የኢት.እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከመስከረም 1/2013 ጀምሮ አቶ መኮንን ኩሩ የሚባል ዳይሬክተር የለኝም አለ

 

..ቦታውን አቶ ሰለሞን ገ/ስላሴ በጊዜያዊነት ይዘውታል

ከውስጥም ከውጪም በመጣብኝ ጫና ስራዬን ለቀኩ… ሲላቸው ቦታዬ ላይ ነኝ ..ሲያሻቸው ደግሞ ፈቅጄ ቦታውን ለቅቄያለሁ ሲሉ የነበሩትና ቢያንስ ባለፉት 10 አመታት ቦታው ላይ ይኑሩም አይኑሩም ተቃውሞ ሲቀርብባቸው የነበሩት የፌዴሬሽኑ የቴክኒክ ዳይሬክተር አቶ መኮንን ኩሩ ያቀረቡትን የስራ መልቀቅ ጥያቄ ተቀባይነት በማግኘቱ ከሃላፊነታቸው ተነስተዋል፡፡

አቶ መኮንን ባቀረቡት የስራ መልቀቂያ ደብዳቤ “…..ከውጭ ባለብኝ ጫና የሚፈለገውን ያህል ልሰራ ስላልቻልኩ……”ከሚል ሃረግ ጋር ቦታውን እንደማይፈልጉት
በመግለጽ ሰው እስኪገኝ ድረስ ስራውን እየሰሩ እንደሚቆዩ ገልጸው የኢንስትራክተርነት ስራቸውን እንደሚሰሩ በማረጋገጥ ፌዴሬሽኑን በሙያቸው ለማገልገል ዝግጁ መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡

የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው አባላት እጃቸው ላይ ያለውን ስራ እስኪጨርሱ ድረስ እንዲቆዩ ይደረግ በሚልና አይ አልፈልግም ካለ ውጤታማ ስለማይሆን ይሰናበት በሚሉ ሁለት ሃሳቦች ላይ ከተወያዩ በኋላ የለቁኝን ጥያቄ ተቀብለውታል፡፡

አመራሮቹ ከዚህም በላይ የፌዴሬሽኑ ምክትል ጸሃፊ አቶ ሰለሞን ገ/ስላሴ በጊዜያዊነት ሃላፊነቱን ደርበው እንዲሰሩ መወሰናቸው ታውቋል

Editor at Hatricksport

Facebook

ዮሴፍ ከፈለኝ

Editor at Hatricksport