ለመጪው የአፍሪካ ዋንጫ ቅድመ ዝግጅት ይረዳቸው ዘንድ ሀገራት ከወዲሁ የወዳጅነት ጨዋታዎችን ለማካሄድ በዝግጅት ላይ ይገኛሉ ።
ይህንንም ተከትሎ በጠንካራ ሊጓ የምትታወቀው ደቡብ አፍሪካ በኮሳፋ ዞን ውስጥ ከሚገኙ ሁለት ሀገራት ጋር በመጪው መስከረም 27 እና ጥቅምት 1 የወዳጅነት ጨዋታዎችን ለማድረግ ከወዲሁ በዝግጅት ላይ እንደሚገኙ ይፋ አድርገዋል ።
የሰሜን አፍሪካዊቷ ሀገር ቱኒዚያ ከጎረቤት ሀገር ሱዳን እና ናይጄርያ ጋር በቀጣይ ወር ለመጫወት ቀነ ቀጠሮ መያዛቸው ተሰምቷል ።
በኢትዮጵያ ምድብ የምትገኘው ኮት ዲቯር ከቱኒዚያ እና ናይጄርያ ጋር የወዳጅነት ጨዋታዎችን እንደሚያደርጉ ይፋ ተደርጓል ።
አስተያየት ይስጡ