የጨዋታ ዘገባ | የአሰልጣኝ ደለለኝ ደቻሳ ወሳኝ ቅያሪ ወላይታ ድቻን ሶስት ነጥብ አስገኝታለች

 

ትላንት የጀመረው የ14ኛ ሳምንት ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዛሬም ቀጥሎ ሶዶ ላይ ባህርዳር ከተማን ያስተናገደው ወላይታ ድቻ ተቀይሮ በገባው ባየ ገዛኻኝ ብቸኛ ግብ 1-0 በማሸነፍ ተከታታይ ሶስተኛ ድሉን አስመዝግቧል።

የጦና ንቦች ሀድያ ሆሳዕና ካሸነፈው ስብስባቸው ውስጥ የአንድ ተጫዋች ለውጥ በማድረግ ያሬድ ዳዊትን በቋሚ አሰላለፍ ይዘው ሲገቡ የጣናው ሞገዶች በበኩላቸው ሰበታን ካሸነፈው አሰላለፋቸው የሶስት ተጫዋቾችን ለውጥ አድርገው ፅዮን መርዕድ፣ደረጄ መንግስቱ፣ፍቃዱ ወርቁ በቋሚ አሰላለፍ ወደ ጨዋታ ይዘው ቀርበዋል።

በመጀመሪያዎቹ አጋማሽ በሁለቱም ቡድኖች በኩል ቅብብሎች ቢኖርበትም ከሚባክኑ ረጃጅም ኳሶች ውጪ ይሀን ቅርፅ የሚመስል አጨዋወት ተከትለዋል ለማላት ያዳግት ነበር። በተለይ በጣናው ሞገድ በኩል ወደ ኋላ ያፈገፈገ ጥንቃቄ የተሞላበት ጨዋታ በመከተል ተጋጣመያቸው ኳስ ተቀባብሎ ቢሄድም የሶስተኛ ማጥቂያ ክልል ላይ እንዲቋረጥ በማድረግ ረገድ ተዋጥቶላቸዋል። በሚያገኟቸው አጋጣሚዎች ወደ ግብ በመድረስ ጥቃቶችን ሲሰነዝሩ የነበሩት ወላይታ ድቻዎች።1ኛው ደቂቃ ሰይድ እንድሪስ ያቀበለውን ኳስ ቸርነት ጉግሳ ኳሷን ተቆጣጥሮ ሳጥን ውስጥ አክርሮ መትቶ ሀሪሰተን ሄሱ ተፍቶት መልሶ የተቆጣጠራትን ኳስ የጥቃታቸው ጅማሬ ነበርች። ኳስን ተቆጣጥሮ ለመጫወት አስበው በተለይ እንደ ወትሮው ያልተቀናጀላቸው ባለሜዳዎቹ ለግብ የተቃረቡ ሙከራዎችን ቢደርጉም ወደ ግብ ለመቀየር ግን ሲቸገሩ ተስተውሏል። 25ኛው ደቂቃ ያሬድ ዳዊት በግምት ከ27 ሜትር ርቀት አክርሮ መትቶ ሀሪሰተን ሄሱ በአሰደናቂ ሁኔታ የተቆጣጠረበት እና 35ኛው ደቂቃ ቸርነት ጉግሳ ከማእዘኔ ያሻገረለትን ሰይድ እንድሪስ በግንባሩ ገጭቶ ለጥቂት ሀሪትሰን ያዳነበት ተጠቃሾች ናቸው።

የደከመውን የፊት መስመራቸው ለማጠናከር አስበው የመሀል ተከላካዩ ደጉ ደበበ በማስወጣት የፊት መስመር አጥቂውን ባየ ገዛሀኝ አስገብተው ፀጋዩ አበራን ወደ ኋላ የመለሱት አሰልጣኝ ደለለኝ ደቻሳ ቅያሪያቸው ተሳክቶላቸው ድቻዎች መሪ የሚያደርጋቸውን ግብ አግኝተዋል ።

46ኛው ደቂቃ ላይ ከእዮብ አለማየሁ ጋር ተቀባብሎ ያገኛትን አስገራሚ ኳስ ባየ ገዛኻኝ ወደሳጥን ሁለቴ ገፋ አድርጎ ገብቶ በመምታት ማራኪ ግብ በማስቆጠር በባለሜዳዎቹ 1-0 መሪነት ወደ መልበሻ ክፍል እንዲያመሩ አስችሏል።

 

በሁለተኛው አጋማሽ ፍፁም መሻሻሎችን በማድረግ ኳስን ተቆጣጥሮ የተረጋጋ እንቅስቃሴ በማድረግ በዛሪ ጨዋታ ድክም ብሎ የታየው የጦናው ንቦች የሜዳ እንቅስቃሴን ከመጀመሪያዎቹ አጋማሽ አንፃር ብልጫ እንዲወሰድባቸው ተገደዋል። 53ኛው ደቂቃ ላይ ከባየ ገዛኸኝ የተቀበለውን ኳስ ተስፋየ አለባቸው ከሳጥን ውጭ አክርሮ ቢመታውም ወደ ውጭ የወጣችበት በተጨማሪም እንድሪስ ሰይድ ከባዩ ገዛኻኝ የተቀበላትን ኳስ ሳጥኑ መስመር ላይ አመቻችቶ ያቆመለትን ኳስ ፀጋየ አበራ መትቶ ለጥቂት በአግዳሚው የወጣታችበት በወላይታ ድቻ በኩል አስቆጪ ነበሩ ማለት ይቻላል። በተለይ ባህርዳሮች የእለቱ አርቢትር ቢኒያም ወርቅአገኘው አልፎ አልፎ የሚሰራቸውን ስህተቶች ተከትሎ ሆን ብለው እየበደለን ነው በማለት በተደጋጋሚ የባህርዳር ቡድን አባላት ቅሬታቸውን ሲገልፁ ነበር።

በሁለተኛው አጋማሽ ባህርዳሮች ብቸኛው አስደንጋጭ የምትባለው ሙከራ ያደረጉት። 85ኛው ደቂቃ ደረጄ መንግስቱ ከግራ መስመር በረጅሙ ያሻማውን ኳስ ስንታየሁ መንግስቱ በግንባሩ ገጭቶ መክብብ ደገፉ እንደምንም ተወርውሮ ለጥቂት ያወጣት ኳስ ምናልባትም ባህርዳር ከተማዎችን ከጨዋታው ነጥብ ተጋርተው እንዲወጡ የምታስችል ነበረች። በጨዋታው መገባደጃም በወላይታ ድቻ በኩል ግብ የሚሆን አጋጣሚ ሳይጠቀምበት ቀርቷል። ጨዋታው በወላይታ ድቻ 1-0 አሸናፊነት ሲጠናቀቅ። ባለሜዳዎቹ ተከታታይ ሶስተኛ ድላቸውን ማስመዝገብ ችለዋል።

Hatricksport website Editor

Facebook

ሚሊዮን ኃይሌ

Hatricksport website Editor