የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝና የካፍ ኤሊት ኢንስትራክተር አብርሀም መብራቱ ለስልጠና ወደ ዙሪክ አምርተዋል፡፡

የአለም አቀፉ እግር ኳስ ማህበር ፊፋ (FIFA) ባዘጋጀው /FIFA High Programes Global football Eco System Analysis Training/ ላይ ለመሳተፍ በዛሬው እለት 30/06/2012 ዓ.ም ወደ ዙሪክ አምርተዋል፡፡
ፊፋ የቀድሞ የአርሰናል ክለብ አሰልጣኝ በነበሩት አርሴን ዊንገር የሚመራ አዲስ የልማት ፕሮግራም ቀርፆ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል፡፡

ይህ ስልጠና እግር ኳስ በተጠናና በተደራጀ መልኩ ለሁሉም የፊፋ አባል ሀገራት እንዲስፋፋ አላማ ያደረገ ነው፡፡


የካፍ ኤሊት ኢንስትራክተር አብርሀም መብራቱ የአለም አቀፉ እግር ኳስ ማህበር ፊፋ (FIFA) ከየካቲት 30/2012 ዓ.ም አስከ መጋቢት 4/2012 ዓ.ም ድረስ በሚቆየው ወርክ ሾፕ ላይ የሚካፈሉት ኢንስትራክተር አብርሀም መብራቱ በአገራችን ካሉ ጥቂት የካፍ ኢንስተትራክተሮች አንዱ ሲሆኑ በቅርቡም ሞሮኮ ራባት ላይ ካፍ ባዘጋጀው የኣፍሪካ ኤሊት ኮንትኔንታል
ኢንስትራክተር ኮርስ የሙያ ማሻሻያ ላይ በመሳተፍ በብቃት የጨረሱ መሆናቸው አይዘነጋም፡፡
እንደዚህ አይነቶቹ ስልጠናዎች ተጨማሪ አቅም እንደሚሆንላቸው ይጠበቃል፡፡

hatricksport team

Hatricksport team

Facebook

hatricksport team

Hatricksport team