መነሻ ገጽ ሪፖርት የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ምድብ ሐ የ4 ሳምንት ጨዋታ መሪው አርባምንጭ ከተማ በኤዶም ኮድዟ ሁለት ግቦች ነገሌ አርሲን 2-1 በማሸነፍ መሪነቱን አጠናክሯል።
ሪፖርትአርሲ ነገሌአርባምንጭ ከተማዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ምድብ ሐ የ4 ሳምንት ጨዋታ መሪው አርባምንጭ ከተማ በኤዶም ኮድዟ ሁለት ግቦች ነገሌ አርሲን 2-1 በማሸነፍ መሪነቱን አጠናክሯል።

አጋራ
አጋራ

በመጀመሪያው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ግዜ ባለሜዳው አርባምንጭ ከተማ የተሻለ መንቀሳቀስ ችሏል። አብዛኛውን የጨዋታ ክፍለ ግዜ የጎል ሙከራዎች ያልታዩበት በተደጋጋሚ በሚሰሩ ጥፍቶች ጨዋታው የሚቆራረጥበት ክፍለ ግዜ ነበር።

አዞዎቹ የመጀመሪያ ሙከራቸውን በ10ደቂቃ ማድረግ ሲችሉ ከምንተስኖት አበራ የተሻገረለትን ያለቀለት ኳስ አጥቂው ኤዶም ኮድዟ ሳይጠቀምት የቀረው አጋጣሚ አዞዎቹን ቀዳሚ ምታደርግ ነበረች። በሚያሰለች የጨዋታ እንቅስቃሴ የቀጠለው የሁለቱ ክለቦች ጨዋታ በ30ደቂቃ ባለሜዳወቹ አዞዎቹ ከቀኝ መስመር አንበሉ ወርቅይታደስ አበበ ያሻማውን ኳስ በጥሩ ቦታ ላይ የነበረው ኤዶም ኮድዟ በግንባሩ በመግጨት አዞዎቹን ቀዳሚ ማድረግ ችሏል።
እንግዳወቹ አርሲ ነገሌዎች በአጥቂያቸው አላዛር ዝናብ በሚያደርጋቸው የግል ክህሎት በስተቀር ምንም አይነት ሙከራ ሳያደርጉ ወደ መልበሻ ክፍል ገብተዋል።

በሁለተኛው አጋማሽ እንግዳው አርሲነገሌ የአቻነት ጎል ለማግኘት ወደፊት ለመጫወት ጥረት ሲያደርጉ በአንፃሩ አዞዎቹ መከላከልን መሰረት ያደረገ አጨዋወት ሲተገበሩ ተመልክተናል። በተለይም 55 እና 60ደቂቃ ለጎል የደረሱ ኳሶችን ሞክረው 70 ደቂቃ ላይ ጥሩ ሲንቀሳቀስ በነበረው አላዛር ዝናቡ የግል ጥረት የአቻነት ጎል ማስቆጠር ችለዋል።


ከጎሉ መቆጠር በሃላ አርባምንጭ ከተማ የመሀል ሜዳ ተጫዋቹን ማሜ በአጥቂው ፍቃዱ በመቀየር የማጥቃት ሃይላቸውን ጨምረው በ85ኛው ደቂቃ ፍቃዱ ከግራ መስመር ያሻማውን ኳስ የእንግዳው ቡድን ተከላካይ በእጅ መንካቱን ተከትሎ የተሰጠውን ፍፁም ቅጣት ምት ኤዶም ኮድዟ በጨዋታው ለራሱ ሁለተኛውን ለቡድኑ አሸናፊ ምታደርገውን ግብ በማስገባት አዞዎቹ ሙሉ 3ነጥብ እንዲያገኝ አድርጓል።በዚህም መሰረት አርባምንጭ ከተማ በ10 ነጥብ የምድቡ መሪ መሆን ችሏል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

ገዛኸኝ ደሳለኝ (ሸገር ከተማ) : ክለቡ ከ ኢትዮጵያ ቡና ጋር ባደረገው የ26ኛ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በዝናባማው ጨዋታ በመቻል ሲረታ የጣናው ሞገድም አሸንፏል

እጅግ በከባድ ዝናብ ታጅቦ በተደረገው ጨዋታ መቻል የሊጉን መሪ ሲዳማ ቡናን 3ለ1...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀድያ ሆሳዕና ፣ ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ ወሳኝ ድል አግኝተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን መርሀግብር ሀዋሳ ከተማ ወደ ሊጉ መሪ የሚጠጋበትን ዕድል...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ፈረሰኞቹ በድል ሲቀጥሉ ንግድ ባንክ እና ድሬዳዋም አሸንፈዋል

ቅዱስ ጊዮርጊስ ተከታታይ ድሉን ወደ ቋቱ ሲከት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከጨዋታ ብልጫ...