የኢትዮጵያ ፉትቦለርስ ኢንተርሚዲየሪ ተመሰረተ !

 

በሀገራችን ኢትዮጵያ እምብዛም ትኩረት በማይሰጠው የተጫዋቾች ወኪል ስራ በመጨረሻም ፍሬ አፍርቶ ማህበር መመስረቱ ይፋ ተደርጓል ::

ማህበሩ በላከው ደብዳቤ እንዳስታወቀው ፍቃድ ያላቸው ወኪሎች ብቻ የእግር ኳስ ተጫዋች ፣ አሰልጣኞችን ፣ ለእግር ኳስ ተጫዋቾች እና አሰልጣኞች የተሻለ ዕድል ማመቻቸት ፣ እግር ኳሱን ወደ ኋላ የሚጎትቱ ድርጊቶችን ለመታገል ማህበሩ እንደተቋቋመ ተገልጿል ::

በተለይም በሀገራችን በተጫዋቾች ዝውውር ላይ በቁጥር በርከት ያሉ የተጫዋቾች ወኪል እንደመኖራቸው ያላቸው ሚና በሌሎች ወይም ሶስተኛ ወገን ጣልቃ ገብነት እና በተለያዩ ምክንያቶች ተገቢውን እና የልፋታቸው ውጤት ሲያዩ የማይስተዋል ሲሆን የዚህ ማህበር መመስረት ይህን ችግር ይቀርፋል ተብሎ ይታሰባል ::Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor