“የወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ ቡድኑ ጋር እንደሌሉና የት እንዳሉም እንደማያውቁ የክለቡ ስራ አስኪያጅ ገለጹ”

👉👉የወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ ቡድኑ ጋር እንደሌሉና የት እንዳሉም እንደማያውቁ የክለቡ ስራ አስኪያጅ ገለጹ፡፡ የክለቡ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አሸናፊ አማረ

“ከአሰልጣኙ ጋር ያለው ጉዳይ አልየለትም የት እንዳሉም አናውቅም ባለፉት ሁለት ቀናት በነበረው ልምምድ ላይም አልነበሩም ቡድኑ በሚገኝበት ሆቴልም ውስጥም የሉም ምክንያቱ ምን እንደሆነ ስላላወቅን እየጠበቅናቸው ነው ቦርዱም በጉዳዩ ላይ ተሰብስቦ ውሳኔ ገና አልሰጠም በቀጣይ የሚሆነውን አብረን የምናየው ይሆናል” በማለት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

የፌዴሬሽኑ የዲሲፕሊን ኮሚቴ በ9ኛው ሳምንት ጨዋታ ወልዋሎ አዲግራት በባህርዳር ከተማ 3 ለ 2 በተረታበት ጨዋታ የአርቢትሩ ለሚ ንጉሴን ውሳኔ በመቃወም ግጥሚያው 13 ደቂቃ እንዲቋረጥ አድርገዋል በሚል የጨዋታና የገንዘብ ቅጣት ያስተላለፈው እንደሌሎቹ አሰልጣኞችና ክለቦች ጠርቶ ሳያናግራቸው መሆኑ ከደንቡ አንጻር ተገቢ አይደለም በሚል ጥያቄ ማስነሳቱ ታውቋል፡፡ አሰልጣኙ ከክለቡ ጋር ያላቸው ግንኙነት ከመቋረጡም በላይ ክለቡና አመራሮቹ አስፈላጊ ድጋፍ አልሰጡኝም በሚል ለከፍተኛ የክለቡ አመራሮች የስራ መልቀቂያ ደብዳቤ ማስገባታቸውም እየተነገረ ይገኛል፡፡

በመጀመሪያዎቹ 10 ጨዋታዎች 8 ግብ ብቻ የተቆጠረበት ወልዋሎ አዲግራት ባለፉት 3 ጨዋታዎች ግን 9 ግብ ማስተናገዱ ተጨዋቾቹ ላይ የደረሰውን የስነልቦና ጉዳትና በራስ መተማመናቸው መውረድን ያሳያል ተብሏል፡፡አሰልጣኙ ቀሪ 2 ጨዋታዎች ላይም ቡድናቸውን የማይመሩ በመሆኑ ምናልባት ሃሳባቸውን ቢቀይሩ እንኳን በቴክኒክ ቦታው ላይ ቡድናቸውን የሚመሩት በ2ኛ ዙር ላይ ይሆናል፡፡ በ14ኛው ሳምንት የሊጉ መርሃግብር ወልዋሎ አዲግራት በቀጣዩ እሁድ አዳማ ላይ ከሜዳ ውጪ አዳማ ከተማን ይገጥማል፡፡

Editor at Hatricksport

Facebook

ዮሴፍ ከፈለኝ

Editor at Hatricksport