ሚያዝያ 26 ትግራይ ስታድየም ላይ በተካሄደው የደደቢት እና ፋሲል ጨዋታ ላይ በታየው የስፖርታዊ ጨዋነት ጉድለት ምክንያት ከዚህ በፊት ደደቢት ላይ ተወስኖ የነበረው የቅጣት ውሳኔ የይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ ውሳኔው ሙሉ በሙሉ በመቀልበስ መቐለ 70 እንደርታ ላይ ኣንድ ጨዋታ በዝግ ስታድየም እንዲጫወት፣የ75 ሺህ ብር እንዲከፍል እንዲሁም 5 የተጎዱትን የፋሲል ተጨዋቾች የህክምና ወጪ እንዲሸፍን ተወስኖበታል።
የዲስፒሊን ኮሚቴው ከዚህ ቀደም ደደቢት ላይ ሁለት ጨዋታዎች በዝግ ስታድየም እንዲያካሂድ እንዲሁም የ150 ሺህ ብር ቅጣት እስተላልፎ የነበረ ቢሆንም ደደቢትና ፋሲል ባቀረቡት የይግባኝ ጥያቄ መሰረት ጉዳዩን ሲመለከተው የነበረው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ ቅጣቱን ሙሉ በሙሉ ከደደቢት በመሻር መቐለ 70 እንደርታ ላይ ወስኗል።
አስተያየት ይስጡ