የዋልያዋቹ ኮከብ ወደ ሜዳ ተመልሷል !

 

ያለፉትን 254 ቀናት ባጋጠመው ጉዳት ከሜዳ ርቆ የቆየው ዑመድ ኡክሪ በትላንትናው ዕለት ወደ ሜዳ በመመለስ ጨዋታውን ከረጅም ጊዜ በኋላ አካሂዷል ።

ኡመድ በትላንትናው ዕለት አስዋን ከሜዳው ውጪ ከ ኤል ጌይሽ ጋር ያለ ምንም ግብ አቻ በተለያዩበት ጨዋታ ላይ ተቀይሮ በመግባት ጨዋታውን ከረጅም ጊዜ ጉዳት በኋላ ማድረግ ችሏል ።

ዑመድ ኡኩሪ በዚሁ ጉዳት የብሔራዊ ቡድን ጨዋታዎች ሲያመልጡት ከጉዳት መመለሱን ተከትሎ በሚያሳየው ወቅታዊ ብቃት ወደ ብሔራዊ ቡድን ዳግም ለመቀላቀል ብርቱ ፉክክር እንደሚጠብቀው ይጠበቃል ።

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor