መነሻ ገጽ ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣ ​የአዳማ ከተማው ሱራፌል በትርፍ አንጀት ሕመም ለአንድ ወር ከሜዳ ይርቃል
ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

​የአዳማ ከተማው ሱራፌል በትርፍ አንጀት ሕመም ለአንድ ወር ከሜዳ ይርቃል

አጋራ
አጋራ

​‘‘ቡናን ማሸነፍ መቻላችን ወደ ዋንጫው ፉክክር 

እንድንገባ ከፍተኛ ተነሳሽነት ፈጥሮልናል”

ሱራፌል ዳኛቸው

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የውድድር ተሳትፎ 

ላይ ለጠንካራውና የሳምንቱ መጨረሻ ጨዋታ 

ላይም ኢትዮጵያ ቡናን 2-1 ላሸነፈው የአዳማ ከተማ 

እግር ኳስ ክለብ የመሀል ሜዳ ላይ የሚጫወተው 

ሱራፌል ዳኛቸው በቅርቡ የትርፍ አንጀት ሕምም 

ያጋጠመው ሲሆን ተጨዋቹም በእዚህ ሕመሙ 

ሳቢያ ለአንድ ወር ከሜዳ ይርቃል፡፡

የአዳማ ከተማው ስኬታማ የአማካይ ስፍራ 

ተጨዋች ሱራፌል ጌታቸው የትርፍ አንጀት 

ሕመም ጉዳት እንዳለበት ያወቀው በቅርቡ የክለቡ 

አንድ ልምምድ ላይ የህመም ስሜት ሲሰማው 

ያንን ህመሙን ለማወቅ ወደ ሆስፒታል ባመራበት 

ወቅት ከዶክተሮች ተነግሮት ሲሆን ተጨዋቹምይህ ህመሙ ከታወቀ በኋላም ካለፉት ሶስት 

ቀናት አንስቶ ከሜዳ ለአንድ ወራት እንዲርቅም 

ሊነገረው ችሏል፤ የአዳማ ከተማው ሱራፌል 

የትርፍ አንጀት ህመሙ ካጋጠመው በኋላ 

ክለቡ እሁድ ዕለት ከኢትዮጵያ ቡና ጋር 

በነበረው ጨዋታ ላይ መሰለፍ ያልቻለ ሲሆን 

ተጨዋቹ በእዚያ ፍልሚያ ላይ ለመኖር 

ባልችልም ክለባችን ቡናን ማሸነፍ መቻሉ በጣም 

አስደስቶኛል፤ ያገኘነው ድልም ወደ ዋንጫው 

ፉክክር እንድናመራ ከፍተኛ ተነሳሽነትን 

ይፈጥርልናል በማለት አስተያየቱን ለሀትሪክ 

ስፖርት ጋዜጣና ድህረ-ገጽ ሊሰጥ ችሏል፡፡

የአዳማ ከተማ ክለብ በሊጉ የ11ኛ ሳምንት 
ጨዋታው ኢትዮጵያ ቡናን 2-1 በማሸነፍ በሊጉ 

የደረጃ ሰንጠረዥ የሁለተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠ 

ሲሆን ክለቡ በቀጣይ ጨዋታዎቹም ይህንን 

የአሸናፊነት መንፈሱን በመቀጠል ዘንድሮ 

የሊጉን ዋንጫ ለማንሳትም የሚጫወትበት 

እድሉ እንደሚኖረውም አማካዩ ሱራፌል 

አስተያየቱን ጨምሮ ሰጥቷል፡፡

የአዳማ ከተማ ክለብ በሊጉ ያለፉት 

ሁለት ተከታታይ ጨዋታዎች ኤሌክትሪክና 

ኢትዮጵያ ቡናን ያሸነፈበት ውጤትና የቡድኑ 

ጥንካሬ ከፍተኛ ተደናቂነትን እያተረፈለት 

ሲሆን ከእዚህም በኋላ ክለቡ ከጨዋታ ወደ 

ጨዋታ ሲያመራ የበለጠ ጥንካሬውን በማሳየት 

ስኬታማነቱን ይቀጥላልም በሚል ሱራፌል 

ይናገራል፡፡

የአዳማ ከተማ ክለብ በሊጉ ላይ ስላለው 

አቋም እንደዚሁም ዘንድሮ ሊያሳኩት ስላሰቡት 

ውጤት ስለራሱ ወቅታዊ አቋምና ካጋጠመው 

ሕመም በፍጥነት ወደ ሜዳ ሲመለስ ለክለቡ 

ሊያበረክተው ስላሰበው ግልጋሎት አጠር ባለ 

መልኩ ጠይቀነው ምላሹን ሊሰጠን ችሏል፤ 

ሱራፌል ስለ ክለባቸው የአሁን ሰዓት አቋም 

በተመለከተ አስተያየቱን ሲሰጥ የአዳማ ከተማ 

ክለብ አሁን ላይ ቀደም ሲል አድርጓቸው 

ከነበሩት ግጥሚያዎች አኳያ ከፍተኛ መሻሻልን 

በማሳየት ወደ ውጤታማነት እያመራ ያለ 

ክለብ ነው፤ ተደጋጋሚ ጎል የማስቆጠር 

ችግሩን ባለፉት ሁለት ጨዋታዎች ላይ ቀርፎ 

ግጥሚያዎችን ሊያሸንፍ ችሏል፤ አሁንም ይህ 

ስኬታማነቱ የሚቀጥልም ይሆናል፤ ካለ በኋላ 

ስለዘንድሮ የውድድር ዘመን ተሳትፎአቸው 

ሊያመጡት ስላሰቡት ውጤትም ሲናገር አዳማ 

በሊጉ ላይ ጠንካራ ከሚባሉት ክለቦች መካከል 

አንዱ የሆነ ነው፤ ጥሩ ጥሩ ልምድ ያላቸው 

ተጨዋቾችንና አበረታች እንቅስቃሴ የሚያሳዩ 

ወጣት ልጆችንም የያዘ በመሆኑ የእዚህ ዓመት 

ላይ የምንፎካከው ዋንጫውን ለማንሳት ነው 

ይህንንም ተግባራዊ ለማድረግ በርትተንም 

እንሰራለን ሲል አስተያቱን ሰጥቷል፡፡

የአዳማ ከተማው ሱራፌል ስለወቅታዊ 

አቋሙና ካጋጠመው ሕመም ወደ 

ሜዳ ሲመለስም ስለሚሰጠው ግልጋሎት 

ጠይቀነውም ሲመልስ ‘‘የአዳማ ከተማ 

ቡድን ውስጥ ያለኝ ወቅታዊ አቋም ጥሩና 

የሚያበረታታ ነው፤ ያም ቢሆን ግን ሰሞኑን 

ያጋጠመኝ የትርፍ አንጀት ሕመም በሜዳ 

ላይ ክለቤን የኢትዮጵያ ቡና ጋር ያደርግነውን 

ጨዋታ ጀምሮ በቀጣይም በሚኖሩት ጥቂት 

ጨዋታዎች ላይ እንዳልሰለፍ ስለሚያደርገኝ 

ያ ሊያስከፋኝ ችሏል፤ ቢሆንም ግን ከሕመሜ 

ድኜ ስመጣ ለአዳማ ብዙ ጥቅምን በመስጠት 

ክለቡን ከጓደኞቼ እርዳታ ጋር ለሻምፒዮናነት 

እንደማበቃው በጣም እርግጠኛ ነን በማለት 

አስተያየቱን አጠቋሏል፡፡

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሲዳማ ቡና የሊጉን መሪነት ሲያጠናክር ኤሌክትሪክ እና አፄዎቹም አሸንፈዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ ሲዳማ ቡና ፣ ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ እና ፋሲል...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

ገዛኸኝ ደሳለኝ (ሸገር ከተማ) : ክለቡ ከ ኢትዮጵያ ቡና ጋር ባደረገው የ26ኛ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በዝናባማው ጨዋታ በመቻል ሲረታ የጣናው ሞገድም አሸንፏል

እጅግ በከባድ ዝናብ ታጅቦ በተደረገው ጨዋታ መቻል የሊጉን መሪ ሲዳማ ቡናን 3ለ1...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀድያ ሆሳዕና ፣ ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ ወሳኝ ድል አግኝተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን መርሀግብር ሀዋሳ ከተማ ወደ ሊጉ መሪ የሚጠጋበትን ዕድል...