የጨዋታ ዘገባ | የይገዙ ቦጋለ ብቸኛ ግብ ሲዳማ ቡና ተከታታይ ሶስተኛ ድሉን እንዲያስመዘግብ አድርጓል

 

15ኛ ሳምንት መርሀ ግብር ትላንት ጀምሮ ዛሬም ሲቀጥል ሀዋሳ ላይ ሰበታ ከተማን ያስተናገደው ሲዳማ ቡናን በይገዙ ቦጋለ ብቸኛ ግብ 1-0 በማሸነፍ የመጀመሪያውን ዙር በድል ደምድሟል።

ሲዳማ ቡናዎች ባለፈው ሳምንት የተጠቀሙበትን አሰላለፍ ወደ ሜዳ ይዘው ሲወርዱ። ሰማያዊ ለባሾቹ የአራት ተጫዋቾች ላይ ለውጥ በማድረግ ደሳለኝ ደባሽ፣ ሳሙኤል ታየ ናትናኤል ጋንቹላን እና ጌቱ ኃ/ማርያም በቋሚ አሰላለፍ ይዘው ገብተዋል።

በቅርቡ ሂወቱ ላለፈው የቀድሞ ተጫዋች ሞገስ ታደስ ከጨዋታ በፊት የህሊና ፀሎት በመደረግ የተጀመረው ይህ ጨዋታ።


በመጀመሪያው አጋማሽ ሁለቱም ቡድኖች ሳቢ እግር ኳስ ያስመለኩቱ ሲሆን። በተለይ ባለሜዳዎቹ ሲዳማ ቡናዎች በአስፈሪው የፊት መስመራቸው ቶሎ ቶሎ በመድረስ የሰበታ ከተማ የተከላካይ ክፍል በማስጨነቅ ጥቃቶችን ሰንዝረዋል። 2ኛው ደቂቃ ላይ አበባየሁ ዮሀንስ ሳጡን ፊት ለፊት ላይ በቀጥታ መትቶ ሳሙኤል ታየ ሳያስበው በግንባሩ ገጭታ የወጣችው ምናልባትም ወደ ግቡ ቀጥታ ሄዳ ቢሆን ግብ ልትሆን የምትችልበት አጋጣሚ ነበረች። ከሶስት ደቂቃዎች በኋላ አዲሱ ተስፋዬ እቆጣጠራለው ሲል አዳልጦት ሲወድቅ አጠገቡ የነበረው ይገዙ ቦጋለ ኳሷን ተቆጣጥሮ ወደ ግብ ቢመታውም ወደ ውጪ ወጥታበታለች።


ከወትሮው በተለየ አሰልጣኝ ውበቱ አባት የግራ መስመር አጥቂያቸው ፍርዳወቅ ሲሳይን ወደ ኋላ በመመለስ የግራ ተከላካይ አድርገው ሲጠቀሙ ውጤታማ ያላደረጋቸው ሲሆን አሰልጣኙ በተደጋጋሚ ፍርዳወቅን በመጥራት ቦታውን እንዲሸፍን ሲነግሩት ሲደመጡ ነበር። በብዛት የዚህ መስመር ከፍት መሆን ጥቃቶች እንዲበረቱባቸውም አድርጓል።11ኛው ደቂቃ ሀብታሙ ገዛኸኝ ከዩሴፍ ዮሀንስ ያገኘውን ኳስ ከቀኝ መስመር ወደ ሳጥን አሻምቶ ይገዙ ቦጋለ እንደምንም ተንሸራቶ መትቶ ዳንኤል አጃዬ ተፎቶት በድጋሚ ይገዙ ቢመታውም ከመስመር ግብ ጠባቂው እንደምንም ተወርውሮ ከግቡ ከመስመር ማውጣት ሲችል።


በድጋሚ ከዚህች ሙከራ በኋላ ሀብታሙ ገዛኸኝ ያቀበለውን ሳጥን ውስጥ አዲስ ግደይ መትቶ ዳንኤል አጃዩ የተቆጣጠረበት ሲዳማ ቡና ሁለት ሁለት ለባዶ የሚመራበት አጋጣሚዎች ነበሩ።

ጥሩ የኳስ ፍሰት ቢኖራቸውም አጋጣሚ በመፍጠር ረገድ ግን ድክመት ታይቶባቸው በመጀመሪያው ግማሽ አንድ አጋጣሚ ብቻ ነበር መፍጠር የቻሉት። 16ኛው ደቂቃ ላይ ሳሙኤል ታየ በቅጣት ምት የተገኘችወን ኳስ ተጠቅሞ በቀጥታ ወደ ግብ መቶት ለጥቂት ፍቅሩ ወዴሳ በጣቶቹ ነክቶ በአግዳሚው በኩል አውጥቶበታል። በቀሪዎቹ ደቂቃዎች የኳስ ሽርሽሮች እንጂ ምንም የግብ አጋጣሚ ሳይፈጠር 0-0 በሆነ ውጤት ለእረፍት ወጥተዋል።

ከነበረው አደገኛ የአየር ፀባይ በመጠኑ ቀዝቀዝ ብሎ በመጠነኛ ካፊያ እና በበርካታውዝግቦች ታጅቦ የተደረገው የሁለተኛው አጋማሽ። እንደመጀመሪያው አጋማሽ ሁሉ ማራኪ እግር ኳስን ያስመለከተን ሲሆን። ሲዳማ ቡናዎች በተጋጣሚያቸው ብልጫን መውሰድ ችለዋል። አበባየሁ ዮሀንስ ከርቀት አክርሮ ደንኤል አጃየ የተቆጣጠረበት ኳስ ሙከራቸውን መሰንዘር የጀመሩት ባለሜዳዎቹ። አዲስ ግደይ ሳጥን ውስጥ እየገፋ ገብቶ ያደረገው ሙከራ ዳንኤል አጃየ ለጥቂት ተቆጣጠረበት እንጂ መሪ ልታደርጋቸው የምትችል የግብ ሙከራ ነበረች።

ተጠባቂው የነበረው የሶስቱም ፊት መስመር አጥቂዎች ጥምረት የተጋጣሚያቸውን መረብ ለመድፈር ያገዳቸው ነገር የለም። 55ኛው ደቂቃ ላይ ሀብታሙ ገዛኸኝ ለሳጥኑ ቅርብ ርቀት ላይ ሆኖ ደንኤል አጃየ ወዳሰፋበት ቦታ መትቶ በግብ ጠባቂው ተተፍታ ስትመለስ ያገኛትን ኳስ ይገዙ ቦጋለ በቀጥታ መትቶ ግብ በማድረግ ሲዳማ ቡናን መሪ አድርጓል።


በእረፍት ስአትም ባለፈው ሳምንት ሲዳማ ቡናዎች ከወልቂጤ ጋር በነበራቸው ጨዋታ። ከጨዋታው መጠናቀቅ በኋላ በተፈጠረው ግርግር ለተጎዱት ደጋፊዎቻቸው ለህክምና የሚሆናቸውን ገንዘብ በደጋፊዎች ማህበር አማካኝነት ከደጋፊው አሰባስበዋል።


ደቂቃዎች በገፉ ቁጥር ሲዳማ ቡና ውጤት ለማስጠበቅ ጥንቃቄ የተሞላበት አጨዋወት ሲከተሉ በአንፃሩ ሰበታ ከተማዎች የአቻነት ግባቸውን ለማግኘች ተጭነው ተጫውተዋል። 63ኛው ደቂቃ መሀል ሜዳ ላይ በሰበታ በኩል ጥሩ ሲንቀሳቀስ የነበረው ሳሙኤል ታየ ከሳጥኑ ውጭ አክርሮ መትቶ ግብ ጠባቂው ፍቅሩ ወዴሳ ገብታለች ብሎ ከቦታው ሳንንቀሳቀስ ቢቀርም የግራ ቋሚው የመለሰችበት ሰበታ ከተማዎች አቻ ልታደርጋቸው የምትችል አጋጣሚ ነበረች። በተለይም በርካታ ደቂቃዎች በተጫዋቾች ሽኩቻ እና እሰጣ ገባ ምክንያት በተደጋጋሚ ጨዋታው ሲቆራረጥ ነበር።

በተለይ በአበዛኛው ግዜ በተጫዋቾች ሽኩቻ እና እሰጣ ገባዎች ጨዋታዎች ሲቋረጡ የነበረ ሲሆን ከአስገራሚ ትእይንቶች ውጭ የግብ አጋጣሚዎችን አላስመለከተንም።

በዚህም ተቀይሮ የገባው ባኑ ዲያዋራ ከ21 ደቂቃዎች በኋላ በሁለት ቢጫ ካርድ ምክንያት የእለቱ አርቢትር ተፈሪ አለባቸው ከሜዳ አስወግደውታል። ጉዳት የደረሰብኝ እኔ ነኝ ከፈለክ እየው ጭንቅላቴ ተሰንጥቆ እየደማ ነው በማለት ተጫዋቹ ለአርቢትሩ ቅሬታውን ቢያሰማም ዝምታን የመረጡት የእለቱ ዳኛ በቀይ ከማሰናበት ወደ ኋላ አላሉም።

 

ለዚህም ተገቢ ካርድ አልተመለከትኩም በማለት ባኑ ዲያዋራ አርቢተሩን ለመደብደብ ተገልግሏል።


ሁኔታውን ለማርገብ አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ወደ ሜዳ ገብተው ለማበረድ ሞክረዋል።

በአስገራሚ ትዕይንቱ የቀጠለው ጨዋታው የእለቱ ዋና ዳኛ ተፈሪ አለባቸው እግራቸው ላይ በደረሰባቸው ጉዳት ጨዋታው ለጥቂት ደቂቃዎች የተቋረጡ ሲሆን። የሲዳማ ቡናው የህክምና ባለሞያ የህክምና እርዳታ አድርገውለት ጨዋታውን አስቀጥለዋል።


ሆኖም ግን ጨዋታው ተጨማሪ ግቦችን ሳያስተናግድ በባለሜዳዎቹ 1-0 አሸናፊነት ተጠናቋል። ይህን ተከትሎ ሲዳማ ቡና ተከታታይ ሶስተኛ ድላቸውን በማስመዝገብ የመጀመሪያውን ዙር አጠናቀዋል። ከጨዋታው መጠናቀቀ በኃላ አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ከደጋፊዎች ከፍተኛ የሆነ ተቃውሞ አስተናግደዋል።

Hatricksport website Editor

Facebook

ሚሊዮን ኃይሌ

Hatricksport website Editor