የጀርመኑ ባየርሙኒክ እግር ኳስ ክለብ የተለያዩ ሥልጠናዎችን ለመስጠት ባለሙያዎችን ወደ አዲስ አበባ ሊልክ ነው፡፡

ባየርሙኒክ እግር ኳስ ክለብ ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጋር ቀደም ሲል የልምድ ልውውጥ፣ ተከታታይ የወጣት አሰልጣኞች ስልጠናት እና ቀጣይነት ያላቸውን ሥራዎች ለመስራት ባደረገው ስምምነት መሠረት የካቲት 8 ቀን 2012 ዓ.ም ባለሙያዎችን ወደ አዲስ አበባ በመላክ የ15 ቀናት ቆይታ በማድረግ የተለያዩ ሥራዎችን የሚሰራ ይሆናል፡፡
የባየርሙኒክ እግር ኳስ ክለብ ቀደም ሲል ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጋር በመተባበር በርካታ ስልጠናዎች እና የልምምድ ልውውጦችን የአደረገ ሲሆን በቀጣይ ቆይታው የተለያዩ ሥራዎችን ለመስራት ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የቴክኒክና ልማት ዳይሬክቴሬት ጋር ቅድመ ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡
በመጀመሪያው ኘሮግራም ቀደም ሲል በሁለት ዙር ከየክልሉ ለተውጣጡ የጀማሪ ወጣት አሰልጣኞች በተሰጠው ስልጠና ተገቢውን ውጤት ላሟሉ እና ወደ ቀጣይ ዙር ላለፋ 30 ወጣት አሰልጣኞች ለተከታታይ 5 ቀናት ከሰኞ የካቲት 9 እስከ የካቲት 13 ቀን 2012 ዓ.ም የቀጣይ ዙር ስልጠና ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ ስታዲየም የሚሰጥ ይሆናል፡፡
በተከታይነትም ለኢትዮጵያ ኘሪሚየር ሊግ የወንዶች ክለቦች እና ለ1ኛ ዲቪዚዮን የሴቶች ኘሪሚየር ሊግ ክለቦች አሠልጣኞች የሙያ ማሻሻያ ሥልጠና ከየካቲት 16 እስከ የካቲት 18 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ ለሦስት ተከታታይ ቀናት የሚሰጥ ሲሆን በየካቲት 19 እና 20 /2012 ዓ.ም ኘሮግራሙ በባየር ወጣቶች ዋንጫ ላይ ተሳታፊ የሚሆኑ ከ15 ዓመት በታች ታዳጊዎችን በመመልመል እና 10 ተጫዋቾችን በመለየት በሚያዚያ መጨረሻ በጀርመን ሙኒክ ከተማ ላይ ለሚካሄደው የባየር የታዳጊዎች ዋንጫ ውድድር ላይ ተሳታፊ የሚሆኑበት እድል የሚፈጠር ሥራዎችን የሚሰራ ይሆናል፡፡

Via – EFF

Hatricksport website Editor

Facebook

ሚሊዮን ኃይሌ

Hatricksport website Editor