የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የዝውውር መስኮት ከቀናቶች በኋላ ይከፈታል እኛም ዝውውሩን በተመለከተ ነጥብ አንስተናል

የዝውውር መስኮቱ ሰኞ የካቲት 16 ተከፍቶ እስከ መጋቢት 16 ይቆያል።

ለአንድ ወር በሚቆየው ይህ የዝውውር መስኮት ክለቦች ፌደሬሽኑ ባስቀመጠው 50 ሺህ ብር የዋጋ ተመን ወይስ ክለቦች ከዚህ በተቃራኒ ለተጫዋቾች ዝውውር ከመጋረጃ ጀርባ በሚደረጉ ሸሮች ፋይናንሳቸው ወጪ ያደርጋሉ። የፕሪምየር ሊጉ እና ክለቦች ትልቅ ፈተና የነበረው ስፖርታዊ ጭዋነት ችግር ተቀርፎ መልካም ገፅታን መፍጠር በጀመረበት ወቅት። መልኩን ቀይሮ የፋይናንስ ችግር በከፍተኛ ደረጃ ህልውናቸውን እየተፈታተነ ይገኛል። እንደምሳሌነት ለማንሳት ያክል ጅማ አባ ጅፋር፣ አዳማ ከተማ የዚህ የፋይናንስ ችግር ሰለባ ናቸው። የክለቦቹ ተጫዋቾች በተደጋጋሚ በደሞዝ አለመከፈል ምክንያት ልምምድ ሲያቆሙ የተስተዋለ ሲሆን ከፍተኛ የደሞዝ ክፍያ ለመክፈል እንደሚቸገሩም ክለቦቹ በግልፅ ተደምጠዋል። ከፍተኛ የሞዝ ተከፋይ የሆኑት የአዳማ ከተማ ሶስት ተጫዋቾች ክለቡ እንዲያሰናብታቸው የመልቀቂያ ወረቀት አስገብተዋል። በአጠቃላይ በመንግስት የሚደጎመውን ሊጋችን በመገንዘብ ለክለቦች የፋይናንስ ችግር ፈተና ሊሆንባቸው እንደሚችል ተረድቶ የአንድ ተጫዋች የጣርያ ደሞዝ 50,000 ያደረገው ፌደሬሽኑ የሚያስመሰግነው ጉዳይ ነው። ቢሆንም ክለቦች ይህን በመተላለፍ የሚመደብላቸውን በጀት ለመቀራመት ሲባል ከመጋረጃ ጀርባ በሚደረጉ ሕገ-ወጥ ዝውውሮች ምክንያት ለከፍተኛ የፋይናንስ ችግር ተዳርገዋል እየተዳረጉ ነው ይዳረጋሉም። ክለቦች ለህልውናቸው መታገል ያለባቸው እራሳቸው ከመሆናቸው ጋር ተያይዞ ይህን ችግር እስካልፈቱ ድረስ በተረጋጋ መንፈስ ውድድራቸውን ያደርጋሉ ማለት ዘበት ነው።

 

Hatricksport website Editor

Facebook

ሚሊዮን ኃይሌ

Hatricksport website Editor