ለ2022 የኳታር ዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ነሐሴ 29 በባህርዳር ስታድየም ሚካሄደው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን እና የሌሴቶ ጨዋታ በአማራ መገናኛ ብዙሃን የቀጥታ ስርጭት ሽፋን ሚያገኝ ይሆናል።
በባህርዳር ስታድየም ሚካሄዱ የብሄራዊ ቡድን እና የክለቦች ጨዋታ በቀጥታ እያስተላለፈ ሚገኘው አማራ ቲቪ ነሐሴ 29 ሚካሄደውን ጨዋታ በቀጥታ ለኢትዮጵያ ህዝብ እንደሚያደርስ አስታውቋል።
በባህርዳር በመከተም ዝግጅቱን እያደረገ ሚገኘው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ሱራፈፌ ዳኛቸውን በግል ምክንያት፣አምሳሉ ጥላሁን በጉዳት ለጨዋታው አይጠቀምም።