በተመስገን ዳና እየተመራ ለመጀመርያ ጊዜ በሩዋንዳ ኣዘጋጅነት እየተካሄደ ባለው የሴካፋ ዞን ለኣፍሪካ ዋንጫ ከ17 ዓመት በታች ማጣሪያ ጨዋታ አየተሳተፈ ያለው ኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ዛሬ ኣመሻሽ ላይ የኡጋንዳ ኣቻውን በ13ኛው ደቂቃ ላይ በሃዋሳ ከተማ ወጣት ቡድን ተጨዋች ምንተስኖት ኢንድሪያስ ብቸኛ ግብ ኣሸንፎ መውጣት ችሏል።

በምድብ ሁለት ከጁቡቲ፣ደቡብ ሱዳን፣ኬንያና ኡጋንዳ የተደለደለችው ኢትዮጵያ የምድብዋ ቀጣይ ጨዋታ ማክሰኞ ከጁቡቲ ብሄራዊ ቡድን ታደርጋለች።
የውድድሩ ኣሸናፊ እና ሁለተኛ ሚወጣው ብሄራዊ ቡድን በቀጥታ በታንዛንያ ኣዘጋጅነት የሚካሄደው የኣፍሪካ 17 ዓመት ውድድር ተሳታፊ ይሆናሉ።
አስተያየት ይስጡ