የካፍ ኤሊት ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ የፊፋን አናሊስስ እንዲሰሩ ሃላፊነት ተሰጣቸው፡፡

የአለም አቀፉ እግር ኳስ ማህበር ፊፋ (FIFA) ከየካቲት 30/2012 – መጋቢት 4 ቀን 2012 ዓ.ም. በስዊዘርላንድ ያዘጋጀውን FIFA HIGH PERFORMANCE PROGRAMMES GLOBAL FOOTBALL ECO SYSTEM ስልጠና ተከታትለው አጠናቀዋል፡፡

ፊፋ በዙሪክ ባዘጋጀው በዚህ ወርክ ሾፕ ላይ የተሳተፉት ኤሊት ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ ለአምስት ቀን የተሰጠውን ስልጠና በብቃት ካጠናቀቁ በኋላ ኃላፊነት ሰጥቷቸዋል፡፡

ኢንስትራክተሩ በሁለት አህጉሮች መስራታቸውን ከግምት በማስገባት በእስያና በአፍሪካ አህጉሮች በ8 አገሮች የሚሰሩ ሲሆን አዲሱን የፊፋ GLOBAL FOOTBALL ECO SYSTEM ANALYSIS በህንድ፤ በሊባኖስ፤ በናይጄሪያ፤ በደቡብ ፈአፍሪካ፤ በዛምቢያ በዝምባብዌ በማላዊና በኬንያ ላይ የሚሰሩ ይሆናል፡፡

የአለም አቀፉ እግር ኳስ ማህበር ፊፋ (FIFA) ባዘጋጀው ስልጠና ላይ እንዲሳተፍ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ጉዞው በአጭር ጊዜ ውስጥ እነዲሳካ ላደረጉት ሃገራዊ ትብብር ኢንስትራክተሩ አመስግነዋል፡፡

የኢትዮጵያ እግር ኳስ  ፌዴሬሽንም ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ  ለዚህ ሃላፊነት በመብቃቱ የተሰማውን ደስታ ይገልፃል፡፡

Via-EFF

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor