መነሻ ገጽ ዜናዎች የጅማ አባጅፋር እግር ኳስ ክለብ ለደጋፊዎቹ በቂ መረጃ ለመስጠት እንዲሁም ድጋፍ ማድረግ የሚያስችል አጭር የፅሁፍ መላኪያ መስመር ይፋ አደረገ።
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግጅማ አባጅፋር

የጅማ አባጅፋር እግር ኳስ ክለብ ለደጋፊዎቹ በቂ መረጃ ለመስጠት እንዲሁም ድጋፍ ማድረግ የሚያስችል አጭር የፅሁፍ መላኪያ መስመር ይፋ አደረገ።

አጋራ
አጋራ

የጅማ አባጅፋር እግር ኳስ ክለብ ለደጋፊዎቹ በቂ መረጃ ለመስጠት እንዲሁም ድጋፍ ማድረግ የሚያስችል አጭር የፅሁፍ መላኪያ መስመር ይፋ አደረገ።
የክለቡ ስራ አስኪያጅ አቶ እስከዳር ዳምጤ በሰጡት መግለጫ ክለቡ ለደጋፊዎቹ በቂ መረጃ ለመስጠት እንዲሁም ድጋፍ እንዲያደርጉለት አዲስ አሰራር ዘርግቷል።

በመሆኑም ደጋፊዎች ለክለቡ አባልነት ለመመዝገብ በነፃ 6732 help ብለው በሞባይላቸው አጭር የፅሁፍ መልክት እንዲልኩ በማድረግ መመዝገብ ይችላሉ።

ይህን ካደረጉ በኋላ በሳምንት አንድ ብር ብቻ እየተቆረጠባቸው አጠቃላይ ክለቡን በተመለከተ ያሉ የዝውውር መረጃዎች ፣ የክለቡን ደረጃና የጨዋታ ውጤት መረጃዎችን የሚያገኙ ይሆናል።

በዚሁ አሰራር ደጋፊዎች በወር፣ በግማሽ ዓመትና በዓመት ጥሩ የሚሉቱን የክለቡን ተጫዋችም መምረጥ የሚችሉም ይሆናል ።

መተግቢያውን የሰሩት የናናሰርቪስስ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ስራ አስኪያጅ አቶ አብርሃም ደጉ በበኩላቸው አሰራሩ በክለቡና በደጋፊዎች መካከል ፈጣንና የተቀላጠፈ ግንኙነት ይፈጥራል ብለዋል።

አሰራሩ የደጋፊዎችን የአባልነት ምዝገባና ክለቡ በተመለከተ መረጃ ከመስጠት ባለፈ ሌሎች አገልግሎቶች እንደሚኖሩትም ጠቁመዋል።

ከነዚህም መካከል ደጋፊዎች የክለባቸውን ማልያ ለመግዛት እንዲሁም የክለቡን ጨዋታ ለመታደም የትኬት ግዥ የሚፈፅሙበት ለማድረግ ታስቧል ብለዋል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

ገዛኸኝ ደሳለኝ (ሸገር ከተማ) : ክለቡ ከ ኢትዮጵያ ቡና ጋር ባደረገው የ26ኛ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በዝናባማው ጨዋታ በመቻል ሲረታ የጣናው ሞገድም አሸንፏል

እጅግ በከባድ ዝናብ ታጅቦ በተደረገው ጨዋታ መቻል የሊጉን መሪ ሲዳማ ቡናን 3ለ1...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀድያ ሆሳዕና ፣ ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ ወሳኝ ድል አግኝተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን መርሀግብር ሀዋሳ ከተማ ወደ ሊጉ መሪ የሚጠጋበትን ዕድል...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ፈረሰኞቹ በድል ሲቀጥሉ ንግድ ባንክ እና ድሬዳዋም አሸንፈዋል

ቅዱስ ጊዮርጊስ ተከታታይ ድሉን ወደ ቋቱ ሲከት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከጨዋታ ብልጫ...