የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሚካሄደውን ጥረት ቅዱስ ጊዮርጊስ የስፖርት ማህበር ከግማሽ ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ አይ ቪ ፍሉድስ ለገሰ፡፡

 

በአዲስ አበባ ከተማ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል የሚደረገውን ቅድመ ዝግጅት ለማጠናከር የአስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ ኢ/ር ታከለ ኡማ በፌስቡክ ገጻቸው ተቋማትና ባለሃብቶች በዓይነትና በገንዘብ የድጋፍ እጆቻቸውን እንዲዘረጉ ጥሪ ማቅረባቸው የሚታወስ ነው፡፡

የምክትል ከንቲባውን የድጋፍ ጥሪ ተከትሎ የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር ስራ አመራር ቦርድ ከደርባ ሲሚንቶና ከሞሃ ለስላሳ መጠጦች ኢንዱስትሪ አክሲዮን ማህበር ጋር በመተባበር ግምታቸው ከግማሽ ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ አይቪ ፍሉድስ ለከተማ አስተዳደሩ ለግሷል፡፡


የስፖርት ማህበራችን ስራ አመራር ቦርድ ፕሬዚዳንት አቶ አብነት ገብረመስቀል ድጋፉን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በመገኘት ለምክትል ከንቲባ ኢ/ር ታከለ ኡማ በዛሬው እለት አስረክበዋል፡፡
አቶ አብነት ገብረመስቀል ቅዱስ ጊዮርጊስ ህዝባዊ ክለብ እንደመሆኑ ለአገራዊ ጥሪዎች አፋጣኝ ምላሽ መስጠትና የቅርብ ድጋፍ ማድረግ የስፖርት ማህበሩ የቆየ ባህልና ልምድ እንደሆነ ገልጸው አሁን የአለምን ህዝብ እያስጨነቀ ያለው የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ከሀገራችን እስኪጠፋ ድረስ ማህበሩ በሚችለው አቅም ሁሉ ድጋፍ ማድረጉን የሚቀጥል መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ህብረተሰቡ የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት በጤና ባለሙያዎችና በሚመለከታቸው መንግስታዊ ተቋማት አማካኝነት የሚተላለፉ የመከላከያ ምክሮችን በመቀበል ራሱን እንዲጠብቅም አሳስበዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢ/ር ታከለ ኡማ አስተዳደሩ ላቀረበው ጥሪ ቅዱስ ጊዮርጊስ በአጭር ጊዜ ውስጥ ላደረገው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡


ሌሎች መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማትም በዓይነትም ይሁን በገንዘብ ድጋፋቸውን እንዲያደርጉ ምክትል ከንቲባው ጠይቀዋል።

via- st George S A

hatricksport team

Hatricksport team

Facebook

hatricksport team

Hatricksport team