የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ዋና ጸሃፊ ዶ/ር ኢያሱ መርሃ ጽድቅ ከቦታቸው እንዲነሱ ተወሰነ

 

ላለፉት ጥቂት ወራቶች የፌዴሬሽኑን የጽ/ቤት ስራ ሲመሩ የነበሩት ዶ/ር ኢያሱ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ዛሬ ባደረገው ስብሰባ ሃላፊነታቸውን በብቃት አልተወጡም የጽ/ቤቱ
አስተዳደራዊ ስራን አልመሩም በሚል ውሳኔውን ሰጥቷል፡፡
ከፌዴሬሽኑ ውስጥ አዋቂ በተገኘ መረጃ ዶ/ሩ በቅርብ ጊዜያቶች እየወሰኑ ያለው ውሳኔ ቅሬታ እያስነሳ ሲሆን የዲሲፕሊንና የይግባኘ ሰሚ ኮሚቴ ውሳኔ ላይ ጣልቃ በመግባት እንዲሁም ተፈጻሚ ባለማድረግ የክለቦች ቅጣት ላይ ተግባራዊ እንዳይደረግ በማዘዝ ደመወዝ ለመክፈል ወራቶች እንዲጨመርላቸው በማድረግ በኮሚቴዎች ስራ ላይ ጣልቃ ገብተዋል በሚል ቅሬታ ሲሰማባቸው ቆይተዋል፡፡ በሳምንታት በፊት አሠልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ በዲሲፕሊን ኮሚቴ ሲቀጣ ይግባኝ በመጠየቅ እስከዛው ድረስ የዲሲፕሊን ኮሚቴ ውሳኔ እንዲታገድ ቢጠይቅም በህግ የተሠጠውን መብት ወደጎን በማለት ሃላፊነታቸውን አልተወጡም በሚል ቅሬታ ቀርቦባቸዋል፡፡ ስራ አሰፈጻሚዎቹም በዚህና ሌሎች አስተዳደራዊ ክፍተቶች ጫና ውስጥ ሳይገቡ እንዳልቀሩ ተገምቷል፡፡
ቦታው እንደ እሳት የሚፋጀው ይሄ ቦታን በሚገባ ለመምራት ጠንካራ አመራርና ውሳኔ ሰጪነት የሚጠበቅ ቢሆንም የአለማያ ዩኒቨርስቲ ምሩቁ ግን ሳይከብዳቸው እንዳልቀረ ይገመታል፡፡ የስራ አስፈጻሚው ውሳኔ ከነገ ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረግ ይጠበቃል፡፡ ስለመረጃውወደ ዋና ፀሃፊው ጋር ብደውልም ስልካቸውን ሊያነሱ አልቻሉም፡፡

Editor at Hatricksport

Facebook

ዮሴፍ ከፈለኝ

Editor at Hatricksport