መነሻ ገጽ U-20 ብሄራዊ ቡድን የኢትዮጵያ ከ20 አመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ፍሬው ኃይለገብርኤል ስለ ዛሬው ጨዋታ ይናገራሉ
U-20 ብሄራዊ ቡድንሉሲዎቹዜናዎች

የኢትዮጵያ ከ20 አመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ፍሬው ኃይለገብርኤል ስለ ዛሬው ጨዋታ ይናገራሉ

አጋራ
አጋራ

 

ዛሬ ከቀኑ 10:00 ከ20 አመት በታች የኢትዮጵያ ሴቶች ቤህራዊ ቡድን የቡሩንድ አቻውን ቡሩንዲ ላይ ኢንዋሪ ስታዴም ላይ የአለም ዋንጫ ቅድመ ማጣሪያውን ያደርጋል ። አሰልጣኙ ስለ ዛሬው ጨዋታ የተናገሩትን የሀትሪክ ስፖርቱ ሚሊዮን ኃይሌ የሚከተለውን አዘጋጅቶላችዋለ።

እንግዲህ ወደ ቡሩንዲ መጥተን ያለውን ነገር አይተናል። በተለይ አልቲቱዱ(altitude) እንዴት እንደሆነ ላማጥናት ሞክሪያለው ሜዳቸውንም ተመልክቻለው። እኔም ተጫዋቾቼም በዚህ ነገር ተሳትፎ እያደረግንበት ነው። ዛሬ 10 ላይ እንግዲህ ጨዋታ አለን ከተጫዋቾቼ ጋር ቡዙ ነገርን አውርቻቸዋለው እነሱም ጋር ያለው ተነሳሽነት ደስ ይላል። ስለዚህ ከሜዳ ውጭ እንደመጫወታችን መጠን ለታክቲካል ዲሲፒሊን ተገዢ ሆን መጫወት እንዳለብን ነግርያቸዋለው። ሁለተኛው ነገር ደግሞ ሳይኮሎጂካሊ (psychologically) እንዴት ነው ማሸነፍ የምንችለው ብለን በደምብ ከልጆቹ ጋር ተነጋግረናል። ከተጫዋቾቼ መሀል ልምድ ያላቸውም የሌላቸውም አሉ እነዚህን አጣምረን እንዴት ነው ወደ ጨዋታ ምንገባው የሚለው ነገር ላይ ነው ትኩረት አድርገን ስንሰራ የነበረው።በሜዳችንም ከሜዳችን ውጭ ኳስ ተቆጣጥረን መጫወት እንዳለብን እና መሳሳት እንደሌለብን ነው። ሌላው አጨራረስ ላይ ምን ማድረግ እንዳለብንም ከተጫዋቾቼ ጋር ተነጋግሪያለው። በመጨረሻም አሰልጣኙ የዛሬውን ጨዋታ አሸንፈው እንደሚወጡ በእርግጠኝነት ተናግረዋል። ሀትሪክ ስፖርትም ለሴት ቤሕራዊ ቡድናችን ልካም ውጤት ይመኛል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

ገዛኸኝ ደሳለኝ (ሸገር ከተማ) : ክለቡ ከ ኢትዮጵያ ቡና ጋር ባደረገው የ26ኛ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በዝናባማው ጨዋታ በመቻል ሲረታ የጣናው ሞገድም አሸንፏል

እጅግ በከባድ ዝናብ ታጅቦ በተደረገው ጨዋታ መቻል የሊጉን መሪ ሲዳማ ቡናን 3ለ1...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀድያ ሆሳዕና ፣ ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ ወሳኝ ድል አግኝተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን መርሀግብር ሀዋሳ ከተማ ወደ ሊጉ መሪ የሚጠጋበትን ዕድል...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ፈረሰኞቹ በድል ሲቀጥሉ ንግድ ባንክ እና ድሬዳዋም አሸንፈዋል

ቅዱስ ጊዮርጊስ ተከታታይ ድሉን ወደ ቋቱ ሲከት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከጨዋታ ብልጫ...