የጨዋታ ዘገባ| ሀዋሳ ከተማ በብሩክ በየነ ብቸኛ ግብ ሶስት ነጥብ አሳክቷል።

 

13ኛ ሳምንት የኢትዮጲያ ፕሪምየር ሊግ ትላንት ጅማሮውን አድርጎ ዛሬም ሲቀጥል ጅማ አባጅፋርን ያስተናገደው ሀዋሳ ከተማ በብሩክ በየነ ብቸኛ ግብ 1-0 ማሸነፍ ችሏል።

ባለፈው ሳምንት ሁለቱም ቡድኖች ማለትም ሀዋሳ ከተማ ወደ መቐለ አቅንተው በሽረ 3-0 በተሸነፉበት እና ጅማዎች በሜዳቸው የሊጉን መሪ መቐለ 70እንድርታን 1-0 በረቱበት ጨዋታ በቋሚ አሰላለፍ የተጠቀሙባቸውን ተጫዋቾች ምንም ለውጥ ሳያደርጉ ወደ ሜዳ ይዘው ገብተዋል።

በመጀመሪያ 10ደቂቃዎች በሁለቱም ቡድኖች በመሀል ሜዳ የተገደበ የኳስ ቅብብል እና ይህ ነው ተብሎ ሊጠቀስ የማይቻል ቅርፅ የሌለው አጨዋወት ሲከተሉ ተስተውለዋል።ደቂቃዎች እየገፉ በመጡት ምንም እንኳን ሀዋሳዎች በተደጋጋሚ ደንኤል ደርቤ ከቀኝ መስመር በቀጥታ ወደ ሳጥኑ በሚያሻማቸው ኳሶች ተጠቅመው ወደ ግብ መድረስ ቢችልሉም የጅማ ተከላካዩች በቀላሉ ሲመልሱባቸው ነበር። 20ኛው ደቂቃ ላይ ሳጥን ውስጥ ሄኖክ አየለ ያቀበለውን ኳስ ተጠቀም ወደ ግብ ቢሞክርም ሰይድ ሀብታሙ በቀላሉ ተቆጣጠረበት እና ያኦ ከግራ መስመስ ወደ ሳጥኑ ያሻማውን ኳስ ኤልያስ አታሮ ባግባቡ ሳይገጫት ቀርቶ በቅርብ ርቀት የነበረው ዳንኤል ደርቤ ተቆጣጥሮ ለሄኖክ ድልቢ ሰቶት ቢሞክረውም ሰይድ ሀብታሙ እንደምንም ያወጣበት በሀዋሳ በኩል ለግብ የተቃረቡ መከራዎች ነበሩ። በተጨማሪም ያኦ ኦሊቨር ከግራ መስመስ ወደ ሳጥኑ ያሻማውን ኳስ ኤልያስ አታሮ ባግባቡ ባለመግጨቱ በቅርብ እርቀት የአበረ ዳንኤል ተቆጣጥሮ ለሄኖክ ድልቢ ሰቶት ቢሞክረውም ሰይድ ሀብታሙ እንደምንም ያወጣበት ባለሜዳዎቹ በግራ መስመር ያኦ ኦሊቨር ወደፊት ገፍቶ በመጫወት ሌላኛው የግብ አጋጣሚ የሚፈልጉበት መንገድ ነበር።


26ኛው ደቂቃ አብርሀም ታምራት ዘላለም ኢሳያስን በክርኑ በመማታቱ ምክንያት የጨዋታው አርቢትር አዳነ ወርቁ በሚገባ ተመልክተውት በቀጥታ ቀይ ካርድ ከሜዳ አስወግደውታል። 38ኛው ደቂቃ የመጀመሪያ ጥቃት የሰነዘሩት እንግዳዎቹ ብዙአየው እንዳሻው በግምት ከ26 ሜትር ርቀት የተገኘው ቅጣት ምት በቀጥታ ወደ ግብ መትቶ ቢሊንጌ ኢኖህ ተውርምሮ አውጥቶበታል። በመጀመሪያ አጋማሽ መጠናቀቂያ ያኦ ኦሊቨር ወደ ሳጥን የላካትን ኳስ ሄኖክ አየለ የጅማ ተከላካዩችን ስህተተ ተጠቅሞ ወደ ጎል ቢሞክርም ግብ ጠባቂው ሰይድ ያዳነበት ሀይቆች 1-0 እየመሩ ለእረፍ ሊወጡ የሚችሉበት አጋጣሚ ነበረች። ሆኖም ግብ ሳያስተናገድ 0-0 በሆነ ውጤት ለእረፍት ወደ መልበሻ ክፍል አቅንተዋል።

በሁለተኛው አጋማሽ ሀይቆች ካስን ለማንሸራሸር ተቀዳሚ ምርጫቸው አድርገው ቢገቡም በቀይ ካርድ ከሜዳ የተሰናበተባቸው እንግዳዎቹ ጎዶሏቸውን ለመሸፈን ወደ ኋላ በማፈግፈግ። በመልሶ ማጥቃት ወደ ተቃራኒ ግብ ለመድረስ ሞክረዋል። በተለይ በዚህ አጋማሽ ሀዋሳ ከተማዎች የግል ብቃቱን እየተጠቀመ ድንቅ እንቅስቃሴን ሲያደርግ የነበረው አለልኝ አዘነ ከሚያደርጋቸው ጨዋታ ውጭ ያሰቡት አጨዋወት ለመተግበር በእጅጉ ሲቸገሩ ነበር። ቢዚህም አለልኝ አዘነ አክርሮ መትቶት በአግዳሚው በኩል ለጥቂት የወጣችበት እና ከመሀል ሜዳ እየገፋ የወሰዳትን ኳስ ለሄኖክ ድልቢ አቀብሎትት እሱም ለብሩክ አየለ ሲያቀብል የጅማ ተከላካዩች ካለመናበባቸው የተነሳ ኳሷን ሳያገኟት ቀርተው በድጋሚ ኳስን ሄኖክ ድልቢ አግኝቶ ከግብ ጠባቂው ሰይድ ሀብታሙ ጋር አንድ ለአንድ ቢገናኝም ሰይድ ለጥቂት ያወጣበት ማሳያዎች ነበሩ።


ከምሀል ሜዳ በቀጥታ መሬት ለመሬት የተላከለትን ኳስ ብሩክ በየነ 75ኛው ደቂቃ በሚገባ ተቆጣጥሩ የጅማ ተከላካዮች ከጨዋታ ውጭ ነው ብለው ተዘናግተው በቆሙበት ሰአት ወደ ጎል እየገፋ ይዞ ሄዶ ግብ ጠባቂውን ሰይድ ሀብታሙን አታሎ በማለፍ ኳስ እና መረብን በማገናኘት ሀዋሳዎችን መሪ ማድረግ ችሏል። ከግቧ ምቆጠር በኋላ ዘላቂ ያልሆነ ጫና መፍጠር የቻሉት ባለሜዳዎቹ ብሩክ በየነ ወደ ግብ አክርሮ መትቶ ሰይድ ሀብታሙ ኳሷን ቢተፋትም መልሶ የተቆጣጠረው ሙክራ አድርገዋል። የጅማ አባጅፋር አሰልጣኝ ጳውሎስ ጌታቸውን ጨምሮ የአሰልጣኝ አባላት እና ተቀያሪ ወንበር ላይ የነበሩ ተጫዋቾች ዳኛው ጨዋታውን በሚገባ እመሩት አይደለም በማለት በተደጋጋሚ ቅሬታዎችን ሲያሰሙ እና በአራተኛ ዳኛ ለሚ ንጉሴ በተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ ሲደርስባቸው ነበር።

በጨዋታው መጠናቀቂያ ጅማዎች በቡዙአየሁ እንዳሻው እና ኤርሚያስ ኃይሉ አማካኝነት አቻ የሚያደርጋቸውን አጋጣሚዎች ቢያገኙም ሳይጠቀሙበት ቀርተዋል። ተጨማሪ ግቦች አለመስተናገዳቸውን ቀጥሎ ጨዋታው በሀዋሳ ከተማ 1-0 አሸናፊነት ሊጠናቀቅ ችሏል ።

 

 

Hatricksport website Editor

Facebook

ሚሊዮን ኃይሌ

Hatricksport website Editor