ፋሲል ከተማ ኬኒያያዊውን የመሃል ተከላካይ ሰንደይ ሙቱኩን በ1 አመት ኮንትራት ውል አስፈርሟል፡፡
ሰንደይ ምትኩ በመሃል ተከላካይና አማካኝ ስፍራ የሚጫዎት ሁለገብ ተጨዋች ሲሆን በትውልድ ሀገሩ ኬኒያ በ3ኛ ዲቪዚዬን የሚሳተፈውን ያታ ኮምቦይን እግር ኳስ ክለብ በ2015 እ,ኤ,አ የተቀላቀለ ሲሆን በቆይታው የተጨዋቹን የኳስ ክህሎትና ብስለት የተመለከቱት በ2ኛ ዲቪዚዬን የሚሳተፉት ካካሜጋ ሆምቦይዝ ክለብ በአመቱ መጨረሻ ወደ ክለባቸው አዛወሩት፡፡
ተጨዋቾቹ በ2ኛ ዲቪዚዬን በሚሳተፈው ካካሜጋ ሆምቦይን እግር ኳስ ክለብ በነበረው ቆይታ የክለቡ አምበል ሆኖ የተጫወተ ሲሆን ባሳለፍነው አመት ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ለሲዳማ ቡና በመፈረም ከክለቡ ጋር ጥሩ ጊዜ ማሳለፉ የሚታወስ ቢሆንም በአመቱ መጨረሻ ባሳለፍነው የክረምቱ የተጨዋቾች የዝውውር መስኮት ሲዳማ ቡናን ለቆ ድሬድዋ ከተማን መቀላቀሉ የሚታወስ ነው፡፡
ሰንደይ ሙቱኩ ከድሬዳዋ ከተማ ጋር በነበረው የ6 ወር ቆይታ የተጠበቀውን ያህል እንቅስቃሴ ሳያደርግ ትናንት በስምምነት ከክለቡ ጋር የነበረውን ኮንትራት ውል በማፍረስ ዛሬ ለፋሲል ከተማ በ1አመት ኮንትራት ውል ፈርሟል፡፡
የፋሲል ከተማ የክለቡ አመራሮች የአጥቂ ክፍሉን ለማጠናከር በዝውውሩ ላይ ተጠናክረው እየተሳተፉ መሆኑ ታውቋል፡፡
አስተያየት ይስጡ