የጨዋታ ዘገባ| መቐለ 70 እንደርታ በዘንድሮው ዓመት ለመጀመሪያ ግዜ በሜዳው በፋሲል ከተማ ተሸነፈ

በሰላም አባዲ

በ13ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ኘሪምየር ሊግ ትግራይ ስታድየም ላይ መቐለ 70 እንደርታ ፋሲል ከተማን አስተናግዶ 2-0 በሆነ ውጤት ተሸንፏል።

መዓም አናብስ ባለፈው ሳምንት በጅማ ሲሸነፉ ከነበረው አሰላለፋቸው ላይ አረት ተጫዋቾችን ለውጥ በማድረግ ስዩም ተስፋየ፣ ቢያድግልኝ ኤልያስ፣ ኣስናቀ ሞገስ እና ኦከኪ ኣፎላቢ ወደ ቋሚ በመመለስ መግባት ችለዋል። በአንፃሩ አፄዎቹ የአንድ ተጫዋች ላይ ለውጥ በማድረግ ኪሩቤል ሃይሉን ወደ ቋሚ አሰላለፍ መልሰዋል።

የመጀመሪያው አጋማሽ የጨዋታ እንቅስቃሴ የመቐለ 70 እንደርታ የኳስ ቁጥጥር የታየበት ቢሆንም። ያገኙት እድል በመጠቀም ረገድ የተዋጣላቸው ፋሲል ከተማዎች በ13ኛው ደቂቃ ሽመክት ጉግሳ ያቀበለውን ኳስ ተጠቅሞ ሙጂብ ቃሲም ግብ በማስቆጠር ፋሲል ከተማን መሪ ማድረግ ችሏል። ከግቧ መቆጠር በኋላም ኣጥቅተው መጫወት የቀጠሉበት ምዓም ኣናብስቶቹ ኳስና መረብ ማገናኘት ግን ኣልቻሉም። በዚህም 15ኛዉ ደቂቃ ላይ ዳኒኤል ደምሴ ያደረገው ሙከራ ለግብ የተቃረበች እንደነበረች መጥቀስ ይቻላል። 20ኛው ደቂቃ ላይ ባለሜዳዎቹ የፍፁም ቅጣት ምት ቢያገኙም አማኑኤል ገብረሚካኤል ሳይጠቀምበት የቀረው ሌላኛው ማሳያ ነበር። በኣንፃሩ ኣፄዎቹ ምንም እንኳን የኳስ ብልጫ ባይኖራቸውም ያገኙትን ኣጋጣሚ በመጠቀም ረገድ የተሻሉ ነበሩ በዚህም በመጀመሪያ አጋማሽ ማገባደጃ ሱራፊል ዳኛቸው ያሻገረለትን ኳስ ሙጂብቃሲም በሚገባ ተጠቅሞ ኳስ እና መረብን በማገናኘት በጨዋታው ለራሱና ለቡድኑ ሁለተኛ ግብ በማስቆጠር በፋሲል 2-0 መሪነት ለእሰፍት ወጥተዋል።

በሁለተኛው ኣጋማሽ ሙሉ በሙሉ መቐለ 70 እንደርታ ተጭኖ በመጫወት ውጤቱን ለመቀልበስ ተደጋጋሚ ለጎል የቀረቡ ሙከራዎች በኦከኪ አፎላቢ፣ ኣማኒኤል ገብረሚካኤል እና ተቀይሮ በገባው ኣሸናፊ ሀፍቱ በተደጋጋሚ ቢያደርጉም ግብ ጠባቂው ሚኬል ሳማኬ አክሽፎባቸዋል። በእንግዳዎቹ በኩል ያገኙትን ውጤት አስጠብቀው ለመውጣት ወደ ኋላ በማፈግፈግ ጥንቃቄ የተሞላበትን መከላከል ሲጠቀሙ ተስተውለው ስኬታማ ሆነው ወጥተዋል።

በ90ኛው ደቂቃ ግብ ባለሜዳዎቹ በአማኑኤል አማካኝነት ግብ ማስቆጠር ቢችሉም ማስቆጠር ከጨዋታ ውጪ በሚል ተሽሮባቸዋል። በጨዋታው መገባደጃ ዳኒኤል ደምሴ በሁለት ቢጫ ካርድ የቀይ ካርድ ተመልክቶ ከሜዳ ተወግዷል። ጨዋታው በፋሲል ከተማ 2-0 ኣሸናፊነት ሲጠናቀቅ ውጤቱን ተከትሎ ኣፄዎቹ በ25 ነጥብ በጊዚያዊነት ሊጉን ሲመሩ መቐለ 70እንደርታ በ22 ነጥብ 3ተኛ ደረጃ ተቀምጠዋል።

hatricksport team

Hatricksport team

Facebook

hatricksport team

Hatricksport team