የጨዋታ ዘገባ| ሀድያ ሆሳዕና አሁንም ወደ ድል መመለስ ተቸግሯል

 

በፌደሬሽኑ በተጣለበት ቅጣት ምክንያት ሁለት ጨዋታዎችን ከሜዳ ውጭ ለመጫወት የተገደዱት ሀድያ ሆሳዕና ሀዋሳ ላይ ወላይታ ድቻን አስተናግደው በጨዋታ በልጠው 1-0 ተሸንፈዋል።

ሀድያ ሆሳዕና ከባለፈው አሰላለፋቸው የሁለት ተጫዋቾች ለውጥ ሲያደርጉ። ሱራፌል ዳንኤል እና በኃይሉ ተሻገር ወደ ቋሚ አሰላለፍ መልሰው ሲገቡ።ወላይታ ድሬዳዋን ካሸነፈው ቡድናቸው ምንም ለውጥ አላደረጉም።

ከአሰልጣኝ ግርማ ታደሰ ጋር ከተለያዩ በኋላ በአዲሱ አሰልጣኛቸው ፀጋዩ ኪዳነማርያም እየተመሩ የመጀመሪያ ጨዋታቸውን ያደረጉት ሀድያ ሆሳዕናዎች በመጀመሪያዎቹ ሀያ አምስት ደቂቃዎች በተጋጣሚያቸው ብልጫ ሊወሰድባቸው ችሏል። በፈጣን አጨዋዋወት ቶሎ ቶሎ ወደ ግብ በመደረስ በኩል የተሳካላቸው ወላይታ ድቻዎች ሲሆኑ። ነብሮቹ ረብ የለሽ የኳስ ቅብብል ብቻ ቢያከናውኑም ጥቃት ከመሰንዘር ግን አልተቆጠቡም።

ፍጥነቱን ተጠቅሞ 2ኛው ደቂቃ ከመሀል ሜዳ የተላከችለትን ኳስ ተቆጣጥሮ ወደ ሳጥን እየገፋ ገብቶ ከግብጠባቂው ኦቮር ኦቮኖ ጋር አንድ ለአንድ ተገናኝተው ያዳነበት ኳስ የጦና ንቦች ከጅምሩ መሪ ሊታደርጋቸው የምትችል አጋጣሚ ስትሆን። በሀድያዎች በኩል ፒስማርክ ኦፒንግ ከሁለት ተከላካዮች ጋር ታግሎ በመንጠቅ ያቀበለውን ኳስ ከሳጥን ውጭ በሀይሉ ተሻገር አክርሮ ቢመታውም ለጥቂት የወጣችበት እና 15ኛው ደቂቃ ላይ ፒስማርክ ኦፖንግ ከግራ መስመር ወደ ሳጥኑ ያሻማትን በረከት ወልዴ በደረቴ ግጭቼ ለመክብብ ደገፉ አቀብለዋለው ሲል በማጠሯ ምክንያት አጠገቡ የነበረው ሱራፌል ደኔኤል ተቆጣጥሮ ለበሀይሉ ተሻገር አመቻችቶ ሰጥቶት በሞክረውም ግብ ጠባቂው መክብብ ደገፉ ያዳነበት ምናልባት ሀድያ ሆሳዕናዎች ሁለት ለባዶ መምራት የሚችሉበት አጋጣሚ ነበር።

የነበራቸውን ብልጫ በመጠቀም ግብ ማስቆጠር የቻሉት ወላይታ ድቻዎች። 26ኛው ደቂቃ በግራ መስመር ረሳ ባየገዛኻኝ ላይ የተሰራውን ጥፋት ተከትሎ ያገኛትን ቀጣት መት ወደ ሳጥን አሻምቶ አንጋፋው ተከላካይ ደጉ ደበበ ብስለቱን ተጠቅሞ በሚገባ በመዝለል በግንባሩ ገጭቶ ግብ አድርጎ ቡድኑን ቀዳሚ አድርጓል። ከዛ ውጭ የወላይታ ድቻው አምበል ባየ ገዛኸኝ በተደጋጋሚ ከእለቱ አርቢትር አሸብር ሰቦቃ በተደጋጋሚ አላስፈላጊ እሰጣ ገባ ውስጥ ሲገባ እንደነበር መመልከት ችለናል። ቀስ በቀስ ወደ ጨዋታ ቅኝት መግባት የጀመሩት ሀድያ ሆሳዕናዎች ከተጋጣሚ ቡድን የሚመጣባቸውን ጫና በመቀነስ ወደ በቅብብሎሽ ወደ ግብ ለመድረስ ጥረት አድርገዋል። 39ኛው ደቂቃ ሄኖክ አርፊጮ ከማእዘን ያሻማትን ኳስ ፒስማርክ ኦፖንግ በግንባሩ ገጭቶ መክብብ ደገፉ ሲመልስበት የወላይታ ድቻ ተጫዋቾች ወደ ውጭ ያወጧት በሀድያ ሆሳዕናዎች በኩል ለግብ የተቃረበች ሙከራ ነበረች። ተጨማሪ ግቦች ሳይሰተናገዱ በወላይታ ድቻ 1-0 መሪነት ለእረፍት ወጥተዋል።

በእረፍት ስአትም ጉልበቷ ላይ ባጋጠማት ጉዳት ከምትወደው እግር ኳስ የተለያየቸው የጌድዮ ዲላ ከተማዋ ተጫዋች ቤዛ ታደሰ ወደ ውጭ ወጥታ መታከም የምትችልበትን ገንዘብ በደጋፊዎች ማህበር ትብብር ተሰብስቧል።

በሁለተኛው አጋማሽ በተለየ ሀድያ ሆሳዕናዎች ፍፁም የበላይነት የነበራቸው ሲሆን ወላይታ ድቻዎች ግን በአንፃሩ የጨዋታ ብልጫ ያደርጋሉ ተብለው ሲጠበቁ የነበሩት ወላይታ ድቻዎች በተገላቢጦሽ በፍፁም መቀዛቀዝ ወደ ሜዳ ገብተዋል። በተለይ አፍወርቅ ሀይሉ ድንቅ ብቃት ታግዘው በተደጋጋሚ ወደ ተጋጣሚ ግብ ክልል መድረስ የቻሉት ነብሮቹ የሁለቱም ፒስማርክ ድክመት እንጂ በቀላሉ ሲሰበር የነበረው የወላይታ ድቻ ተከላካይ ስፍራ በማለፍ በዙ ግብ የሚሆኑ ኳሶችን አምክነዋል። ሀድያዎች ሱራፌል ዳንኤል ከርቀት አሻግሮለት ፀጋለው ዴማሞ የነፃ የማግባት እድል አግንቶ ሳይጠቀምበት ሲቀር። 57ደቂቃ ላይ አፍወርቅ ሀይሉ ከርቀት አክርሮ መትቶ ለጥቂት በአግዳሚው ስትወጣ። ከዝች ሙከራ በኋላ ፒስማርክ ኦፖንግ ሳጥኑ ጠርዝ ላይ ሆኖ የሞከራት በርካታ ግብ የሚሆኑ ኳሶችን በማዳን ወላይታ ድቻ ሲታደግ የነበረው ምክብብ ደገፉ ተቆጣጥሮበታል።

በኋድያዎች በኩል ምናልባትም የጨዋታውን ሚዛን ልትቀይር የምትችል ግብ በአስቆጪ መንገድ ወጥታባቸዋለች። 67ኛው ደቂቃ ከመሀል ሜዳው በቀኝ በኩል የተጣለችለትን ኳስ በእግሩ ዘሎ በማውረድ ወደ ሳጥኑ ይዞ ሄዶ ኳሷን ለማስጣል ከግቡ ወጥቶ የነበረው መክብብ ደገፉን ሸውዶ ደስታውን ለመግለፅ ሊሮጥ ሲል። ከየት መጣ ሳይባል ውበሸት አለማየሁ ተንሸራቶ በመውረድ ከግቡ መስመር አውጥቶበታል። ከዛ ባሻር ወላይታ ድቻዎች በአንበላቸው ባየ ገዛኸኝ አማካኝነት በተደጋጋሚ በደኛ በደል እየደረሰብን ነው በማለት ክስ አስመዝግበዋል።

በደጋፊዎች በኩል ግርግር ቢፈጠርም በደጋፊዎች ማህበር ርብርብ ቶሎ የረገበብት ሂደት በሌሎች ስታዲዮሞችም መተግበር ያለበት ጉዳይ መሆን አለበት። በሁለተኛው አጋማሽ በብቸኝነት የምትገለፀው የወላይታ ድቻ ሙከራ። ተስፋይ አለባቸው ከሳጥን ውጭ የመታውን ኦቮር ኦቮኖ በአስደናቂ ሆኔታ ተለጥጦ የያዛት ኳስ ነበረች። አፍወርቅ ሀይሉ አቀብሎት 16.50 ውስጥ አገብቶ አገባው ሲባል ወደ ውጭ የወጣችበት በሀድያዎች በኩል አስቆጪ ነበረች። ጨዋታው በወላይታ ድቻ 1-0 አሸናፊነት ተጠናቋል። ድቻ ተከታታይ ሁለተኛ ድሃቸውን ሲያስመዘግቡ ነብሮቹ ወደ ድል ለመመለስ አሁንም እየተቸገሩ ነው።

Hatricksport website Editor

Facebook

ሚሊዮን ኃይሌ

Hatricksport website Editor