መነሻ ገጽ ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣ የኢትዮጵያ ቡና ቤተሰቦች 8 ኪ.ሜ ሩጫ በተሳካ ሁኔታ ተካሂዷል፡፡
ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣ

የኢትዮጵያ ቡና ቤተሰቦች 8 ኪ.ሜ ሩጫ በተሳካ ሁኔታ ተካሂዷል፡፡

አጋራ
አጋራ

የኢትዮጵያ ቡና ቤተሰቦች 8 ኪ.ሜ ሩጫ በደመቀና በተሳካ ሁኔታ ተካሂዷል፡፡

የኢትዮጵያ ቡና ቤተሰቦች ሩጫውን ለመሣተፍ ከጠዋቱ 12 ሰዓት ጀመሮ ነበር መሰባሰብ የጀመሩት ፤የሩጫው መነሻው በጀሞ ስልሳ ሰባት ማዞሪያ በለቡ መብራት ሃይል አድርጎ በጀርመን አደባባይ እንዲሁም በጀሞ ሚካኤል አድርጎ የክለቡ ስተዲየም በሚገነባበት ሜዳ ላይ  እንደሚጠናቀቅ ተናግረዋል ፡፡ ይህ የሁለተኛው ዙር የቡና ቤተሰቦች ሩጫ 8 ኪ.ሜ የሸፈን ሲሆን ሜዳችን በራሳችን በሚል መሪ ቃል  ተካሂዷል  ፡፡

ሩጫው በአትሌት አለቃ ደራርቱ ቱሉ የተጀመረ  ሲሆን በእለቱም የመንግስት ባለስልጣናንትና የፌዴሬሽኑ አመራሮች ፤ የመከላከያ የማርሽ ባንድ በተገኙበት የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ ሰታድዬም የመሰረት ድንጋይ ተጥሏል ፡፡



 የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ የሥራ አመራር ቦርድ ፕሬዚደንት መቶ አለቃ ፈቃደ ማሞ ባደረጉት ንግግር ደጋፊውን አመስግነው በመሮጫ ቲሸርጥ እጥረት ከስህተታችን ተምረን ለቀጣይ በመቶ ሺ የሚቆጠር እንደሚዘጋጅና ተናግረዋል ደጋፊውን በሁሉም መልኩ አመስግነዋል::


 

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌደሬሽን ፕሬዚደንት አቶ ጁነይዲን ባሻ  ባደረጉት ንግግርም እዚህ መጥተን ጨዋታ ለማየት ያብቃን ኢትዮጵያ ቡና ባለብዙ ደጋፊና ቀደምት ከለብ ነው የዚህ የስታዲየም ግንባታ ከክለቡ ባለፈም ለሃገሪቱ ስፖርት ብዙ ጥቅም አለው እንኳን ደስ አላችሁ እንኳን ደስ አለን ብለዋል!

የዕለቱ የክብር እንግዳ የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ልማትና ግብይት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክትር አቶ ሳኒ ረዲ የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብን በሁሉም ዘርፍ ቀዳሚ ለማድረግ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከክለቡና ከደጋፊው ጎን እንደሚቆም አረጋግጠዋል የስታዲየሙን ግንባታም በመከታተል የሚጠበቅባቸውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ ክለቡ የእናንተ ነው እዚህ በመገኘቴ ደስ ብሎኛል ኢትዮጵያ ቡና ተያይዘን ወደ ትልቅ ደረጃ እናደርሳለን ሲሉ በስሜት የተሞላ ደስ የሚል ንግግር አድርገዋል ደጋፊውም ድጋፉን ገልፆላቸዋል


የዕለቱ የክብር እንግዳ የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ልማትና ግብይት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክትር አቶ ሳኒ ረዲ፤ የተከበሩ አቶ ጁነይዲን ባሻ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌደሬሽን ፕሬዚደንት፤ መቶ አለቃ ፈቃደ ማሞ የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ የሥራ አመራር ቦርድ ፕሬዚደንት፤ ክብርት ዶክተር ኮረኔል ደራርቱ ቱሉ የሥራ አመራር ቦርድ አባለት የደጋፊ ማህበሩ አመራሮች እንዲሁም በርካታ ደጋፊዎች በተገኙበት የስታዲየሙ የመሰረት ድንጋይ ተቀምጧል!

SOURCE -SOL BUNNA

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣዜና እረፍትዜናዎች

የጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ አጭር የህይወት ታሪክ

ጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ ከእናቱ ከወ/ሮ ጌጤ ገ/ስላሴ እና ከአባቱ ሀምሳ አለቃ ወልዴ...

ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣ

ሀትሪክ አሁንም ቀጠሮ ማክበር ስልጣኔ ነው በሚለው አቋሟ ጸንታለች

ቅዳሜ ጠዋት በቀጠሮ  ቀናችን  እርስዎ ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ አዳዲስና ያልተሰሙ መረጃዎችን...

ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣዜናዎች

ሀትሪክ አሁንም ቀጠሮ ማክበር ስልጣኔ ነው በሚለው አቋሟ ጸንታለች

ቅዳሜ ጠዋት በቀጠሮ  ቀናችን  እርስዎ ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ አዳዲስና ያልተሰሙ መረጃዎችን...