የጨዋታ ቅድመ ዕይታ| ፋሲል ከነማ ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ

 

የ 14ኛው ሳምንት ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ መርሀግብር ዛሬ ጅማሮውን አድርጎ ነገም ሲቀጥል በዋንጫ ፉክክር ውስጥ የሚገኙት የሁለቱም ቡድኖች ተጠባቂው ጨዋታ እንደሚከተለው አይተነዋል።

ባለፈው ሳምንት ወደ ትግራይ አቅንተው ተጋጣሚያቸውን በማሸነፍ ሙሉ ሶስት ነጥብ በማሳካት በዚህ አመት የመጀመሪያ የሜዳ ውጭ ድል ማሳካት የቻሉት የሁለቱም ቡድኖች ጨዋታ። በተከታታይ ድል ላይ የሚገኙ ቡድኖች ከመሆናቸው በተጨማሪ በዋንጫ ፉክክር ውስጥ መሆናቸው ደግሞ ጨዋታው በጉጉት እንዲጠበቅ አድርጎታል። በሱራፌል ዳኛቸው የሚመራው የመሀል ሜዳ ኳስን ተቆጣጥሮ በመጫወት ለተጋጣሚያቸው ፈተና ይሆናሉ ተብሎ የሚጠበቀው ባለሜዳዎቹ አፄዎቹ። በተለይ ከፍተኛ መነቃቃት ውስጥ የሚገኘው ሰርዳን ዚቪጂኖቭ ከሜዳቸው ውጭ እንደመጫወታቸው መጠን ጥንቃቄ ያለው አጨዋወት ይከተላሉ ተብሎ ቢጠበቀም በተለይ በአብዛኛው ግዜ ጨዋታ ላይ የሚተገብሩት ወደ ጋዲሳ መብራቴ በማጋደል እና ቀጥተኛ ብሎም በረጃጅም ኳሶች ተፎካካሪያቸውን ይፈትናሉ ተብሎ ይጠበቃል። ፈረሰኞቹ በጌታነህ ከበደ፣አቤል ያለው እና ጋዲሳ መብራቴ እየተመራ አሰፈሪ ጥምረትን በመፍጠር ለተጋጣሚ ቡድን ከባድ እየሆነ ያለው የፊት መስመራቸው። በያረድ ባየህ የሚመራው የፋሲል ከተማ ተከላካይ ስፍራ ይህን አስፈሪ ጥምረት የመመከት ትልቅ ፈተና ይጠብቀዋል። ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪው ሙጂብ ቃሲም አስቻለው ታመነን በነገው ጨዋታ የማይጠቀመው የፈረሰኞቹ ተከላካይ ስፍራ ከማስቸገሩ ባሻገር። የተከላካይ መስመር አልፎ ኳስ እና መረብን በማገናኘት የኮከብ ግብ አግቢነቱ ለማጠናከር ትልቅ ትግል ይጠብቀበታል ይጠብቀዋል። ባለሜዳዎቹ በዚህ ተጠባቂ ጨዋታ አብዱራሕማን ሙባረክ የማይኖር ሲሆን። ፈረሰኞቹ በበኩላቸው ሳልሀዲን ሰይድ፣ ለዓለም ብርሀኑ፣ አቤል ከበደ እና አስቻለው ታመነ በነገው ጨዋታ በጉዳት የማይሰለፉ ሲሆን የአምበሉ ምንተስኖት አዳነ መግባት አለመግባት አጠራጣሪ ሆኗል ።

የእርስ በእርስ ግንኙነት

ፎርፌ ጨምሮ ሁለቱ ቡድኖች ሰባች ጊዜ ሲገናኙ ፈረረኞቹ ሶስት ግዜ አፄዎቹ በበኩላቸው ሁለት ሲያሸንፉ። በቀሪው ጨዋታ አቻ ተለያይተዋል። ይህ ተጠባቂ ጨዋታ በአፄ ፋሲለደስ ስታዲዮም ነገ 9:00 በኢንተርናሽናል ዳኛ ሊዲያ ታፈሰ ዋና ዳኝነት እየተመራ ይደረጋል።

Hatricksport website Editor

Facebook

ሚሊዮን ኃይሌ

Hatricksport website Editor