መነሻ ገጽ ሀዲያ ሆሳዕና የጨዋታ ዘገባ | ሰበታ አሁንም በሜዳው ሀያል መሆኑ ቀጥሎበታል
ሀዲያ ሆሳዕናሰበታ ከተማዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የጨዋታ ዘገባ | ሰበታ አሁንም በሜዳው ሀያል መሆኑ ቀጥሎበታል

አጋራ
አጋራ

የ12ኛ ሳምንት ቀሪ ጨዋታ ከነበረው አንዱ አዲስ አበባ ላይ የተደረገው የሰበታ ከተማ እና ሀድያ ሆሳዕና ጨዋታ በባለሜዳዎቹ ሰበታ ከተማዎች አሸናፊነት 2-1 ተጠናቋል።

ሰበታዎች ወደ ድሬዳዋ አቅንተው ሽንፈት ካስተናገዱበት አሰላለፋቸው የሶስት ተጫዋቾች ላይ ለውጥ በማድረግ ደሳለኝ ደባሽ፣አንተነህ ተስፋይ እና ጌቱ ኃይለማርያምን በቋሚ አሰላለፍ ይዘው ሲገቡ አዞዎቹ በበኩላቸው በተመሳሳይ ሶስት ተጫዋቾች ላይ ለውጥ አድርገው ኦቮር ኦቮኖ፣ሱራፌል ጌታቸው እና ሱራፌል ዳንኤልን ወደ ቋሚ አሰላለፍ መልሷል።

ሰበታ ከወራጅ ቀጠናው ለመራቅ ግርጌ ላይ የሚገኙት እንግዳዎቹ ደግሞ የነጥብ ልዩነቱ ከሌሎች አቻ ክለቦች እንዳይሰፋበት የሚያደርገው ተጠባቂ እንዲሆን ያደረገው ይህ ጨዋታ። በተቀዛቀዘ የደጋፊዎች ድባብ የተጀመረው ሲሆን ሰበታዎች በመጀመሪያዎች ደቂቃዎች ላይ ተጭነው ሲጫወቱ የልፋታቸውን ውጤት ማግኘት ችለዋል :: በመስመር በተገደበው የሰበታ ማጥቃት እንቅስቃሴ በስድስተኛው ደቂቃ ላይ ከመስመር የተሻገረውን ባኑ ዲያዋራ ከሳጥ ውጭ አክርሮ በመምታት የመጀመሪያውን ጎል ለማስቆጠር ችለዋል ::


ከጎሉ መቆጠር ተደጋጋሚ ሙከራዎችን ያደረጉት ሰበታዎች የበረኛውን መዘናጋት ተከትሎ ፍፁም ገብረ ማርያም ከርቀት ሞክሮ ግብ ጠባቂው አቤር ኦቮኖ ያወጣው ሙከራ ተጠቃሹ ነው :: በሀድያ ሆሳዕና በኩል በመልሶ ማጥቃት በሚገኙ አጋጣሚዎች ጫናዎችን ለመፍጠር ሲሞክር ከመስመር የተሻገረውን ካስ በነፃ አቋቋም ላይ ይገኝ የነበረው ሱራፌል በመቀስ ምት ቢሞክርም በግቡ የቀኝ አግዳሚ ታካ ለመውጣት ችላለች :: በሌላ አጋጣሚ ሀድያዎች ከመሀል ሜዳ ፀጋሰው ለአጥቂው ቢስማርክ አፖንግ አቀብሎት የሰበታውን ግብ ጠባቂ ዳንኤል አጃይ ቢያልፈውም ካስ ረዝሞበት ሳይጠቀምባት ቀርቶል :: በተደጋጋሚ የሰበታ ግብ ክልል መድረስ የቻሉት ሀድያዎች ከሳጥን ውጭ ቢስማርክ አፖንግ ያቀበለውን ኳስ ሀድያ ሆሳዕናዎችን አቻ ያደረገውን ግብ ቢስማርክ አፒያ ከመረብ ላይ አሳርፎታል ::

ሰበታዎች ካስን በመቆጣጠር ወደ ግብ መድረስ ሲፈልጉ ከጎሉ መቆጠር በሃላ ጫናዎችን ያን ያህል ሲፈጥሩ አልተስተዋለም :: ከመጀመሪያው አጋማሽ መጠናቀቅ በፊት ፍፁም ገብረ ማርያም ሳጥን ውስጥ ግልፅ አጋጣሚ አግኝቶ ሳይጠቀምበት የቀረው ሙከራ በሰበታዎች በኩል የምታስቆጭ ሙከራ አድርጎ በባለሜዳዎቹ 1-0 መሪነት ለእረፍት ወጥተዋል። በሁለተኛው አጋማሽ እንቅስቃሴ ሰበታዎች የመስመር እንቅስቃሴያቸውን በማጠናከር ሲገቡ በተደጋጋሚ በግራ መስመር በኩል በባኑ ዲያዋራ ጫናዎችን ሲፈጥሩ ተስተውላል ::

ሀድያ ሆሳዕናዎች በሁለቱ ቢሳማርኮች ላይ በተመሰረተ የማጥቃት እንቅስቃሴ ጫናዎችን ሲፈጥሩ በጨዋታው መሀል ቢስማርክ አፒያ ከመሀል ሜዳ ተሻግሮለት ሳጥን ውስጥ አክርሮ መቶ በግቡ አግዳሚ የወጣበት ሙከራ በሀድያ በኩል የሚያስቆጭ አጋጣሚ ነበር ::በተቆራረጠ የጨዋታ ሂደት የቀጠለው የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ሀድያ ሆሳዕናዎች ከመጀመሪያው አጋማሽ በተሻለ የካስ ቁጥጥር እና ሙከራዎች ተሽለው ታይተዋል :: በተሻለ ወደ ጎል ሲያጠቁ የነበሩት ሀድያዎች አፈወርቅ ሀይሉ ይዞ ወደ ሳጥን ገብቶ አክርሮ መቶት ግብ ጠባቂው ዳንኤል አጃይ ያዳነበት ሙከራ የሚጠቀስ ነበር ::

ሰበታዎች የማጥቃት እንቅስቃሴያቸውን በግራ መስመር አመዝነው በባኑ ዲያዋራ ሲያደርጉ በመጨረሻም ተሳክቶላቸው ዳግም መሪ የሆኑበትን ጎል ማስቆጠር ችለዋል :: ባኑ ዲያዋራ በግራ መስመር የግል ብቃቱን በመጠቀም ይዞት የገባውን ካስ ለፍፁም አቀብሎት ፍፁም ገብረ ማርያም ሰበታን መሪ ያደረገች ጎል ሲያስቆጥር በሊጉ ያስቆጠራቸውን የጎል ብዛት ወደ ስድስት ከፍ ማድረግ ችሏል ::


ባኑ ዲያዋራ በእለቱ ለሰበታዎች ድንቅ ብቃቱን ሲያሳይ በሁለቱም ጎሎች ላይ ቀጥተኛን ተሳትፎ ሲያደርግ የማስጠንቀቂያ ካርድም ለመመልከት ችሏል :: ጨዋታው በሰበታ አሸናፊነት ሲጠናቀቅ በደረጃው ሰንጠረዥ አምስተኛ ላይ በመቀመጥ ከመሪዎቹ ጋር ያለውን ልዩነት ወደ ስድስት ማጥበብ ሲችል ሀድያ ሆሳዕናዎች በወራጅ ቀጠናው ለመቆየት ተገደዋል::

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የ32ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች አህመድ ረሺድ (ድሬደዋ ከተማ) : በኢትዮጵያ ዋንጫ ውድድር 1 እንዲሁም...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀምራዊ ለባሾቹ እና የጣና ሞገዶቹ ጣፋጭ ሦስት ነጥብን ወደ ቋታቸው ከተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ባህርዳር ከተማ ወሳኝ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሲዳማ ቡና ሲሸነፍ በተጠባቂው ጨዋታ መቻል በጎል ፌሽታ ነገሌን ረቷል

በሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን ጨዋታ የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በሀድያ ሆሳዕና ሽንፈት ሲያስተናግድ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ውጤት ለውጧል የተባለው ዳኛ ተባረረ

በዮሴፍ ከፈለኝ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውጤት ለውጠዋል የተባሉ አርቢትሮችን ወደመጡበት መመለሱን አሁንም ቀጥሏል። ከቀናት...