የጅማ አባጅፋር የፕሪሚየር ሊግ ፀሃይ እየጠለቀ ይሆን?

 

👉 የመክፈያው ቀን ይራዘምልን ብለው ቢጠይቁም
ተቀባይነት አጥተዋል….

 

ጅማ አባጅፋሮች ክፈሉ የተባሉት የመመዝገቢያ 870 ሺህ ብር የመክፈያ ቀነገደቡ በ15 ቀን እንዲራዘም ያቀረቡት ጥያቄ ውድቅ ተደርጓል፡፡ በአዲሱ የሊግ ኮሚቴ ከታገዱት 7 ክለቦች 6ቱ የተጠየቀውን ከፍለው ለሁለተኛው ዙር ዝግጁ ሲሆኑ ጅማ አባጅፋሮች ግን ቀኑ እንዲራዘም ጠይቀዋል፡፡ ሊግ ኮሚቴም በሰጠው ምላሽ ምንም የሚራዘም ቀን እንደሌለ ገንዘቡም ካልተከፈለ የእሁዱ ጨዋታ በፎርፌ እንዲቀጡ እንደሚደረጉ በመግለፅ ጥያቄውን ውድቅ አድርጓል፡፡ ጅማዎች ለመክፈል 15 ቀን ድረስ ከጠበቁ ከባህርዳር ከተማና አርብ ከኢትዮጲያ ቡና ጋር የሚደረገው ጨዋታ በፎርፌ ሊቀጡ ይችላሉ ተብሎ ተሰግቷል፡፡ ይሄ ደግሞ በፌዴሬሽኑ ደንብ መሠረት ወደ ከፍተኛ ሊግ እንዲወርዱ ሊያስገድዳቸው ይችላል ተብሏል፡፡ አሁንም የባከነ ሰአት አለ….

Editor at Hatricksport

Facebook

ዮሴፍ ከፈለኝ

Editor at Hatricksport