መነሻ ገጽ ወላይታ ድቻ የጨዋታ ዘገባ| ወላይታ ድቻ ድሬዳዋ ላይ በታሪኩ ለመጀመሪያ ግዜ ድልን ተቀዳጀ
ወላይታ ድቻዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግድሬዳዋ ከተማ

የጨዋታ ዘገባ| ወላይታ ድቻ ድሬዳዋ ላይ በታሪኩ ለመጀመሪያ ግዜ ድልን ተቀዳጀ

አጋራ
አጋራ

 

በ12ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ወላይታ ድቻ ሶዶ ላይ ድሬዳዋ ከተማን አስተናግዶ ከፍፁም የጨዋታ ብልጫ ጋር በመጀመሪያው አጋማሽ ባስቆጠራቸው ግቦች 3-0 በማሸነፍ ታሪክ ፅፏል።

ሁለቱም ቡድኖች ከባለፈው ሳምንት አሰላለፋቸው የአንድ ተጫዋች ብቻ ለውጥ አድርገው ገብተዋል ባለሜዳዎቹ ደጉ ደበበን ወደ ቋሚ አሰላለፍ ሲመልሱ። ቡርቱካናማዎቹ በበኩላቸው አማኑኤል ተሾመን ይዘው ገብተዋል።

በፌደራል አርቢትር እያሱ ፈንቴ የተመራው ይህ ጨዋታ ፊሽካ ተነፍቶ ሲጀመር ግብ ተስተናግዶበታል። በዛሬው ጨዋታ ድንቅ ጥምረት በማሳየት ጨዋታው እያፈጠኑ ወደ ፊት ተጭነው በመጫወት ተጋጣሚያቸው ፋታ እንዳይሰማው ሲያደርጉ የወላት ባየ ገዛኻኝ፣ እዮብ አለማየሁ እና ቸርነት ጉግሳ ግብ ገና ከጅማሮው እንዲቆጠር አስተዋፆኦ ነበራቸው። አርባ ሰባተኛው ሰከንድ እድሪስ ሰይድ ከሬችሞንድ ኦዶንጎ እግር ስር በመንጠቅ ያቀበለውን የተመጠነች ኳስ ተጠቅሞ እዮብ አለማየሁ ግብ ጠባቂው ሳምሶን አሰፋ ኳሳ ላይ ከመድረሱ በፊት ኳሷን በመንካት ኳስ እና መረብን አገናኝቶ ባለሜዳዎቹን መሪ ማድረግ ችሏል። በመጀመሪያው አጋማ ፍፁም የበላይነት የወሰዱት የጦና ንቦች የተቃራኒ ቡድን መረብ ላይ ግብ ለማስቆጠር አላወላዱም። 13ኛው ደቂቃ ባየ ገዛኻኝ ካሳጥን ውጭ ቸርነት ጉግሳ ያቀበለውን ተጠቅሞ ሁለት ተጫዋቾችን አጋድሞ ቦታ ከከፈተ በኋላ አክርሮ በመምታት ጥሩ አቋቋም ላይ ያልነበረው ሳምሶን አሰፋ ከቆመት ሳይንቀሳቀስ በቀጥታ ግብ ሆና መሪነቱን ወደ ሁለት ከፍ አድርጓል።

ቅርፅ የሌለው አጨዋወት ሲከተሉ የነበሩት ቡርቱካናማዎቹ ለግብ የተቃረበ ሙከራ ቢያደርጉም ከተጋጣሚያቸው ጥንካሬ አንፃር እጅጉኑ ወርደው ታይተዋል። በቅብብል ስህተት ያገኛትን ኳስ ሪችሞንድ ኦዶንጎ ኳስ የሚቀበለው ተጫዋች በማጣቱ ከሳጥን ውጭ ቀለል ያለ ጥቃት ለመሰንዘር ሲገደድ መክብብ ደገፉ በትክክል ሳይቆጣጠራት ቀርቶ ገባች ሲባል ከንደገና የያዛት ኳስ ተጠቃሽ ነበረች። ዘሪሁን አንሼቦ ባጋጠመው ጉዳት ተክቶ የገባው በረከት ሳሙኤል ለተጋጣሚ ቡድን ክፍት የነበረውን የድሬዳዋ ተከላከይ ሰፍራ በመጠኑ ቢሻሻልም ግብ ከማስተናገድ ግን አልተቆጠበም። በመጀመሪያዎቹ አጋማሽ በጨዋታው ጎልቶ በመውጣት ጫና ሲፈጥር የነበረው እዮብ አለማየሁ 40ኛወ ደቂቃ ከቀኝ በቀኝ መስመር የተገኘችውን የቅጣት ምት ፀጋየ አበራ አሻምቶ ቸርን ጉግሳ በሚገባ ተቆጣጥሮ የሰጠውን ኳስ ወደ ግብነት ቀይሮ ለቡድኑ ሶስተኛ ለራሱ ሁለተኛ ግብ አስቆጥሯል። ጥቃት ለመሰንዘር ለሁለተኛ ግዜ በተጋጣሚ የግብ ክልል የተገኙት ተጋባዦቹ 19 በእጁ ግብ ቢያስቆጥሩም ጨዋታውን በጥሩ መንገድ የመሩት እያሱ ፈንቴ አይተውት የቢጫ ካርድ መዘውበታል። የወላይታ ድቻ ፍፁም የበላይነት የታየበት የመጀመሪያው አጋማሽ በባለሜዳዎቹ 3-0 መሪነት ለእረፍት ወጥተዋል።

በሁለተኛው አጋማሽ ያሬድ ሀሰንን በማስገባት የመሀል ሜዳ ክፍተታቸውን በመድፈን በመጀመሪያ አጋማሽ ከነበረባቸው ጫና አፎይታን መፍጠር የቻሉት ድሬዳዋዎቹ የተከላካይ መስመራቸውም ፍፁም መሻሻሎችን ይዞ ቀርቧል። በመጀመሪያው አጋማሽ የሚፈልጉትን ያሳኩት የሚመስሉት ድቻዎች በዚህ አጋማሽ ፍፁም ተቀዛቅዘዋል ማለት ያስደፍራል። በረከት ሳሙኤል ያደርጋቸው የነበሩ ድንቅ ብቃት እንጂ ድሬዳዋዎች ከዚህም በላይ ግብ ሊስተናግዱበት አጋጣሚዎች ነበሩ። ቸርነት ጉግሳ ከባየ ገዛኻኝ ጋር ተቀባብሎ ወደ ሳጥን እየገፋ ገብቶ አገባው ተብሎ ሲጠበቅ በረከት ሳሙኤል ተንሸራቶ በመውረድ ወደ ውጭ አውጥቶበታል። ተረጋግተው በመጫወት ረገድ ጥሩ የነበሩት እንግዳዎቹ አጋጣሚዎችን ቢፈጥሩም በደጉ ደበበ የሚመራው የተከላካይ ስፍራ የሚቀመስ አልነበረም።

ከቅብብል በዘለለ ፍሪያማ የግብ አጋጣሚዎች መፍጠር የተሳናቸው ሁለቱም ቡድኖች በቅጣት ምት ከሚገኙ አጋጣሚዎች ግብ ለማግኘት ጥረት ሲያደርጉ ይስተዋሉ ነበር። አማኑኤል ተሾመ ከቅጣት ምት ያሻማትን ኳስ ፍሬዘር ካሳ በግንባሩ ሲገጭ መክብብ ደገፉ የተቆጣጠረበት እና ያሲን ጀማል ከተመሳሳይ ቦታ ያሻማትን የቅጣት ምት ቢኒያም ፆመልሳን በግንባሩ ገጭቶ መክብብ ያዳነበት በድሬዳዋ በኩል እንደምሳሌነት የሚጠቀሱ ናቸው። ከተስፋየ አለባቸው ተመቻችታ የመጣችለት ኳስ ብቻውን የነበረው ፀጋየ ብርሀኑ ነፃ አጋጣሚ ቆራጥ ውሳኔ አለመስጠቱ በረከት ሳሙኤል ከኋላ መጥቶ ኳሱን አስጥሎታል። ጨዋታው ተጨማሪ ግብ ሳያስተናግድ በወላይታ ድቻ 3-0 አሸናፊነት መጠናቀቁን ተከትሎ ከአምስት አመታት በኋላ ድሬዳዋ ለወላይታ ድቻ እጁን በመስጠት ለመጀመሪያ ግዜ ሸንፈትን አስተናግዷል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በዝናባማው ጨዋታ በመቻል ሲረታ የጣናው ሞገድም አሸንፏል

እጅግ በከባድ ዝናብ ታጅቦ በተደረገው ጨዋታ መቻል የሊጉን መሪ ሲዳማ ቡናን 3ለ1...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀድያ ሆሳዕና ፣ ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ ወሳኝ ድል አግኝተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን መርሀግብር ሀዋሳ ከተማ ወደ ሊጉ መሪ የሚጠጋበትን ዕድል...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ፈረሰኞቹ በድል ሲቀጥሉ ንግድ ባንክ እና ድሬዳዋም አሸንፈዋል

ቅዱስ ጊዮርጊስ ተከታታይ ድሉን ወደ ቋቱ ሲከት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከጨዋታ ብልጫ...

ዋልያዎቹዜናዎችየኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን

አንጋፋው አሰልጣኝ በስማቸው የእግር ኳስ ማሰልጠኛ አካዳሚ ሊገነባላቸው ነው

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የቀድሞ አሰልጣኝ ኢንስትራክተር ሰውነት ቢሻውን ለማመስገን እና ዕውቅና ለመስጠት...