የዋሊያዎቹ አለቃ ወቅታዊ መግለጫ !

በአሁን ሰዓት ለጋዜጠኞች የጋዜጣዊ መግለጫ እየሰጡ የሚገኙት አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ምላሾችን እየሰጡ ይገኛሉ ።

” ተጨዋቾቹ ዳሌ አውጥተዋል የሚለውን ሰምቻለው ነገር ግን ዳሌ ያወጣ ተጨዋች አልገጠመኝም ” ሲሉ ለተነሳላቸው ጥያቄ ምላሽ ሰጥተዋል ።

• አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ብሄራዊ ቡድኑ በጥሩ ሁኔታ እየተዘጋጀ መሆኑን ገልጿል፡፡

• ሐሙስ እና እሁድ ከዛምቢያ ብሄራዊ ቡድን ጋር ከሚደረገው የወዳጅነት ጨዋታ በኋላ ያሉትን የተጨዋቾች ቁጥር ቀንሰን ለኒጀሩ ጨዋታ የምንዘጋጅ ይሆናል ሲልም አስረድቷል ፡፡

• የተጨዋቾቹ አቋም እንደፈራነው አልነበረም ያ ማለት ሁሉም የጠራናቸው 38 ተጨዋቾች ለጨዋታ ዝግጁ ናቸው ማለት አይቻልም ።

• ከታፈሰ ሰለሞን ጋር ተያይዞ የተፈጠረውን ችግር መርምረን የእርምት እርምጃ ወስደናል ፣ ልጆቹ ወጣት እንደመሆናቸው ስህተት ሰርተዋል አርመናቸዋል ።

• ትልቅ የገጠመኝ ፈተና የሚዲያን ጥያቄ በሚፈለገው መጠን መመልስ አለመቻሌ ነው ፣ በቲቪ ሁሌ ብታይ ደስ ይለኛል ነገር ግን በቲቪ ከምታይ ብሰራ እመርጣለሁ ሲሉ አሰልጣኝ ውበቱ አባተ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል ።

Editor at Hatricksport

Facebook

ዮሴፍ ከፈለኝ

Editor at Hatricksport