የጨዋታ ዘገባ | አዳማ ከተማ ወልቂጤ ከተማን በመርታት ደረጃውን አሻሽሏል

 

የ17ኛው ሳምንት የጨዋታ መርሀ ግብር በይፋ በአንድ ጨዋታ ዛሬ ሲካሄድ ወልቂጤ ከተማ ከ አዳማ ከተማ አገናኝቶል ::

ጨዋታው በሁለቱም ቡድኖች ድንቅ ደጋፊዎች ሲጀመር ወልቂጤዎች የመጀመሪያዎቹን አምስት ደቂቃዎች ላይ ጫና ለመፍጠር ሲሞክሩ ሲስተዋል ከማእዘን ምት ያገኙትን የግብ እድል ሳይጠቀሙበት ቀርተዋል ::

አዳማ ከተማዎች ወሳኙን የፊት መስመር አጥቂያቸውን ዳዋ ሆቴሳ በመጀመሪያው አሰላልፍ ውስጥ አለመካተቱ በቡድኑ የማጥቃት እንቅስቃሴ የተገደበ ሆነ እንድንመለከተው አድርጎናል ::

የመጀመሪያዎቹን አስር ደቂቃዎች ላይ በሁለቱም የመስመር ክፍሎች ላይ ሲጫወት የተመለከትነው ከንአን ማርክነህ ከቀኝ መስመር በረጅሙ የተሻገረለትን ኳስ የግል ብቃቱን በመጠቀም ከሳጥን ውጭ ግሩም ጎል በማስቆጠር አዳማ ከተማን መሪ ያደረገች ጎል ማስቆጠር ችሏል ::

ከጎሉ መቆጠር በሃላ ጫና ፈጥረው መጫወት ያሰቡት ወልቂጤዎች አስደንጋጭ የሚባል ሙከራን ማድረግ ተስኖቸው ታይተዋል :: በተለይም ቡድኑ በዛሬው ጨዋታ ላይ በጫላ ተሺታ ላይ አመዝኖ የጨዋታ እንቅስቃሴውን ለማድረግ ሲሰተዋል በብዙ አጋጣሚዎች ተጫዋቹ ከጨዋታ እንቅስቃሴ ውጪ ሆኖ ለመመልከት ችለናል ::

አዳማ ከተማዎች ከጎሉ መቆጠር በሃላ አልፎ አልፎ ሙከራዎችን ሲያደርጉ በተለይም ፉአድ ፈረጃ ሞክሮ የግቡ አግዳሚ የመለሰበት ሙከራ የምታስቆጭ ነበረች ::

ወልቂጤዎች ተደጋጋሚ ጫናዎችን ለማድረግ ቢሞክሩም ጨዋታው ብዙም አስደንጋጭ ሙከራዎች ሳይታይበት የመጀመሪያው አጋምሽ ሊጠናቀቅ ችሏል ::

ሁለተኛው አጋማሽ በአዳማ 1-0 መሪነት የተጀመረ ሲሆን ወልቂጤዎች ውጤቱን ለመቀልበስ አወልን ከድርን በ አብዱልከሪም ወርቁ በተጨማሪም ፍፁም ተፈሪን በኤፍሬም ዘካሪያስ ቀይረዋል። በመጀመሪያዎቹ 10 ደቂቃዎች ኳስን ቶሎ ቶሎ ወደ ግብ ለማድረስ ሲሞክሩ የታዩት ክትፎዎቹ በተለይ በጫላ ተሺታ በኩል ኳሶችን ከተለያዩ አቅጣጫዎች በረጅም እና በአጭር በማድረስ የጫላን ፍጥነት እና የኳስ የመግፋት ብቃት ለመጠቀም ሲሞክሩ ነበር። ሆኖም ግን ጫላ ያለ ወትሮው በተደጋጋሚ ኳሶች ስሲበላሹበት እና በ አዳማ ከተማ ተጫዋቾች ሲነጠቅ ተስተውሏል።

በሁለተኛው አጋማሽ አፈግፍገው ሲጫወቱ የታዩት አዳማዎች የተገኙ ኳሶችን በረጅሙ ለፊት መስመር ተጫዋቾቻቸው እና ለአማካኙ ከንአን ማርክነህ ኳስን በማቀበል የማጥቃት እንቅስቃሴ ለመፍጠር ሲሞክሩ ነበር።

የአብዱልከሪም መቀየር ወልቂጤዎች በመህል ሜዳ ያላቸውን የበላይነት የጨመረ ቢሆንም ኳስን ወደመጨረሻው የማጥቃት ቀጠና ማሳለፍ ተስኗቸው ነበር። አሳማዎች። በዛ ብለው በመከላከል ወርቃማው ቀጠና ላይ በቂ የሆነ የቁጥር የበላይነት በመውሰድ ኳስን ሲያጨናግፉ እና ሲነጥቁ ተመልክተናል። ሆንልም ግን አልፎ አልፎ ክትፎዎቹ የሚያገኟቸውን ኳሶች አጥቂው አህመድ እና ጫላ ተሺታ ሲያምክኗቸው ነበር።

አዳማዎች በመልሶ ማጥቃቱ ብዙም ፍሪያማ አለመሆናቸውን ተከትሎ ፉአድ ፈረጃን በፈጣኑ በረከት ደስታ የቀሩ ሲሆን ቅያሬውንም ተከትሎ በረጅሙ የሚላኩ የመልሶ ማጥቃት ኳሶችን ከቀደምው በተሻለ መልኩ ለመጠቀም ሲጥሩ ታይተዋል።

አዳማዎች ቅያሪያቸው ፍሬ አፍርቶ በመልሶ ማጥቃት ያገኟትን ኳስ በረከት ደስታ ፍጥነቱን በመጠቀም ለቡድኑ ሁለተኛዋን ግብ በማስቆጠር ወደ ጨዋታው ለመመለስ ሲጥሩ የነበሩት ወልቂጤ ከተማዎች ላይ ቀዝቃዛ ውሃ የከለሰባቸው ሆኗል።

ጨዋታው መገባደጃ ላይ በአሰልጣኝ አብርሀም መብራህቱ ለብሄራዊ ቡድን ጥሪ የቀረበለት የአዳማው አማካኝ ከንአን ማርክነህ ጉዳት አጋጥሞት በሀይሌ እሸቱ የተቀየረ ሲሂሆን። ጉዳቱ ከባድ እንዳልሆነ እና ብሄራዊ ቡድኑን ሙሉ ጤንነት እንደሚቀላቀል ለማወቅ ተችሏል።

የጨዋትውን ውጤት ተከትሎም አሸናፊው አዳማ ከተማ ወልቂጤን በግብ በልጦ በ22 ነጥብ 6ተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ወልቂጤ ከተማ ደግሞ 7ተኛን ደረጃ በተመሳሳይ 22 ነጥብ በግብ ክፍያ ተበልጦ መያዝ ችሏል።

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor