | ሀዋሳ ከተማ ከ አርባምንጭ ከተማ
ሀዋሳ ከተማቅድመ ዳሰሳአርባምንጭ ከተማየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

የጨዋታ ዳሰሳ | ሀዋሳ ከተማ ከ አርባምንጭ ከተማ

አጋራ
አጋራ

13ኛ ሳምንቱ ላይ የደረሰው የኢትዮጵያ  ፕርምየር ሊግ ቅዳሜ በሚደረጉ ሶስት ጨዋታወች ይጀመራል ከነዚህም ጨዋታወች መካከል ሀዋሳ ላይ በደቡብ ደርቢ ሀዋሳ ከተማ አርባምንጭ ከተማን ሚያስተናግድበት ጨዋታ ይጠበቃል፡፡
አርባምንጭ ከተማ በ12ኛ ሳምንት አዳማ ከተማን ሲያሸንፍ፡፡ ሀዋሳ ከተማ ከ አትዮጵያ ቡና ጋር ሊያደርገው የነበረው ጨዋታ በተለያዩ ምክንያቶች ለሌላ ግዜ መተላለፉን ተከትሎ አለመጫወቱ ይታወሳል፡፡ 

በአሰልጣኝ ውበቱ አባተ የሚሰለጥነው ሀዋሳ ከተማ  በሜዳው እንደመሆኑ መጠን በተጋጣሚው ላይ ድልን በማስመዝገብ ከመሪወቹ ያለውን የነጥብ ልዩነት ለማጥበብ እንደሚጫወት ይጠበቃል፡፡

በተመሳሳይ በእዮብ ማሌ የሚሰለጥነው አርባምንጭ ከተማ  ከወራጅ ቀጠናው ለመወጣት በጥንቃቄ በመጫወት ና በመልሶ ማጥቃት በሚገኙ ኳሶች ጎል አግብተው ሶስት ነጥብ ለማግኝት ወደ ሜዳ እንደሚገቡ ይጠበቃል፡፡   

ባለሜዳወቹ ሀዋሳዎች ከደረጉት 11 ጨዋታ 13 ነጥብ በመሰብሰብ 8ደረጃን በመያዝ በደረጃ ሰንጠረዡ ወገብ ላይ ሲቀመጡ፡፡

ተጋጣሚያቸው አርባምንጭ ከተማ ካደረጋቸው 12ጨዋታወች 9ነጥብ በመያዝ  በሊጉ ሰንጠረዥ  ግርጌ ላይ መቀመጥ ችለዋል፡፡

በሀዋሳ ከተማ በኩል ተክለማርያም፣ ሳዲቅ ሴቾ፣ ያቡን ዊሊያም ላውረንስ ላርቴ በጉዳት እና ፍሬው ሰለሞን – በቅጣት የማይሰለፉ ሲሆን፡፡

በተመሳሳይ አርባምንጭ ከተማ  ወንድሜነህ ዘሪሁን፣ ወንደሰን ሚልኪያስ፣ብርሀኑ አዳሙ በጉዳት ስያጣ ገብረሚካኤል ያዕቆብ ከ3 ጨዋታ ቅጣት በሃላ ወደ ሜዳ ይመለሳል፡፡  

ጨዋታው በመሀል ዳኛ አርቢትር ዳንኤል ግርማይ የሚመራ ሲሆን፡፡አምና ሁለቱ ቡድኖች በሀዋሳ ስታድዬም ተገናኝተው ሀዋሳ ከተማ 2-0 ማሸነፉ ይታወሳል፡፡

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀድያ ሆሳዕና ፣ ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ ወሳኝ ድል አግኝተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን መርሀግብር ሀዋሳ ከተማ ወደ ሊጉ መሪ የሚጠጋበትን ዕድል...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ፈረሰኞቹ በድል ሲቀጥሉ ንግድ ባንክ እና ድሬዳዋም አሸንፈዋል

ቅዱስ ጊዮርጊስ ተከታታይ ድሉን ወደ ቋቱ ሲከት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከጨዋታ ብልጫ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

1. ፉአድ ኢብራሂም (ኢትዮጵያ ቡና) : ከታች በተጠቀሱት 5 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ድንቅ የቅጣት ምቶች በነበሩት ጨዋታ ነገሌ ሲያሸንፍ ሀዋሳ በወልዋሎ ነጥብ ጥሏል

7 ጎሎች እና ሁለት ድንቅ የቅጣት ምት ጎሎች በነበሯቸው ሁለት ጨዋታዎች ነገሌ...