መነሻ ገጽ ሪፖርት የጨዋታ ሪፖርት | በድንጉዛ ደርቢ ሁለቱን ክለቦች ያገናኝው ጨዋታ በማይማርክ እንቅስቃሴ ታግዞ በአቻ ውጤት ተጠናቋል፡፡
ሪፖርትአርባምንጭ ከተማወላይታ ድቻየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

የጨዋታ ሪፖርት | በድንጉዛ ደርቢ ሁለቱን ክለቦች ያገናኝው ጨዋታ በማይማርክ እንቅስቃሴ ታግዞ በአቻ ውጤት ተጠናቋል፡፡

አጋራ
አጋራ

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 26ሳምንት መርሀግብር በድንጉዛ ደርቢ አርባምንጭ ከተማ ከ ወላይታ ድቻ ያገናኝው ጨዋታ የተመልካችን ከልብ በማይስብ መልኩ 0-0 በሆነ የአቻ ውጤት ተጠናቋል፡፡

በኢትዮጵያ ህዝብ መዝሙር እና በአርባምንጭ ደጋፊዎች በተደረገው አቀባበል የተጀመረው የመጀመሪያው አጋማሽ በእጅ በሚቆጠሩ ሙከራወች እና መሀል ላይ በሚደረጉ ኳስን በልጦ ለመጫወት በሚደረጉ ፍትግያወች የተጠናቀቀ ነበር ለዚህም ወላይታ ድቻ ይዞት የገባው አሰላለፍ ሙሉ ለሙሉ መከላከል ላይ ያመዘነ እና ተጫዋችን ማርክ በማድረግ የአቻ ውጤት ለማግኝት ሲጥሩ ተስተውለዋል፡፡

አዞዎቹ ጎል ለማግባት ያላቸው ተነሳሽነት ወርዶ በታየበት በዚህ ጨዋታ በሚፈጥሯቸው ስህተቶች ከተመልካቹ ቅሬታንም የፈጠረ ነበር
በ25 ደቂቃ አዞዎቹ የመጀመሪያ ሙከራቸውን ያደረጉ ሲሆን ከወርቅይታደስ የተላከለትን ኳስ ብርሀኑ አዳሙ በግንባሩ ቢገጭም በአግዳሚ ብረቱ ወጣለች፡፡ ከዚህ ውጪ ምን አይነት ሙከራ ማድረግ ሳችሉ የመጀመሪያውን አጋማሽ ተጠናቋል፡፡

በጦና ንቦች በኩል በመልሶ ማጥቃት በሚላኩ ኳሶች አማካኝነት በሚገኙ ኳሶች የአዞዎቹን ተከላካዬች ስፈትሽ የነበረው ታዳጊው እዮብ አለማየሁ ለጎል የቀረቡ ሙከራወችን በ24 እና 35ደቂቃ ማድረግ ችሏል፡፡

በሁለተኛው አጋማሽ ጥሩ የኳስ እንቅስቃሴ ይደረጋል ተብሎ ቢጠበቅም ከመጀመሪያው አጋማሽ የወረደ እንቅስቃሴ ልንመለከት ችለናል

በተለይም አዞዎቹ የወላይታ ዲቻን የተከላከይ ክፍል ሰብሮ ለመግባት የተቸገረበት የወላይታ ዲቻ ታክቲካል የሆነ የመከላከል ስልት እና በተደጋጋሚ በሚሰሩ ጥፍቶች የጨዋታው እንቅስቄሴ የተጠበቀውን ያክል እንዳይሆን አድርጎታል፡፡ በነዚህ ድባቦች ውስጥ የሁለቱንም ደጋፊዎች ከመቀመጫ ያስነሳ ለጎል የቀረቡ ሙከራወች ሊፈጠሩ ችለዋል በተለይ በ72 ደቂቃ ዲቻወች በመልሶ ማጥቃት የተገኝውን አጋጣሚ በጨዋታው ጥሩ ሲንቀሳቀስ በነበረው እዮብ አለማየሁ አማካኝነት አግኝተው የበረኛውን መውጣት በመመልከት ወደ ጎል የመታውን ኳስ ተከላካዩ አንድነት አዳነ በግንባሩ ያወጣበት አጋጣሚ የጦና ንቦችን መሪ የምታደርግ ሙከራም ነበረች፡፡

በ76ደቂቃ አዞዎቹ ለጎል የቀረበ ሙከራ ያደረጉ ሲሆን ከቀኝ መስመር አማኑኤል ጎበና መረት ለመረት የመታው ኳስ አቅጣጫዋን ባትጠብቅም በቦታው የነበረው ተመስገን ኳስትሮ ከጨዋታ ውጪ ቢሆንም ወደ ግብ ሞክሮት ወደ ውጪ የወጣበት አጋጣሚ በአዞዎቹ በኩል የሚጠቀሱ አጋጣሚወች ነበሩ፡፡
በ78 ደቂቃ ከወላይታ ዲቻ በኩል ጥሩ ሲንቀሳቀስ የነበረው እዮብ አለማየሁ በአሌክስ አሙዙ ላይ በሰራው ጥፍት 2 ቢጫ ካርድ ከሜዳ መውጣት ችሏል፡፡ከዚህም ክስተት በሃላ ዲቻወች የመከላከል ሀይላቸውን በመጨመር አጥቂውን ጃኮ አራፍትን በአቡዱልሰመድ አሊ በመቀየርግብ እንዳይቆጠርባቸው ለማድረግ ተጫውተዋል፡፡

በዚህም መሰረት ምንም አይነት የጎል ሙከራ ሳይደረግበት ጨዋታው 0-0 የአቻ ውጤት መጠናቀቁን ተከትሎ አዞዎቹ ተመልሰው ወደ ወራጅ ቀጠናው ሊገቡ ችለዋል፡፡

የአሰልጣኞች አስተያየት

የአርባ ምንጭ ከተማ ግዚያዊ አሠልጣኝ ጃክሰን ፊጣ

” ለማሸነፍ ተዘጋጅተን ነበር ነገር ግን ተቃራኒ ቡድን ተከላክሎ በመጫወቱ ያሰብነው አልተሳካም “

አሠልጣኝ ዘነበ ፍሰሃ -ወላይታ ድቻ

” በውጤት ቀውስ ዉስጥ በመሆናችን በጥንቃቄ ተጫውተናል ማሸነፍ ካልቻልን ደግሞ ውጤት ለማስጠበቅ መከላከልና መልሶ ማጥቃትን መርጠናል”

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የ32ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች አህመድ ረሺድ (ድሬደዋ ከተማ) : በኢትዮጵያ ዋንጫ ውድድር 1 እንዲሁም...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀምራዊ ለባሾቹ እና የጣና ሞገዶቹ ጣፋጭ ሦስት ነጥብን ወደ ቋታቸው ከተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ባህርዳር ከተማ ወሳኝ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሲዳማ ቡና ሲሸነፍ በተጠባቂው ጨዋታ መቻል በጎል ፌሽታ ነገሌን ረቷል

በሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን ጨዋታ የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በሀድያ ሆሳዕና ሽንፈት ሲያስተናግድ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ውጤት ለውጧል የተባለው ዳኛ ተባረረ

በዮሴፍ ከፈለኝ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውጤት ለውጠዋል የተባሉ አርቢትሮችን ወደመጡበት መመለሱን አሁንም ቀጥሏል። ከቀናት...