የጨዋታ ዘገባ | ኢትዮጵያ ቡና ስሁል ሽረን በግማሽ ደርዘን ጎል ዘርሮታል

 

የሁለተኛው ዙር ሁለተኛ ጨዋታ አዲስ አበባ ላይ የካሳዬ አራጌውን ኢትዮጵያ ቡናን እና በ15 ቀኑ እረፍት አሰልጣኝ ሳምሶን አየለን አጥቶ ከቀናት በፊት የቀድሞ የአዳማ ከተማ አሰልጣኝን ሲሳይም የሾመው ስሁል ሽረን ያገናኘ ሲሆን ጨዋትውም ቀዝቀዝ ባለ የደጋፊዎች ድባብ ተጀመሯል።

ከተደጋጋሚ ነጥብ መጣሎች በውሃላ በ15ተኛው ሳምንት ወላይታ ዲቻን 3-1 በመርታት ወደ አሸናፊነቱ የተመለሰው ኢትዮጵያ ቡና ጨዋታውንም እንደተለመደው ኳስን በመሬት በማንሸራሸር አልፎ አልፎ ደግሞ ኳስን መካከለኛ የአየር ኳስ በመቀባበል ነበር የጀመሩት።

በጨዋታው የመጀመሪያ አስር ደቂቃች ስሁል ሽረዎች ኳስ በረጅም ለመስመር አጥቂዎቻቸው በመጣል የማጥቃት እንቅስቃሴ ሲያደርጉ ታይቷል። በጨዋታው 4ተኛ ደቂቃ ላይ የኢትዮጵያ ቡናው አማካኝ አለምአንተ ካሳ ኳሷን በማለፍ በማድረግ ለታፈሰ ሰለሞን ያቀበልው ሲሆን ታፈሰ ኳሳን ሳይነካት የስሁል ሽረው ተከላካይ ሲመልሳት የቡናው የመስመር አጥቂ ሀብታሙ ኳሷን ወደ ግብ የሞከራት ቢሆንም ኳሷ በተከላካዮች ተመልሳ የቡናው አጥቂ አቡበከር ጋር ስታርፍ አቡበከር ያገኘውን ነፃ የግብ እድል አምክኖታል።

ከመጀመሪያው የግብ ሙከራ በኃላ ሁለቱም ቡድኖች የተቀዛቀዘ ጨዋታ አሳይተውናል በተልይ ደግሞ ስሁል ሽረዎች በጣም የወረደ የጭዋታ ፍላጎት አሳይተዋል። ሆንልም ግን አልፎ አልፎ ከፍፁም ቅጣት ውጪ ሙከራዎችን ሲያደርጉ ተስተውለዋል።

በጥሩ የጨዋታ እንቅስቃሴ የግብ እድል ለመፍጠር ሲሞክሩ የተስተዋሉ ሲሆን በእንደዚህ አይነት እንቅስቃሴ የፈጠሩትን ኳስ ሀብታሙ ታደሰ ለማመን በሚከብድ መልኩ ሲስት ተመልክተነዋል።

በጨዋታው ፍፁም የበላይነት የነበራቸው ኢትዮጵያ ቡናዎች በ9ተኛው ደቂቃ የሽረ ግብጠባቂ ምንተስኖት በሰራው ስህተት በአቡበከር ናስር አማካኝነት የጨዋታውን የመጀመሪያ ግብ ማስቆጠር ችለዋል።

ከመጀመሪያዋ ግብ መገኘት በኃላ ሌላ ግብ ለመድገም የተሻለ ተነሳሽነት ሲያሳዩ የነበሩት ኢትዮጵያ ቡናዎች ውደ ሽረ ግብ ክልል ደርሰው የቁጥር ብልጫ ሲወሰድባቸው በቃላሉ ካስ ሲነጠቁ ነበር። በአንፃሩ ሽረዎች የሚያገኟቸውን ኳሶች በረጅሙ ለአጥቂ መስመር ተጨዋቾቻቸው ቢያሻግሩም የመስመር ተጨዋቾቻቸው እና አጥቂው ኳሶችን ሲነጠቁ ተመልክተናል ሆኖም ግን የመስመር ተጨዋቹ ዲዴዬ ሌብሬ በረጅም የሚሻገሩለትን ኳሶች ተቆጣጥሮ ወደ ማጥቃት እንቅስቃሴው ለመግባት በተደጋጋሚ ቢጥርም ከቡድን አጋሮቹ በቂ ድጋፍ አለማግኘቱ ኳሶቹ እንዲመክኑበት ሆኗል።

ኳስን ተቆጣጥረው የነበሩት ኢትዮጵያ ቡናዎች በ32ተኛው ደቂቃ አጥቂው ሀብታሙ ታደሰ ወደግብ የመታትን ቀላል የሽረው ግብጠባቂ ምንተስኖት አሎ መቆጣጠር አቅቶት ሁለተኛዋ ግብ ልትቆጠር ችላለች። በግብጠባቂው ስህተት ሁለት ግቦችን ያስተናገዱት ስሁል ሽረዎች በስነልቦና ተጎድተው ይባስ የመጫወት ፍላጎታቸው ወርዶ የመጀመሪያውን 45 ደቂቃ ሲጫወቱ ተመልክተናል።

በጨዋታው የመጀመሪያው አጋማሽ መጠናቀቂያ ላይ ሀብታሙ ያሻገራት ኳስ የሽረው ተከላካይ ኳሷን በእጁ በመንካቱ ምክንያት ኢትዮጵያ ቡማዎች ፍፁም ቅጣት ምት ማግኘት ችለዋል። ፍፁም ቅጣቱን ሚኪያስ ለመምታት ቢዘጋጅም በአሰልጣኝ ካሳዬ ትዕዛዝ አቡበከር እንዲመታው ተደርጎ አቡበከርም ለቡድኑ ሶስተኛዋን ግብ ማስቆጠር ችሏል።

ከዕረፍት በኃላ ዐወትን በክፍሎም ቀይረው ያሰገቡት ስሁል ሽረዎች ወደ ጨዋታው ለመመለስ ፍላጎት እንዳላቸው በመጀመሪያው 10 ደቂቃ ማሳየት ችለዋል። ይሄ ጥረታቸው ፍሬ አፍርቶ የኢትዮጵያ ቡናው ተከላካይ ፈቱዲን ጀማል ኳስ በእጁ በመንካቱ ምክንያት ያገኟትን ፍፁም ቅጣት በሀብታሙ ሸዋለም አማካኝነት በ48ተኛው ደቂቃ አስቆጥረዋል።

ሽረዎች ግቧን ካቆጠሩ በኃላ ሌላ ግብ በመድገም ኢትዮጵያ ቡና ላይ ጫና ለመፍጠር ቢታትሩም ጥረታቸውን መና የምታስቀር ግብ ቡናዎች በአቡበከር ናስር አማካኝነት በ57ተኛው ደቂቃ አስቆጠሩ። ከአራተኛው ግብ በውላ ኢትዮጵያ ቡናዎች ፍፁም በሚባል መልኩ ጨዋትውን ተቆጣጥረው ተጨማሪ ግን ለማግኘት ሲጥሩ ታይተዋል በጥረታቸው የፈጠሩዋቸውን ኳሶች ተጨዋቾቻቸው ሲባክኑ ተስተውለዋል።

በ66ኛው ደቂቃ በጨዋትው ጥሩ እንቅስቃሴ ሲያደር የነበረው የኢትዮጵያ ቡናው ተጨዋች ሀብታሙ ቦጋለ ተጠልፎ ቡናች ፍፁም ቅጣት ምት ያገኙ ሲሆን። የቅጥቱ መቺ አቡበከር ነስሮ ለመጀመሪያው ፍፁም ቅጣት ምት ማካካሻ በሚመስል መልኩ ኳሷን አሳልፎ ለ ሚኪያስ የሰጠው ሲሆን ሚኪያስም ምንተስኖትን አስክዶ የቡድኑን 5ተኝ ግብ ማስቆጠር ችሏል።

 

በግብ የተንበሸበሹት ቡናዎች የቀሩትን ደቂቃዎች በተረጋጋ መልኩ ኳስን በመቀባበል ለማሳለፍ ሲሞክሩ ነበር ሆኖም ግን አልፎ አልፎ ወደ ግብ በመጠጋት ሙከራዎችን ሲያደርጉ ታይተዋል። ሽረዎችም ቢሆን አልፎ አልፎ ከዲዲየ ሌብሬ በመነሳት ሙከራዎችን ሲያደርጉ ነበር።

በጨዋታው ጥሩ ሲንቀሳቀስ የነበረው ሆኖም ግን ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን ሲያመክን የታየው ሀብታሙ ታደሰ በ 87ተኛው ደቂቃ ከግብ ጠባቂ ጋር ብቻ ለብቻ ሲገናኝ ኳሷንም በግሩም ሁኔታ ከፍ በማድረግ (ቺፕ በማድረግ) የጨዋታውን ማሳረጊያ ጎል ማስቆጠር ችሏል።

ኢቲዮጵያ ቡናዎች በምክትል አሰልጣኝ እየተመራ ወደ ሜድ የገባው ስሁል ሽረ ላይ ስድስት ጎሎችን በማዝነብ ለቀጣይ ጨዋታዎች የሚሆናቸውን የሞራል ስንቅ ይዘው ከሜዳ ሲወጡ በአንፃሩ ከቀናት በኃላ ስራቸውን የሚጀምሩት የሽረዎች አዲሱ አሰልጣኝ ሲሳይ አብርሐም በርካታ የቤት ስራዎች እንደሚጠብቁት ይጠበቃል።