የጨዋታ ዘገባ | በአዝናኙ ጨዋታ ሀዋሳ ከተማ ከመመራት ተነስቶ ፋሲል ከተማን አሸንፏል

ዛሬ ከተደረጉ የ15ኛ ሳምንት ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሀዋሳ ላይ ፋሲል ከተማን ያስተናገደው ሀዋሳ ከተማ ከመመራት ተነስቶ 3-2 አሸንፎ የመጀመሪያውን ዙር በድል ዘግቷል።

 

ባለሜዳዎቹ ባለፈው አስከፊ ሽንፈት ካስተናገዱበት ጨዋታ የስድስት ተጫዋቾች ለውጥ በማድረግ ሀብቴ ከድር፣ዳንኤል ደርቤ፣ አሰጨናቂ ሉቃስ፣መስፍን ታፈሰ፣ዘላለም ኢሳያስ እና ሄኖክ ደልቢን ወደ ቋሚ አሰላለፍ ይዞ ወደ ሜዳ ሲገቡ። ፋሲሎች ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ነጥብ በተጋሩበት ጨዋታ የሁለት ተጫዋቾች ለውጥ አድርገዋል ሰይድ ሀሰን።፣ሀብታሙ ተከስተን ወደ ቋሚ መልሰዋል።

ከጨዋታው መጀመር አስቀድሞ የእለቱ አራተኛ ረዳት ፌደራል ዳኛ አዳነ ወርቁ የዳኝነት  ሙያ ባልተላበሰ ባህሪይ የመገናኛ ብዙሀን ጋር ሰጣ ገባ ውስጥጠ የገቡ ሲሆን። ለመገናኛ ብዙሀን አንፈቅድም በማለት ወደ ሜዳ እንዳንገባ የከለከሉን ቢሆንም ከብዙ ጭቅጭቆች በኋላ በስተመጨረሻ ፈቅደዋል።


በኢንተርናሽናል አርቢትር በአምላክ ተሰማ ያለምንም እንከን የተመራው ይህ ጨዋታ ሁለቱም ቡድኖች ኳስ ተቆጣጥረው የሚጫወቱ ቡድኖች አኳያ ፈጣን እና ቶሎ ቶሎ ወደ በመድረስ በርካታ ሙከራዎችን አድርገዋል። በተለይ በመጀመሪያዎቹ 20 ደቂቃዎች ፍፁም የበላይነት የነበራቸው አፄዎቹ ኳስ እና መረብን ለማገናኘት አራት ደቂቃዎ ብቻ ፈጅቶባቸዋል። ጥሩ የሚባል የኳስ ቅብብል ላይ የተመሰረተችውን ኳስ በዛብህ መለዮ ብቻውን ለነበረው ኢዙ አዙካ አቀብሎት አመቻችቶ ካቆመ በኋላ ከሳጥን ውጭ አክርሮ መትቶ ግብ አድርጎ ፋሲልን ቀዳሚ አርጓል።


የግራ አጥቂያቸው ስፍን ታፈሰ በተሰለፈበት የግራ መስመር አቅጣጫ በማጋድል ወደ ግብ ለመድረስ የሞከሩት ሀይቆቾ። በፈጣን ቅብብል በፍጥነት ፋሲል ግብ ክልል ላይ የተገኙት መስፍን ታፈሰ ሳጥን ውስጥ ብቻውን ይዞ የገባው ኳስ አገባው ሲባል ወደ ውጭ ልኳታል። በድጋሚ ዳንኤል ደርቤ ከርቀት አክርሮ መትቶ ግብ ጠባቂው ሚካኤል ሳማኪ እንደምንም ተወርውሮ ያወጣበት አስደንጋጭ ሙከራ ነበረች።


የሀብቴ ከድርን በዛሬ ጨዋታ ድክመት በሚገባ የተረዳው ሱራፌል ዳኛቸው በተደጋጋሚ ከርቀት አክርሮ በመምታት ግብ ጠባቂውን ፈታ ሲነሳው ተስተውሏል። በዚህም 15ኛው ደቂቃ ላይ ሱራፌል ዳኛቸው ከመሀል ሜዳ አክርሮ በመምታት የሀብቴ ከድር ጥሩ ያልሆነው አቋቋም ግብ እንዲያስተናግድ አድርጎ መሪነቱን ወደ ሁለት ከፍ አድርጓል።

ከዝች ግብ መቆጠር በኋላ የሀዋሳ ከተማ ደጋፊዎች በአሰልጣኝ አዲሴ ካሳ ላይ ከፍተኛ ተቃውሞ ሲያደርሱ የተሰተዋለ ሲሆን። አሰልጣኙ በምላሹ ወደ ደጋፊው በመዞር ኮፍያቸውን በማውለቅ ለደጋፊው ያላቸውን ክብር ገልፀዋል።

ብልጫቸውን በሚገባ ሲጠቀሙ የነበሩት ፋሲሎች ሙጂብ ቃሲም ወደ ሳጥኑ መረት ለመሬት ያቀበላትን ኳስ ኢዙ ወደ ግብ ቢሞክረውም ሀብቴ ከድር በእግሩ ተንሸራቶ ሲመልስበት። መልስ የሰጡት ሀዋሳ ከተማዎች መስፍን ታፈሰ ያቀበለውን ኳስ ዳንኤል ደርቤ ሲሞክር ሳማኪ ያለቀላት ኳስ አድኖበታል። ከዝች ሙከራ በኋላ ሱራፌል ግብ ካገባበት ተመሳሳይ ቦታ ላይ ሙከራ አድርጎ ለጥቂት በአግዳሚው የወጣችው አስደንጋጭ ነበረች።


የነበራቸውን ፈጣን አጨዋወት ቀስጠበቀስ እየተቀዛቀዙ የመጡት ፋሲሎች በተጋጣሚያቸው ፍፁም ብልጫ ተወስዶባቸው በርካታ ግቦች እንዲያስተናግዱ አድርጓቸዋል። 20ኛው ደቂቃ የፊት አጥቂው ብሩክ በየነ ግብ አስቆጥሮ የሀዋሳን ተስፋው ማለምለም ሲችል።ከሶስት ደቂቃዎች በኋላ ባለሜዳዎቹ በሄኖክ ደልቢ አማካኝነት አቻ መሆን ችለዋል።

ከፍተኛ ተቀውሞ ሲስተናግዱ የነበሩት አዲሴ ካሳ ወደ ደጋፊው በመዞር ደስታቸውን ገልፀዋል።

የመጀመሪያ አጋማሽ ሳይጠናቀቅ የነበራቸውን ጫና በመጠቀም መሪ ለመሆን ሲታትሩ የነበሩት ሀይቆች። 34ኛው ደቂቃ ዘላለም ኢሳያስ ከማእዘን ያሻገረውን ኳስ ተስፋየ መላኩ በግንባሩ ሲገጭ በድጋሚ መስፍን ታፈሰም በግንባሩ  ገጭቶ ግብ በማድረግ ሀዋሳን መሪ አድርጓል። ግቧ ከተቆጠረች በኋላ ተጫዋቾች ወደ አሰልጣኝ አዲሴ ካሳ በመሄድ ደስታቸውን በመግለፅ ተቃውሞ በርትቶባቸው የነበሩት አሰልጣኙ ተጫዋቾቹ ከጎናቸው መሆናቸውን አሳይተዋል።

የተጫዋቾች አጋርነት የተመለከቱት አዲሴ ካሳ ያላቸውን ፍቅር እያለቀሱ በእንባ ገልፀውላቸውል።

ተመጣጣኝ የሚመሰል የነበረው የመጀመሪያው አጋማሽ ቀስ በቀስ እንግዳዎቹ ብልጫን በመውሰድ ጫና ፈጥረው ሲጫወቱ። የመሀል ሜዳዎቹ በዛብህ መለዮ፣ሱራፌል ዳኛቸው፣ሀብታሙ ተከስተ ጥምረት በዚህ አጋማሽ አስደናቂ ነበር። 51ኛው ደቂቃ መስፍን ታፈሰ ከግራ መስመር ያሻገረለትን ብሩክ በየነ በግንባሩ ቢገጨውም ወደ ላይ ወጥታበታለች። 57ኛው ደቂቃ ሙጂብ ቃሲም ከፍ አድርጎ የሰጠውን ኳስ በዛብህ መለዮ የሀዋሳ ተከላካዮችን መዘናጋት ሳይጠቀምበት ቀርቶ በግንባሩ ገጭቶ ወደ ውጭ የወጣቸው በሁለቱም ቡድኖቹ በኩል የሚጠቀሱ ጥሩ ሙከራዎች ነበሩ። በጨዋታው መሀል እሰጣ የብሩክ በየነ እና ሚካኤል ሳማኪ እሰጣገባ ተከትሎ የፋሲል ከተማ ቡድን መሪ ሀብታሙ ዘዋለ እየተበደልን ነው በማለት ከአራተኛው ደኛ ላይ ቁጣቸውን ገልፀዋል።

64ኛው ደቂቃ ተቀይሮ የገባው አለምብርሀን ይግዛው ከመአዘን አከባቢ ያሻገረውን ሙጂብ ቃሲም በግሩም ሁኔታ ዘሎ በግንባሩ ቢገጨውም በአግዳሚው ወጥታበታለች። ጫናዎችን በማበርታት ግቦችን ሲያነፈንፉ የነበሩት ፋሲሎች ሙጂብ ቃሲም ማእከል አድርጋ የተነሳችው ኳስ ያገኘው ሱራፌል ዳኛቸው ከርቀት አክርሮ መትቶ ለጥቂት ሀብቴ ከድር በጣቶቹ ነክቶ ያወጣበት አቻ የምታደርጋቸው አጋጣሚ ነበረች።

በቀሪዎቹ ደቂቃዎች በብሩክ በየነ እና መስፍን ታፈሰ ወደ ፊት ሲያደርጉት ከነበረው አስፈሪ አካሄድ ውጪ ምንም የግብ አጋጣሚዎችን አልፈጠሩም። ጨዋታው ተጨማሪ ግቦች ሳያስተናግድ በመጀመሪያው አጋማሽ በተቆጠሩ ግቦች ሀዋሳ ከተማዎች 3-2 አሸንፈው ወጥተዋል። ከጨዋታው መጠናቀቅ በኋላ በደጋፊወች መካከል ግጭት ቢፈጠርም ወደ ከፋ ደረጃ ከመሄዱ በፊት የፀጥታ ሀይሉ በቁጥጥር አውለውታል።

 

Hatricksport website Editor

Facebook

ሚሊዮን ኃይሌ

Hatricksport website Editor