የጨዋታ ዘገባ | ቅዱስ ጊዮርጊስ ከአዳማ ጋር ነጥብ ተጋርቷል

 

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 15ኛ ሳምንት ዛሬ ፍፃሜውን ሲያገኝ አዲስ አበባ ስታዲዮም ላይ ቅዱስ ጊዮርጊስ አዳማ ከተማን አስተናግዶ 0-0 በሆነ ውጤት ነጥብ ተጋርቶ ወጥቷል።

 

ከባለፈው ሳምንት አሰላለፋቸው ምንተስኖት አዳነ፣አብዱልከሪም መሀመድ፣ ሰልሀዲን ሰይድ አቡበከር ሳኒን ፈረሰኞቹ በቋሚ አሰላለፍ ሲጠቀሙ። አዳማዎች ሱሌይማን መሀመድን ይዘው ገብተዋል።

በጥቂት ደጋፊዎች ታጅቦ የተጀመረው ይህ የመጀመሪያዎቹ አጋማሽ እጅግ አሰልቺ የሚባል ነበር። በተለይም በዚህ አጋማሽ ንቁ ያልነበሩት ፈረሰኞቹ የመሀል ተአላካዩ ምኞት ደበበ የትኩረት ማነስ እና ግብ ጠባቂው ጃኮፕ ፔንዝ ተደጋጋሚ ኳስ ለመቆጣጣር ሲሳነው ብሎም ለሚሰነዘርበት ጥቃት ቆራጥነት የሌለው ምላሽ ሳይጠቀሙበት ቀርተዋል። ሙላለም መስፍን ያሻገረለ ኳስ አቤል ያለው ሳይጠቀምበት የቀረችው አጋጣሚ የዚህ ሂደት ቁልጭ አድርጋ የምታሳይ ነበረች። አስደንጋጭ ሙከራን ያደረጉት ባለሜዳዎቹ 5ኛው ደቂቃ ከቅጣት ምት የተሻገረችውን ምንተስኖት በግንባሩ ገጭቶ ለጥቂት በአግዳሚው ወጥታበታለች።

ወደ ቀኝ መስመር በማድላት ከተለመዳው አጨዋወታቸው ውጪ ኳስን ይዘው ተረጋግተው ለመጫወት ሲሞክሩ የነበሩት አዳማ ከተማዎች። አልፎ አልፎ በሚያገኟቸው ኳሶች ወደ ፊት በመጣል በመልሶ ማጥቃት ወደ ተጋጣሚ ለመድረስ ችለዋል።17ኛው ደቂቃ ሱሌማን መሀመድ ከማእዘን የተሻማችውን ኳስ ሳጥን ውስት መሬት ለመሬት አክርሮ ሲመታ በአብዱልከሪም መሀመድ ተደርባ ስትመለስ ከንአን ማርክነህ መትቶ ማታሲ ለጥቂት የተቆጣጠረበት መሪ ልታደርጋቸው የምትችል አጋጣሚ ነበረች። ጌታነህ ከበደ ከቅጣት ምት ያሻማትን ፍሪምፖንግ ሜንሱ በእግሩ መትቶ ለጥቂት አግዳሚውን ለትማ የወጣችው ደግሞ በፈረሰኞቹ በኩል መሪ ሊሆኑ የሚችሉበት እድል ነበረች።


አዳማዎች ኳስ ለመቆጣጠር የሚያደርጉት ጥረት የሚቆራረጠው ቅብብላቸው ውጤታማ መሆን አልቻሉም። ጊዮርጊሶች በፊት መስመሮቻቸው በኳስ ንክኪ ለመድረስ ወደ ግብ ቢሞክሩም ሰብረው በመግባት ግብ ለማስቆጠር ግን ተቸግረዋል። 44ኛው ከሳጥኑ አፋፍ ላይ ዳዋ ሆቴሳ አክርሮ መትቶ ወደ ውጭ ስትወጣ። የመጀመሪያው ግማሽ ግብ ሳይቆጠሩበት ሁለቱም ቡድኖች ለእረፍት ወጥተዋል።

ሁለተኛው አጋማሽ ከመጀመሩ በፊት ከቅርብ ቀናቶች በፊት ህይወቱ ላለፈው የቀድሞ የቅዱስ ጊዮርጊስ ተጫዋች ሞገስ ታደሰ የህሊን ፀሎት ተደርጓል።

ከመጀመሪያው አጋማሽ ይልቅ በአንፃራዊ መሸሻሎች የታዩበት ይህ አጋማሽ ፈረሰኞቹ ወደ ግብ በመድረስ ሙከራወችን ቢያደርጉም በተለይም ግብ ለማስቆጠር የነበራቸው ጉጉት ያገኙትን አጋጣሚ ተረጋግተው የፈለጉትን እንዳያሳኩ አድርጓቸዋል።ጌታነህ ከበደ ከቅጣት ምት ወደ ሳጥኑ ሲያሻማ መንተስኖት አዳነ ከመውጣቷ በፊት እንደምንም በግንባሩ ገጭቶ ሲመልሳት ፍሪምፖንግ ሜንሱ ተቀልብሶ ቢመታውም ለጥቂት ወጥታበታለች። አቤል ያለው ምጥኖ ወደ ሳጥኑ የላከለትን ኳስ ሰልሀዲን ሰይድ በግንባሩ ቢገጨውም ፔንዝ በቀላሉ ተቆጣጥሮበታል። ሄኖክ አዱኛ መሬት ለመሬት አክርሮ መትቶ ሳጥን ውስጥ ሰልሀዲን ቢቆጣጠራትም ባለመናበብ ችግር አቤል ያለው መትቶ ወደ ውጭ የወጣችበት እንደ አብነት ማንሳት ይቻላል።


በተጠንቀቅ ግባቸውን አስከብረው በአዲስ ህንፃ ኳስ ነጣቂነት እና አደረጃጀት ወደፊት ለመድረስ ሲጥሩ የነበሩር ባለሜዳዎቹ። ሱሌማን መሀመድ ሳጥን ውስጥ ብቻውን ይዞ ገብቶ ሊያቀብል ሲሞክርፐማታሲ እንደምንም የያዛት ኳስ ብታልፍ ኖሮ ግብ የምትሆንበት አጋጣሚ ነበራት።

አቡብከር ሳኒ ያቀበለውን ኳስ አቤል ያለው ወደ ሳጥኑ እየገፋ ገብቶ አገባው ሲባል ወደ ላይ የወጣችው እና። መሀሪ መና ከቅጣት ምት መሬት ለመሬት ወደ ግቡ የላካትን በአዳማ ከተማ ተከላካዮች ስትመለስ ያገኛትን ኳስ ሀይደር ሸረፋ በቀጥታ ወደ ግብ መትቶ ፔንዝ ለጥቂት ያወጣበት በፈረሰኞቹ በኩል አስቆጪዎች ነበሩ ።


ቴዎድሮስ በቀለ ከርቀት አክርሮ ቢሞክረውም ማታሲ በቀላሉ የተቆጣጠረበት አስደንጋጭ ሙከራ ውጭ ሌላ አጋጣሚ ያልፈጠሩት እንግዳዎቹ። በጨዋታው መገባደጃ ባለሜዳዎቹ ጫና በመፍጠር በርካታ አጋጣሚዎችን ቢፈጥሩም ኳስ እና መረብን ሳያገናኙ ቀርተው። ጨዋታው 0-0 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቆ። ፈረሰኞቹ ከተከታዮቻቸው የሚያሰፉበትን ነጥብ ሳይጠቀሙበት ቀርተዋል።

Hatricksport website Editor

Facebook

ሚሊዮን ኃይሌ

Hatricksport website Editor