የካፍ ፕሬዝዳንት አህመድ አህመድ ከሰአታት በኋላ አዲስ አበባ ይገባሉ፡፡

 

ከማዳጋስካር አንታናናሪቦ ተነስተው ወደ ካይሮ ግብጽ የሚጓዙት አህመድ አህመድ ምሽት አንድ ሰአት ላይ አዲስ አበባ ይገባሉ፡፡

ፕሬዝዳንቱ ትራንዚት ሲያደርጉ ባላቸው 4 ሰአት ላይ በፌዴሬሽኑ የእራት ግብዣ የሚደረግላቸው ሲሆን ፕሬዝዳንቱ አቶ ኢሳያስ ጅራና ዋና ጸሃፊው ባህሩ ጥላሁን ጋር ተቀብለዋቸው በቦሌ ቪ አይ ፒ ሳሎን ከአህመድ አህመድ ጋር በኢትዮጲያ እግርኳስ ዙሪያና ሌሎች ጉዳዮች ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የፌዴሬሽኑ ምንጮች ገልጸዋል፡፡ የአፍሪካ ዋንጫና ሌሎች ቁሳቁሶች ካይሮ ከሚገኘው ቢሮው የተዘረፈው ካፍ ከግብጽ የጸጥታ ሃይሎች ጋር ዝርፊያው ላይ ምርመራ መጀመራቸው ታውቋል፡፡

Editor at Hatricksport

Facebook

ዮሴፍ ከፈለኝ

Editor at Hatricksport