የኢትዮጵያ ቡና የመጀመሪያው ዙር ጉዞ ሲዳሰስ

 

በዛሬው የክለቦች የመጀመሪያው ዙር እይታችን ኢትዮጵያ ቡና በመጀመሪያው ዙር ምን ይመስል ነበር የሚለው በተከታዩ አዘጋጅተንላችኃል።

በአሰልጣኝ ካሳየ አራጌ እየተመሩ የመጀመሪያውን ዙር በ18 ነጥብ 11ኛ ደረጃን ይዘው ማጠናቀቅ የቻሉት ኢትዮያ ቡናዎች። በሊጉ ጅማሬ በሚከተሉት ኳስን መሰረት ያደረገ ማራኪ አጨዋወት የሊጉ ክስተት ሆነው የነበሩት ቡናማዎቹ ጥንካሪያቸው በውጤት ለመግለፅ ተቸግረው በተደጋጋሚ ነጥብ ለመጣል ተገደው የወራጅ ቀጠናው ተርታ ተሰልፈው ነበር። አበዛኛውን ጊዜ ቡድኑ ከኋላ መስመር መስርቶ መጫወትን ታሳቢ አድረጎ ለመጫወት ሲያስብ ይህም በበርካታ የሊጉ ሳምንታት ላይ በተጋጣሚ ቡድኖች ጫና ውስጠጥ እየገቡ ተደጋጋሚ ሙከራዎች ብሎም ጎሎችን ሲያስተናግዱ ለመመልከት ችለናል ፡፡ ቡድኑ ምንም እንኳ የተሳኩ ቅብብሎሽን ከሊጉ ክለቦች የተሻለ ማደረግ ቢችልም ጠቃሚነታቸው እዚህ ግባ የማይባል አይይለም ፡፡ ምክንያቱም አብዛኞቹ የተሳኩ ቅብብሎሽ በራስ ሜዳ ላይ ይደረጉ የነበሩ ስለሆነ። ቡድኑ በማጥቃት እንቅስቃዎች ላይ ሲቸገር እና የማጥቃት እንቅስቃሴዎች ላይ የፈጣሪ አማካይ ተጫዋቾች እጥረት ሲታይበት በተለይም በክረምቱ ክለቡን ከሀዋሳ ከነማ የተቀላቀለው ታፈሰ ሰለሞን በጉዳት ምክንያት የታሰበውን አለመሆን ቡድኑ ላይ ክፈተት መፍጠሩ ተስተውሏል ፡፡

ኢትዮጵያ ቡናዎች በመጀመሪያ ዙር ካደረጓቸው ጨዋታዎች አራቱን በድል ሲወጡ በአምስቱ ተሸንፈው በቀሪው ስድስት ጨዋታ ነጥብ ተጋርተዋል። በሜዳቸው ካደረጓቸው ሰባት ጨዋታዎች አራቱን ሲያሸንፍ በቀሪዎቹ ሶስት ጨዋታዎች ነጥብ ተጋርተዋል። ቡናማዎች በሜዳዎ ሶስት ነጥቦችን ይዞ የሚወጣ ካልቻለ ግን ነጥብ የሚጋራ እንጂ ሽንፈትን የሚያስተናግዱ አይደሉም። በሜዳቸው ባደረጓቸው ጨዋታዎች አስራ አምስት ግቦችን የተቃራኒ መረብ ላይ አሳርፎ አምስትም ግቦች አስተናግዷል። ይህ ማለት ደግሞ ቡናማዎቹ በሊጉ ጅማሮ የነበራቸውን ጥንካሬ ታግዘው በርካታ ግቦችን በማስቆጠር በሜዳው ከፍተኛ ግብ የማግባት አቅም እና ጠንካራ የመከላከል አቅም እንደነበራቸው የቁጥራዊ መረጃው ያሳያል። ኢትዮጵያ ቡና በሜዳው ሲጫወት 2.1 ሲያገባ 0.7 ግቦች ይቆጠሩበታል።

ኢትዮጵያ ቡናዎች በመጀመሪያው ዙር ከሜዳቸው ውጭ ባደረጓቸው ጨዋታዎች ስምንት ጨዋታዎች በአራቱ ተሸንፈው በአራቱ አቻ ተለያይተዋል። ይህም ማለት ደግሞ ኢትዮጵያ ቡና ሌላኛው ከሜዳው ውጭ ነጥብ ይዞ ለመውጣት የሚቸገር የሊጉ ቡድን ያደርገዋል። በዚህም መሰረት ኢትዮጵያ ቡና ከሜዳው ውጭ ምንም ጨዋታ ማሸነፍ አልቻለም። ከሜዳቸው ውጭ ባደረጉት ጨዋታ አምስት ማስቆጠር ሲችሉ በአንፃሩ አስራ አንድ ግቦች አስተናግዷል። በሜዳቸው ያላቸው ጠንካራ የፊት መስመር እና የኋላ ተከላካይ ስፍራ በሜዳው ውጭ ያለውን ጥንካሬ ከሜዳው ወጥቶ ሲጫወት ለተጋጣሚ ቀላል ያደርገዋል። ኢትዮጵያ ቡና በየጨዋታው በአማካይ 0.6 ሲያገባ 1.3 ግቦች ይገቡበታል። ቡናዎች በመጀመሪያው ዙር 20 ግቦችን በተጋጣሚው ላይ ሲያሳርፍ 16 ግቦች ተቆጥሮባቸዋል። በ15 ሳምንት ጉዟቸው ባደረጉት ጨዋታ በየጨዋታው 1.3 ግቦችን ሲያመርቱ 1 ግብ ያስተናግዳል። ሀድያ ሆሳዕናን እና ሀዋሳ ከተማን ያሸነፉበት ጨዋታ ላይ 5-0 እና 4-1 በቅደም ተከተል ያሸነፉበት ጨዋታ በርካታ ግቦች አስቆጥረው ያሸነፉበት ጨዋታ ነው። በአራት ጨዋታዎች ግብ ሳይቆጠርባቸው መውጣት ሲችሉ በስድስት ደግሞ ሳያገቡ ወጥተዋል። ለተከታታይ አምስት ጨዋታዎች ነጥብ የጣሉበት አስከፊው የመጀመሪያው ጉዟቸው ሆኖ ተመዝግቧል። እንዳለ ደባልቄ አምስት ግቦችን በማግባት የመጀመሪያው ዙር የክለቡ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ በመሆን ደምድሟል።

ኢትዮጵያ ቡና ባለፈው አመት የመጀመሪያውን ዙር
22 ነጥቦችን ሰብስቦ 8 ደረጃን በመያዝ ነበር ያጠናቀቀው። በዘንድሮው አመት ግን በአራት ነጥቦች ዝቅ ብሏል።

የኢትዮጵያ ቡና የመጀመሪያው ዙር ጠንካራ እና ደካማ ጎን

ቡድኑ እንደ ጥንካሬ ከሚነሱለት ነገሮች አንዱ በመስመር በኩል የሚያሰልፋቸው ተጫዋቾች ቡድኑ በሊጉ ላስቆጠራቸው ጎሎች ትልቁን ድርሻ መውሰድ ሲችሉ ፡፡ በተለይ ለየጨዋታው ተለዋዋጭ የጨዋታ አቀራረብ ይዘው አለመቅረባቸውን ተከትሎ በሌሎች ቡድኖች ተገማች እየሆነ ነጥብ ለመጣል የተገደደበት በደካማ ጎኑ ይነሳል።

በሁለተኛው ዙር የሚጠበቅባቸው

ቡናማዎች ምንም እንኳን ግብ ማስቆጠር ቢችሉም ይህ ጥንካሪያቸው በሜዳቸው ብቻ የማይወሰን ከሆነ በሁለተኛው ዙር ጠንካራ ተፎካካሪ እንዲሆኑ ይረዳቸዋል። ኳስ የማንሸራሸሩ ሂደት ከራሳቸው የመጫወቻ ሜዳ ባሻር ወደ ተጋጣሚ በመልቀቅ ጫና በመፍጠር ያገኟቸውን አጋጣሚዎች ወደ ግብነት መቀየር ይኖርባቸዋል።

Hatricksport website Editor

Facebook

ሚሊዮን ኃይሌ

Hatricksport website Editor