መነሻ ገጽ ሰበር ዜና የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የ19ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕርምየር ሊግ መርሀግብር በነበረው በወልዲያ እና ፋሲል ከተማ ጨዋታ ዙርያ የሚከተለውን ውሳኔ ወስኗል።
ሰበር ዜናዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የ19ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕርምየር ሊግ መርሀግብር በነበረው በወልዲያ እና ፋሲል ከተማ ጨዋታ ዙርያ የሚከተለውን ውሳኔ ወስኗል።

አጋራ
አጋራ

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን 19 ሳምንት የኢትዮጵያ ፕርምየር ሊግ መርሀግብር በነበረው በወልዲያ እና ፋሲል ከነማ ጨዋታ ዙርያ የሚከተለውን ውሳኔ ወስኗል።

1. የወልዲያ እግርኳስ ክለብ ከፋሲል ከተማ እግርኳስ ክለብ ጋር 03/08/2010.ዓ.ም ያደረገው ጨዋታ በፎርፌ ተሸናፊ ሆኖ ለፋሲል ከተማ እግርኳስ ቡድን 3ነጥብ እና 3ጎል እንዲመዘገብለት ተወስኗል፡፡

2. በወልዲያ ሼክ አሊ አላሙዲ ስታድየም ጥፋት ከፈፀሙበት ከሚያዝያ 02/08/2010 ዓ.ም አስከ ሚያዚያ 02/08/2011 ዓ.ም ድረስ ጨዋታዎች የመጫወት መብት እንዲያጡ እና በኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የሚካሄዱ ማንኛውም ውድድሮች እንዳይካሄዱ ተወስኗል፡፡

3. ክለቡ የሚያደርጋቸውን የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ እግርኳስ ውድድሮች ከከተማው 500ኪ.ሜ በላይ በሚገኝው ሜዳ ላይ ውድድሩን እንዲያካሂድ ተወስኗል፡፡

4. የክለቡ ደጋፊዎች በፈፀሙት ሁከት፣ እረብሻ እና ጥፋት 250,000 ብር የገንዘብ ቅጣት እንዲከፉሉ ተወስኗል፡፡

5. ክለቡ በዳኞች ላይ በደረሰው ጉዳት በሚገኝበት ሆስፒታል እንዲያሳክም እና ወደፊት በሚቀርበው ማስረጃ መሰረት ክለቡ ለኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ጽ/ቤት ድረስ ቀርቦ እንዲከፍል ተወስኗል፡፡

6. ክለቡ ደጋፊዎቻቸውን ስለ ስፖርታዊ ጨዋነት እስከ ሚያዚያ 02/08/2011 ዓ.ም ድረስ በጥልቀት እንዲያስተምሩ፡፡ ይህንን ካልፈፀሙ የወልዲያ እግርኳስ ክለብ ከውድድሩ እንዲታገድ ተወስኗል፡፡

7.አሰልጣኝ ዘማርያም ወ/ጊዮርጊስ የጨዋታወን ዳኛ በማነቅ፣ በመሳደብ እንዲሁም ተጫዋቾችን እና ደጋፊዎችን ለረብሻ እንዲነሳሱ በማድረግ 1ዓመት ከማንኛውም እግርኳስ አሰልጣኝነት እንዲታገዱ እና ብር 25,000 ቅጣት እንዲከፍሉ ተወስኗል፡፡

8.ተጫዋች ብሩክ ቃልቦሬ ዳኛ ለመማታት ሙከራ በማድረጉ እና ተጫዋቾችን እንዲሁም ደጋፊዎችን ለረብሻ በማነሳሳት 1 ዓመት ከማንኛውም እግር ኳስ ተጫዋችነት እንዲታገድ እና ብር 10,000 የገንዘብ ቅጣት እንዲከፍል ተወስኗል፡፡

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀድያ ሆሳዕና ፣ ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ ወሳኝ ድል አግኝተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን መርሀግብር ሀዋሳ ከተማ ወደ ሊጉ መሪ የሚጠጋበትን ዕድል...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ፈረሰኞቹ በድል ሲቀጥሉ ንግድ ባንክ እና ድሬዳዋም አሸንፈዋል

ቅዱስ ጊዮርጊስ ተከታታይ ድሉን ወደ ቋቱ ሲከት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከጨዋታ ብልጫ...

ዋልያዎቹዜናዎችየኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን

አንጋፋው አሰልጣኝ በስማቸው የእግር ኳስ ማሰልጠኛ አካዳሚ ሊገነባላቸው ነው

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የቀድሞ አሰልጣኝ ኢንስትራክተር ሰውነት ቢሻውን ለማመስገን እና ዕውቅና ለመስጠት...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

1. ፉአድ ኢብራሂም (ኢትዮጵያ ቡና) : ከታች በተጠቀሱት 5 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ...