የድሬዳዋ ከተማ ስፖርት ክለብ ተጫዋቾች የኮሮና ቫይረስ ለመከላከል የከተማ አስተዳደሩ ያቀረበውን ጥሪ ተከትሎ የአንድ ወር ደሞዛቸውን ለገሱ

 

ክለቡ ዛሬ በምድር ባቡር ስፖርት ክለብ ርቀቱን ጠብቆ ባካሔደው ውይይት ተጫዋቾች የአንድ ወር ደሞዝ ለመለገስ የተስማሙ ሲሆን የብር መጠኑም ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ እንደሆነ ታውቋል።
ክለቡ ከብሩ ድጋፍ ባሻገርም የተለያዩ ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራ ለመስራት ተስማምቷል።
ክለቡ ላደረገው ድጋፍ የአስተዳደሩ ም/ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጁሓር በቦታው በመገኘት ምስጋና አቅርቧል።
ክለቡ ህብረተሰቡን ማስተማሩ ላይ ትኩረቱን እንዲያደርግ የክለቡ ፕሬዝዳንት አቶ አብዱሰላም መሐመድ አቅጣጫ ያስቀመጠ ሲሆን ለበጎ ስራዎች አስፈላጊው ግብዓቶች ከባለሓብቶች ጋር ሆኖ እንደሚያቀርቡ የገንዘብ እና ኢኮኖሚ ቢሮ ኀላፊ አቶ ሱልጣን አሊዪ ቃል ገብቷል።
የደጋፊ ማህበሮችም የተለያዩ ግንዛቤ የማስጨበጥ የሚሰሩ ይሆናል።

hatricksport team

Hatricksport team

Facebook

hatricksport team

Hatricksport team