የወላይታ ድቻ ተጫዋቾች ቅሬታቸውን አሰምተዋል

 

የወላይታ ድቻ እግር ኳስ ክለብ ተጫዋቾች በኮሮና ቫይረስ ውድድሮች ከተቋረጡ ጀምሮ የሶስት ወር ደሞዛቸው ባለመከፈሉ ምክንያት ቅሬታቸውን አሰምተዋል።

በሀገራችን ኮሮና ቫይረስ ከተከሰተ ጊዜ ጀምሮ የስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ከታገዱ ወራቶች ሲቆጠሩ በዚህም የተለያዩ ክለቦች ለተጫዋቾቻቸው ደሞዝ ባለመክፈል ቅሬታ ይነሳል። የዚህ ችግር ሰለባ የሆኑት የወላይታ ድቻ ተጫዋቾች ከ3ወር በላይ ደሞዝ እንዳልተከፈላቸው የክለቡ ተጫዋቾች በተለይ ለሀትሪክ ስፖርት በስልክ ቅሬታቸውን አሰምተዋል። “ከሶስት ወር በላይ ደሞዝ አልተከፈለንም በዚህም ከፍተኛ ችግር ውስጥ ገብተናል በተደጋጋሚ የሚመለከተውን አካል አነጋግረን ዛሬ ነገ ከ ከማለትውጪ ምንም ለጥያቄያ ምላሽ ሳይሰጡን ወራት ተቆጥረዋል በተጨማሪም ክለቡ ግዜያችን በምን መልኩም እያሳለፍን እንደሆነ በቅርበት አለመጠየቁ ይበልጥ ነገሩ አስከፊ አድርጎብናል ያሉት ተጫዋቾቹ እኛ የቤተሰብ አስተዳዳሪዎች ነን መተዳደሪያችንም እግር ኳሱ ስለሆነ ክለቡ ምላሽ የማይሰጠን ከሆነ ጉዳዩን ወደ ህግ እንወስደዋለንም ብለዋል”። ሲሉ የክለቡ ተጫዋቾች ቅሬታቸውን አሰምተዋል።

ጉዳዩን ለማጣራት ባደረግነው ጥረት በተደጋጋሚ ወደ ክለቡ አመራሮች ስልክ ብንደውልም ስልክ ባለማንሳታቸው ምክንያት የነሱን ምላሽ ሳናካትት ቀርተናል።