የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የቀድሞ ተጨዋች ሳምሶን ሽፈራው /ጆሮ/

በመሸሻ ወልዴ /G.BOYS/

“በእዚህን ወቅት አስባችሁኝ ላደረጋችሁልኝ ስጦታ በጣም አመሰግናለው”

የእግር ኳስን በክለብ ደረጃ ለኢትዮጵያ ቡና ለቅዱስ ጊዮርጊስ ለሰሚት ለወንጂ ስኳር እና ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ተጫውቶ ያሳለፈው ዓመለ ሸጋው እና ፈጣኑ የኮሪደር ስፍራው ተጨዋች ሳምሶን ሽፈራው /ጆሮ/ በአሜሪካንም ሆነ እዚሁ በአዲስ አበባ ከተማ ላይ የሚገኙት የቀድሞ ጓደኞቹም ሆኑ የእግር ኳስንም አብረዉት የተጫወቱት ተጨዋቾች በተጨዋችነት ዘመኑ ለሀገር ላበረከተው አስተዋፅኦ በማሰብ ግምቷ ግማሽ ሚሊየን የምትደርስ የመኪና ስጦታ ያበረከቱለት ሲሆን ይኸው ዓመለ ሸጋም ተጨዋች ለተደረገለት የመኪና ስጦታ ሁሉንም ጓደኞቼንም ሆነ በማስተባበሩ ላይ ለተሳተፉት ከፍተኛ ምስጋናዬን በፈጣሪ ስም አቀርብላቸዋለሁም ብሏል።
የእግር ኳስ ጨዋታ ዘመኑ ላይ በቀኝ የኮሪደር ስፍራ ላይ ፈጣን የማጥቃት እንቅስቃሴን በማድረግ ለአጥቂዎች የግብ ኳስ ለማቀበል ከፍተኛ ጥረት ያደርግ የነበረው እና በኢትዮጵያ ቡና ክለብ የተጫዋችነት ዘመን ቆይታውም ቡና የሱዳኑን ክለብ ባሸነፈበት የአዲስ አበባ ጨዋታው ላይ የመጀመሪያ ኢንተርናሽናል ጎሉን ለቡድኑ ያስቀጠረው ሳምሶን ከኳሱ ባሻገር በቀልደኝነቱም የሚታወቅ ሲሆን በእዚህ አስቸጋሪ ወቅት ላይ የተደረገልኝ የመኪና ስጦታ በእውነቱ በጣም ያስደሰተኝ እና ለውለታቸውም ፈጣሪ ብድራቸውን ይክፈልልኝም በማለት ሀሳቡን ቋጭቷል።

Editor at Hatricksport website

Facebook

መሸሻ ወልዴ

Editor at Hatricksport website