ሰበር ዜና |የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ላልተወሰነ ጊዜ ተቋረጠ

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን እና የሊግ ካምፓኒ ዛሬ ከሰዓት በፌዴሬሽኑ መሰብሰቢያ አዳራሽ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የዘንድሮ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ላልተወሰነ ጊዜ መቋረጡን ይፋ አድርገዋል፡፡ ክለቦችም ተጫዋቾችን ለመጠበቅ በዚህ ጊዜ ልምምዶችን ማቋረጥ እንዳለባቸው የእግር ኳሱ አስተዳዳሪው አካል አሳውቋል፡፡

በደብረዘይት በሚገኘው የክቡር ይድነቃቸው ተሰማ አካዳሚ ለፕሪሚየር ሊጉ ዝግጅታቸውን ሲያደርጉ የነበሩት ቅዱስ ጊዮርጊሶች በኮሮና ስጋት ምክንያት ልምምዳቸውን ከነገ ጀምሮ እንደሚያቆሙ ከክለቡ የወጡ መረጃዎች ጠቁመዋል፡፡

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor