የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የገንዘብ ድጋፍ አደርገ

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በአደገኛ ሁኔታ በአለማችን ብሎም በሀገራችን ኢትዮጵያ እየተዛመተ የሚገኘውን የኮሮና ቫይረስ ለመከላከል ያስችል ዘንድ የኢ.እ.ፌ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት በስልክ ኢ.እ.ፌ ፕሬዝዳንት ጋር ውይይት ካደረጉ በኋላ ፌዴሬሽኑ የፋይናንስ እጥረት እንዳለበት ቢታወቅም ከዚህ ጉዳይ የሚብስ ነገር የለም በማለት የ500,000.00 ብር ( የአምስት መቶ ሺህ ብር) ድጋፍ አደረገ።
ይህንን ገንዘብ በብሔራዊ ደረጃ የተቋቋመው ኮሚቴ ባዘጋጀው የባንክ ሒሳብ ገቢ የተደረገ ሲሆን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ ያሳወቁ ሲሆን ክለቦችም ይህንን ከፊታችን የተጋረጠውን ቫይረስ ለመከላከል መንግስት የጀመረውን ተግባር በመደገፍ የበኩላቸውን እዲወጡ አደራ ብለዋል።
አያይዘውም በየአካባቢው የሚደረጉ የማስ ስፖርት እንቅስቃሴዎች ለበሽታው ተጋላጭነታችንን ሊጨምሩ ስለሚችሉ ብሎም ለቫይረሱ መስፋፋት ምቹ ሁኔታን ስለሚፈጥሩ መንግስት በሰጠው አቅጣጫ መሰረት በጋራ ከሚሰሩ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ማህበረሰቡ እዲቆጠብ አሳስበዋል ።

Via – EFF

hatricksport team

Hatricksport team

Facebook

hatricksport team

Hatricksport team