የጅማ አባ ጅፋር የመጀመሪያው ዙር ጉዞ ሲዳሰስ

 

የሊጉ መጠናቀቅ ተከትሎ የተለያዩ ክለቦች የመጀመሪያው ዙር ጉዞ ምን ይመስላል የሚለውን የገር እያነሳን ቆይተናል በዛሬው ፅሁፋችን ደግሞ የጅማ አባጅፋር የመጀመሪያውን ዙር ጉዞ ምን ይመስል ነበር የሚለውን አይተናል።

በአሰልጣኝ ጳውሎስ ጌታቸው እየመሩ በ18 ነጥብ 13ኛ ደረጃ ይዘው የመጀመሪያውን ዙር ያጠናቀቁት ጅማ አባጅፋሮች በተደጋጋሚ ከፋይናንስ ችግር ጋር አየታገሉ የመጨረሻውን ዙር አጠናቀዋል። ከነበራቸው ችግር አንፃር የያዙት ነጥብ ከሌሎቹ ጋር ሲነፃፀር ጥሩ የሚባልላቸው አባጅፋሮች። በተደጋጋሚ ማጥቃት ላይ የተመረኮዘ ፈጣን ኳሶችን ከኤሊያስ አህመድ እና ንጋቱ ገብረስላሴ በሚነሱ በሚልኳቸው ኳሶች ወደ ፊት አጥቂዎቻቸው በማድረስ የግብ አጋጣሚ ለመፍጠር በመጀመሪያው ዙር ሲከተሉት የነበረው የጨዋታ ስልት ነው። ተጫዋቾች ደሞዝ አለመከፈሉን ተከትሎ በተደጋጋሚ ልምምድ እያቆሙ በወጥነት ለመዝለቅ ቢቸጉሩም በተለይ ከቅርብ ጨዋታዎች ወዲህ ግን ለተጋጣሚ ፈታኝ መሆን ችለዋል።

ጅማ አባጅፋሮች ካደረጓቸው 15 ጨዋታዎች 4 አሸንፎ በ5 ሲሸነፉ በቀሪዎቹ 6 ጨዋታዎች ነጥብ ተጋርተዋል። በቅጣት አዳማ ላይ ያደረጋቸውን 2 ጨዋታዎችን ጨምሮ በሜዳቸው ካደረጓቸው 8 ጨዋታዎች አራቱን በድል ሲወጣ በሁለት ተሸንፎ በቀሪው ሁለት ደግሞ ነጥብ ተጋርቷል። ይህም ማለት ጅማ አባጅፋሮች በመጀመሪያው ዙር ያስመዘገቧቸውን የአራት ጨዋታዎች ድል በሜዳቸው ብቻ ነው። በሜዳቸው ባደረጉት ጨዋታ በተጋጣሚ መረብ ላይ ዘጠኝ ግቦችን ማሳረፍ ሲችሉ በተቃራኒው ስድስት ግቦች ተቆጥረውባቸዋል። ጅማዎች በሜዳቸው የሚያደርጉት ጨዋታ ላይ ግብ ያስቆጥራሉ ግብም ይቆጠርባቸዋል። በሜዳቸው በሚያደርጉት እያንዳንዱ ጨዋታ ላይ 1.2 ግቦችን ሲያመርቱ 0.7 በአንፃሩ በአማካይ ይቆጠርባቸዋል።

ጅማ አባጅፋሮች ከሜዳቸው ውጭ ባደረጓቸው 7 ጨዋታዎች በሶስቱ ተሸንፎ በአምስቱ አቻ ተለያይቷል። ይህ የሚያሳየው ደግሞ ከሜዳው ውጭ ማሸነፍ እንኳን ባይችል ነጥብ ተጋርቶ የመውጣት ከፍተኛ አቅም አለው። ከሜዳው ውጭ ባደረገው ጨዋታ አንድ ግብ ሲያስቆጥር አንድ ግብ ተቆጥሮበታል። የኋላውን ዘግቶ በጥብቅ መከላከል የመልሶ ማጥቃት አጨዋወት ወደ ተጋጣሚ የግብ ክልል ቢደርስም የፊት መስመራቸው ከሜዳው ውጭ ግብ ለማስቆጠር ያዳግተዋል። ጅማ አባጅፋሮች በአጣቀላይ በመጀመሪያው ዙር በአጠቃላይ በተጋጣሚቻቸው ላይ 10 ግቦችን አግብተው 12 ገብቶባቸዋል። በየጨዋታው 0.6 ግቦችን ሲያገቡ በአንፃሩ 0.8 ይቆጠርባቸዋል። ይህ ደግሞ ግብ የማያገባ እና ግብ የማይገባበት ጅማ አባጅፋር ብለን እንድናነሳ ያደርገናል። በመጀመሪያው ዙር በሰበታ 3-1 ሲሸነፉ ከፍተኛ ግብ የተቆጠረባቸው ብቸኛው ጨዋታ ሲሆን። የሊጉን መሪ ቅዱስ ጊዮርጊስን ያሸነፉበት ደግሞ ለጅማዎች በመጀመሪያው ዙር ያሳኩት ጣፋጭ ድል ነው። በአምስት ጨዋታዎች ግብ ሳይቆጠሮባቸውም ሳያስቆጥሩም ወጥተዋል። ኤርሚያስ ኃይሉ እና ብዙአየሁ እንዳሻው ሁለት ሁለት ግቦችን በማስቆጠር የመጀመሪያው ዙር የቡድኑ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪዎች ናቸው።

ጅማ አባጅፋሮች ባለፈው አመት የመጀመሪያው ዙር በ21 ነጥቦች 9 ደረጃን ነበር ይዞ ያጠናቀቀው። ዘንድሮ ከአምናው በሶስት ነጥቦች ዝቅ ብሎ 18 መሰብሰብ ችሏል።

የቡድኑ ጠንካራ እና ደካማ ጎን

ቡድኑ ፍንክች የማይል የኋላ መስመራቸው እንደ ጠንካራ ጎኑ ሲነሳ። የአጥቂ መስመራቸው በአንፃሩ ግቦች ቢያገባም እንደሚፈለገው እያስቆጠረ ነው ማለት አያስደፍርም።

በሁለተኛው ዙር የሚጠበቅባቸው

ምንም እንኳን ከአጨዋወት ጋር የሚያያዝ አይሁን እንጂ የፋይናንስ ችግር በክለቡ ውጤት ላይ ከፍተኛ ጠባሳን እያሳረፈ ይገኛል። ይህ ችግር ተቀርፎ በተለይ በመጨረሻዎቹ ጨዋታዎች ላይ ያሳየው የቡድኑ አጨዋወት በጓደሎ እንኳን ለተጋጣሚ በቀላሉ እጁን አለመስጠቱን የሚያስቀጥል ከሆነ። በተጨማሪም የአጥቂ መስመራቸውን በሁለተኛው አስተካክለው የሚመጡ ከሆነ ጠንካራ ተፎካካሪ ሆነው መቅረብ የሚያስችላቸው አቅም እንዳላቸው ማየት ችለናል።

Hatricksport website Editor

Facebook

ሚሊዮን ኃይሌ

Hatricksport website Editor