የኢ.እ.ፌ ፕሬዝዳንት ለሰዓታት ቦሌ አየር ማረፊያ ከቆዩት የካፍ ፕሬዝዳንት ጋር ተወያዩ

የካፍ ፕሬዝዳንት አህመድ አህመድ ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ዛሬ ማምሻውን በአዲስ አበባ ተወያዩ።
ወደ ካይሮ ለማቅናት ዛሬ ነሐሴ 30/2012ዓ.ም ከቀኑ 9፡49 ከማዳጋስካር በኢትዮጵያ አየር መንገድ የተጓዙት የካፍ ፕሬዚዳንት ማምሻውን ቦሌ አለማቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ የኢ.እ.ፌ ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ኢሳያስ ጅራ እና የጽ/ቤት ኃላፊው አቶ ባህሩ ጥላሁን አቀባበል አድርገውላቸዋል። የካፍ ፕሬዝዳንት አህመድ አህመድ በቦሌ አየር ማረፊያ የVIP Salone ለሰዓታት የቆዩ ሲሆን በቆይታቸው ከአቶ ኢሳያስ ጅራ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገዋል።


ካፍ በታህሳስ ወር አመታዊ ጠቅላላ ጉባኤውን በአዲስ አበባ ለማድረግ ስለወሰነ መደረግ ስለሚገባቸው ቅድመ ዝግጅቶች ላይ ውይይት አድረገዋል።
በቀጣይ የሚደረጉ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ውድድሮች እና ኮቪድ 19 በአፍሪካ ላይ እያሳደረ ስላለው ተጽኖ እንዲሁም ኢትዮጵያ ውድድሮችን ለማስጀመር እያደረገች ስላለው ጥረት ተወያይተዋል።
ማምሻውንም ወደ ግብጽ ካይሮ ያቀኑ ሲሆን ሴፕቴምበር 10 የካፍ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ በቪዲዮ በመታገዝ ስብሰባ በማካሄድ የተለያዩ ውሳኔዎችን ያስተላልፋል ተብሎ ይጠበቃል።

Via-EFF

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor