የኢትዮጲያ ቡና ደጋፊዎች እርዳታ እየሰጡ ነው

የኳስ ሜዳና አካባቢው የኢትዮጵያ ቡና መረዳጃ እድር አባላት ለመስተዳድሩ በቁሳቁስ ደረጃ ከፍተኝ ልገሳ አደረጉ፡፡ አባላቱ 80ሺ ብር የሚጠጋ ድጋፋቸውን ለክቡር ከንቲባው አስረክበዋል፡፡ ከዚህ ውጪ የቡና ደጋፊዎች ክለባቸው ከመቀለ 70 እንደርታ ጋር ሊያደርገው የነበረው ጨዋታ ቢራዘምም ስታዲየም ተገኝተው ከደጋፊው ካሰባሰቡት ገንዘብ ቆሼ ተብሎ ወደሚጠራው ስፍራ በመጓዝ 541 አቅመ ደካሞችን እረድተዋል፡፡ ድጋፉ ዕድሜያቸው ከ100 አመት በላይ የሆነና አካል ጉዳተኞችን ያካተተ ሲሆን ለእያንዳንዳቸው 2 ኪሎ ሩዝ 2 ሳሙና 1 ፈሳሽ ሳሙና 1 ሳኒታይዘር አከፋፍለዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በተለያዩ ሁለት ቦታዎች ላይ ትልልቅ ሮቶ እንዲሰቀል አድርገዋል፡፡

በዚህ የእርዳታ መርሃ ግብር ላይ የክለቡ ተጨዋች አህመድ ረሺድ ሽሪላውና አርቲስት ማርያማዊት አባተ ተሳታፊ እንደነበሩ ታውቋል፡፡
በዚህ አጋጣሚ የርዳታ እጃችሁን ዘርጉ ለህዝብ እናሳውቃለን

Editor at Hatricksport

Facebook

ዮሴፍ ከፈለኝ

Editor at Hatricksport