የጨዋታ ዘገባ| ሰበታ ከተማ እና ኢትዮጵያ ቡና ነጥብ ተጋርተዋል

 

ቀሪ የ14ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ መርሀ ግብር ዛሬ ፍፃሜውን ሲገኝ አዲስ አበባ ስታዲዮም ላይ ሰበታ ከተማ ኢትዮጵያ ቡናን አሰተናግዶ 0-0 በሆነ ውጤት ነጥብ ተጋርተዋል።

ኢትዮጵያ ቡናዎች ከባለፈው ሳምንት አሰላለፋቸው አንድ ቅያሬ ብቻ ያደረጉ ሲሆን አጥቂውን እንዳለ ደባልቄ በ አቡበከር ናስር ቀይረው ጨዋታውን ጀምረዋል።

ባለሜዳዎች ሰበታ ከተማ በመሆናቸው ምክንያት የአዲስ አበባ ግማሽ የመቀመጫ ክፍል የተሰጣቸው ቢሆንም ጥቂት የክፍሉን ብቻ በመሙላት ሜዳውን ጭር አድርገውት ነበር ጨዋታው የጀመረው።

በመጀመሪያ አስር ደቂቃዎች ሁለቱም ቡድኖች ቀዝቀዝ ያለ እንቅስቃሴ በማሳየት ነበር የጀመሩት። ሰበታውክች ወደውሃላ በማፈግፈግ የምከላከ ስልትን በመጀመሪያዎቹ ደቂዊች የተገበሩ ሲሆን በቡና በኩል እንደተለመደው ከግብ ጠባቂ ኳስን በመመስረት ክፍተቶችን በመፍጠር የግብ እድልን ለመፍጠር ሲሞክሩ ተስተውሏል።

በመጀመሪያው ሰላሳ ደቂቃዎች ኳስን ተቆጣጥሮ በመጫወት ላይ የነበሩት ኢትዮጵያ ቡናዎች በአቡበከር ነስሮ አማካኝነት ሁለት ለግብ የቀረቡ ኳሶችን የሞከሩ ሲሆን በተለይም በጨዋታው ድንቅ እንቅስቃሴን ሲያደርግ የነበረው አማካኙ ታፈሰ ሰለሞን ለአቡበከር አቀብሎት ከግብ ጠባቂ ጋር ፊት ለፊት በመገናኘት የግብጅን ቋሚ መታ የወጣችበት ኳስ ቡናዎችን የመሪነቱም ግብ ልታገኝላቸው የምትችል ግሩም እድል ነበረች።

በራሳቸው የሜዳ ክልል ውስጥ ተሰብስበው ሲከላከሉ የነበሩት ሰበታዎች አልፎ አልፎ በመልሶ ማጥቃት የግብ እድል ለመፍጠር ሲሞክሩ ማየት ችለናል።

 

ኢትዮጺያ ቡናዎች በጥሩ የኳስ ቅብብል በሰበታ ከተማ የሜዳ ክፍል ያገኟትን ታፈሰ ሰለሞን ኳሷን በመግፋት ወደ ፍፁም ቅጣት ምት ውስጥ ይዞት በመግብታ ብቻው ለቆመው አቡበከር ናስር ያቀበለው ሲሆን አቡበከርም ኳሷን ወደ ግብ መቀየር ቢችልም የለቱ የመስመር ዳኛ ኳሷ ከጨዋታ ውጪ ናት በማለት ግቧን ሽረዋታል። ከዳኛው ውሳኔም በውሃላ የኢትዮጵያ ቡና ተጫውቻች ተቃውሟቸውን ያሰሙ ሲሆን በሂደቱም አጥቂው አቡበከር ናስሮ የቢጫ ካርድ መመልከት ችሏል።

የመጀመሪያው አጋማሽ ላህ ዳኛው በሁለቱ ምክለቦሽ ቅሬታን ያስከተሉ ተደጋጋሚ ውሳኔዎችን ሲወስኑ ተመልክተናል። በደጋፊው ተፅእኖ ስር የነበሩት ኢትዮጵያ ቡና ተጭች በዳኛው ውሳኔ በመበሳጨት በተደጋጋሚ ዳኛው ላይ ቅሬታቸውን ሲያሰሙ ተመልክተናል።

በሁለተኛው አጋማሽ በጥሩ መነቃቃት የጀመሩት ሰበታ ከነማዎች በመጀመሪያው አስር ደቂቃዎች ሁለት ኳሶችን ወደ ግብ ቢሞክሮም ፍርልያማ ሊሆኑላቸው አልቻሉም። ኢትዮጵያው ቡናዎች ከስልሳኛው ደቂቃ በኃላ ከሰበታዎች ተደጋጋሚ ጥቃት በማገገም ኳስን በማያዝ ቶሎ ቶሎ ወደ ግብ ለመድረስ ሲሞክሩ ተስተውሏል።

 

በሁለተኛው አጋማሽ በአቤል ያለው ተቀይሮ ተገባው የኢትዮጵያ ቡናው የፊትመስመር ተጫዋች ሀብታሙ በመስመር ጥሩ የሚባሉ እንቅስቃሴዎችን በማድረግ ኳሶችን ወደ ግብ ለማሻገር ቢሞክርም የኢትዮጵያ ቡና ተጨዋቾች በተደጋጋሚ ሳይጠቀሙባቸው ሲቀሩ ታይቷል።

ጨዋታው በገፋ ቁጥር ግብ ለማስቆጠር በተደጋግሚ ጎል ላይ ለመድረስ ሲሞክሩ የነበሩት ኢትዮጵያ ቡናዎች ባለመረጋጋት እና ግብ ለማግባት በመጓጓት በጣም ለግብ የቀረቡ ኳሶችን በማይታመን መልኩ ሲያመክኑ ተስተውለዋል።

የጨዋትው አልቢትር በተደጋጋሚ ሲፈፀሙ ለነበሩ ጥፋቶች በርካታ የማስጠንቀቂያ ካርዶችን ሲሰጡ ታይተዋል። በተጨማሪም አንዳንድ ውሳኔዎች ላይ ከመስመር ዳኞቹ ጋር አለመግባባት ሲስተዋልባቸው ተመልክተናል በዚህም የሁለቱም ክለብ ተጨዋቾች እና ደጋፊዎች በተደጋጋሚ ብስጭታቸውን ሲገልፁ ተመልክተናል።

 

በሁለቱም አጋማሽ ክፍት የነበረው እና በርካታ ለግብ የቀረቡ ሙከራዎችን የተመለከትነበት ይህ ጨዋታ አንዱም ሙከራ ፍሬ ሳያፈራ ባዶ ለባዶ መጠናቀቅ ችሏል።