የጦና ንቦቹ የወሳኝ ተጫዋቻቸውን ውል አራዘሙ !
የወላይታ ድቻን የፊት መስመር እየመራ የሚገኘው ባዬ ገዛኸኝ ለተጨማሪ ዓመታት በጦና ንቦቹ ቤት ለመቆየት መስማማቱ ተገለፀ ።
ወላይታ ድቻዎች ከደቂቃዎች በፊት በሊጉ የፊት መስመር አጥቂ ቦታ ላይ ብቃቱን ያስመሰከረውን ባዬ ገዛኸኝ በክለቡ ማቆየት ችለዋል ።
ባዬ ገዛኸኝ ያለፈፉትን ቀናት ስሙ ከተለያዩ የሊጉ ክለቦች ጋር ሲነሳ መቆየቱ ይታወቃል ።
ባዬ ገዛኸኝ ከዚህ ቀደም ከሚዛን ቴፒ አንስቶ በስልጤ ወራቤ ፣ መከላከያ ፣ ሲዳማ ቡና በመጫወት አሳልፏል ።