በኢንተርናሽናል ዳኛ ባምላክ ተሰማ አማካኝነት የተካሄደው የሁለቱ ጨዋታ በመጀመሪያው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ብዙም ለጎል የቀረቡ ሙከራዎች ያልተደረጉበት መሀል ላይ ብቻ በሚንሸራሸሩ ኳሶች የተገታ ጨዋታ ለመመልከት ችለናል፡፡ ለዚህም ማሳያ እንግዳው ክለብ ወልድያ ከተማ የአሰላለፍ ስልት ሲሆን 5-4-1 አሰላለፍ ይዞ ወደ ሜዳ በመግባት ወሳኝ 1ነጥብ ይዞ ለመውጣት ሲጥሩ ተስተውለዋል፡፡
በተቃራኒ ባለሜዳው አርባምንጭ ከተማ በሜዳው እደመሆኑ መጠን የማጥቃት ሀይሉን በመጨመር በ 4-3-3 አሰላለፍ ወደ ሜዳ ገብተዋል፡፡
ብዙም በማይማርከው የመጀመሪያ አጋማሽ አርባምንጭ ከተማ በተሻለ መልኩ ወደ ጎል መድረስ ሲችሉ የመጀመሪያ ሙከራቸውን በፀጋዬ አበራ አማካኝነት ማድረግ ችለዋል፡፡
ወልድያ ከተማዎች ከቢያድግልኝ ኤልያስ በረጅሙ በሚጣሉ ኳሶች በመልሶ ማጥቃት ወደ ተቃራኒ ቡድን ክልል ለሜሄድ የሚያደርጉት ጥረት በአርባምንጭ የመሀል ክፍል ተጫዋቾች በታዳጊው አለልኝ አዘነ እና በአንበሉ አማኑኤል ጎበና አማካኝነት ሊከሽፉ ችለዋል፡፡
በዚህም መሰረት የመጀመሪያ አጋማሽ ብዙም በማይማርክ እንቅስቃሴ ቢጠናቀቅም ነገርግን አርባምንጭ ከተማ ጨዋታውን የቀየረች ወሳኝ ጎል ማግኝት ችለዋል በ39 ደቂቃ ላይ ቢድግልኝ ኤልያስ በእጁ መንካቱን ተከትሎ የተሰጠውን ቅጣት ምት ወጣቱ ተስፈኛ ታዳጊው አለልኝ አዘነ በግሩም ሁነቴ ከመረብ በማሳረፍ አዞዎቹን ቀዳሚ ማድረግ ሲችል በአመቱ የአጋባቸውን ጎሎች ወደ 3ከፍ ማድረግም ችሏል፡፡

በሁለተኛው አጋማሽ የባለሜዳዎቹ አርባምንጭ ከተማ የበላይነት የታየበት እንዲሁም የወልድያ ከተማ ደካማነት የተንፀባረቀበት ጨዋታ ማየት ችለናል፡፡
ወልድያ ከተማዎች 1ግብ ማስተናገዳቸውን ተከትሎ የአሰላለፍ ለውጥ በማድረግ በ 4-5-1 አሰላለፍ ወደ ሜዳ የገቡ ቢሆንም ምንም አይነት የአጨዋወት ለውጥ ማድረግ ሳይችሉ ቀርተዋል ይባስ ብሎ የተከላካይ ክፍላቸው በመሳሳቱ በተደጋጋሚ የግብ ክልላቸው ሊደፈር ችሏል፡፡
ለዚህም ማሳያ ገና በተጀመረ 48ኛው ደቂቃ ከአለልኝ አዘነ የተሻገረለትን ኳስ ተመሰገን ካስትሮ ከበረኛው ጋር ተገናኝቶ ያበከናት ኳስ የሚጠቀስ ነው፡፡
ከዚችም ሙከራ በሃላ የተነቃቁት አዞዎቹ በ52 ደቂቃ ከእንዳለ ከበደ የተላከችውን ኳስ በጥሩ አቋም ላይ የነበረው ተመስገን ካስትሮ በሚያስደንቅ አጨራረስ ወደ ግብነት በመቀየር አዞዎቹን ወደ 2-0 መሪነት ከፍ እንዲሉ ማድረግ ሲችል ያገባት ጎል ለተጫዋቾቹ የእራስ መተማመን ችሎታውን ከፍ ማድረግ ችላለች፡፡
ከግቧ መቆጠር በሃላ እንግዳዎቹ ወልድያዎች ወደ ፊት ለመሄድ ሲጥሩ ቢስተዋልም የቆዩት ግን ለ 5 ደቂቃዎች ብቻ ነበር ሆኖም ለአንዱአለም ንጉሴ በሰማይ ላይ የሚላኩ ኳሶች በቀላሉ በአርባምንጭ ከተማ ተጫዋቾች እና ግብ ጠባቂው ሊያዝ ችሏል፡፡
ከአለልኝ አዘነ በሚነሱ ኢላማቸውን ጠብቀው በሚላኩ ረጃጅም ኳሶች በጥሩ መደራጀት ወደ ፊት መጫወት የጀመሩት አዞዎቹ የሳሳውን የወልድያ የተከላካይ ክፍል በተደጋጋሚ ሲረብሹ ቆይተው ተጨማሪ 3ኛ ጎል በተመስገን ካስትሮ አማካኝነት ማግኝት ችለዋል፡፡
73ኛው ደቂቃ ከቀኝ መስመር በኩል ወርቅይታደስ አበባ ያሻማውን ኳስ አጥቂው ብርሀኑ አዳሙ ወደ ግብ ቢሞክርም አግዳሚ ብረቱን በመግጨት ተመልሳ ብትወጣም በአቅራቢያው የነበረው ተመስገን ካስትሮ አግብቶ ቡድኑን ወደ 3-0 መሪነት ከፍ ማድረግ ችሏል፡፡
ግቧ ከተቆጠረች ከጥቂት ደቂቃዎች በሃላ በ78 ደቂቃ ከግራ ጠርዝ እንዳለ ያሻማውን ኳስ የጨዋታው ኮከብ የሆነው ተመስገን ካስትሮ በጥሩ ሁኔታ ወደ ግብነት ቀይሮ ለራሱ 3ጎሎችን በማግባት ሀትሪክ ሲሰራ ቡድኑን 4-0 እንዲመራ አሰችሎታል፡፡
ብርሀኑ አዳሙን በመቀየር ወደ ሜዳ የገባው በረከት አዲሱ በ82 ደቂቃ 5ኛዋን እና የመጨረሻዋን ጎል በማስቆጠር በሜዳው የነበረውን ደጋፊ በደስታ እንዲጨፍር ማድረግ ሲችል፡፡ በተቃራኒው ወልድያ ከተማን ለመደገፍ ወደ ሜዳ የገቡትን በአርባምንጭ የሚማሩ የወልዲያ ደጋፊዎችን ሜዳውን ለቀው እንዲወጡ ማድረግ ችሏል።

እንግዳቹ ወልድያዎች የወረደ አጨዋወት ባሳዩበት በዚህ ጨዋታ ለጎል የቀረበ 1ሙከራ ሳያደርጉ ጨዋታው በባለሜዳው በአርባምንጭ ከተማ 5-0 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡
የአሰልጣኞች አስተያየት
የአርባምንጭ ከተማ ግዝያዊ አሠልጣኝ ጃክሰን ፊጣ
” ካለንበት ደረጃ አንፃር ወሳኙን ጨዋታ በድል መወጣታችን ለክለቡ ደጋፊዎች ደስታን ያጎናጸፈ ነበር።
የድሉ ምስጢር የተጫዋቾች ተነሳሽነትና ፍላጎት እንዲሁም በተደረገው ተጫዋቾችን የማሸጋሸግ ሥራ በጥንቃቄ መሥራታቸው ለድል አብቅቶናል ፡፡በዚሁ ተነሳሽነት ቀጣይ ሳምንት ከደደቢት ጋር አዲስ አበባ ላይ የሚኖረንን ጨዋታ በድል ለመወጣትም ጠንክረን እንሠራለን። ”
አሠልጣኝ ዘላለም ሽፈራዉ ~ ወልዲያ
“አርባ ምንጮች ድሉ ይገባቸዋል፡፡በቀጣይ የክለቡን መሠረታዊ ችግሮች በማስተካከል ድሎችን አስመዝግበን ክለቡ በሊጉ እንዲቆይ ጠንክረን እንሰራለን። ”
አስተያየት ይስጡ